Be'kur (Jun 08, 2026)
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የአብክመ ግብርና ቢሮ የፔ.ሳ.ፒ.ዬ ፕሮጀከት (Productivity enhancement support for the integrated Agro-Industrial parks and youth employment PESAPYE) project ማስተባበሪያ ዩኒት በጣባና ብልጭት ለሚያሰራው መስኖ ግንባታ አገልግሎት የሚውሉ የችግኝ ጣቢያ እና የተፋሰስ ልማት መሳሪያዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል ፤
ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ እንድትወዳደሩ ይጋብዛል ፡፡
- በዘርፉ የተሰማሩና በ2018 ዓ.ም የታደሰ ንግድ ፈቃድ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይ መሆናቸዉን የሚገልጽ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ህጋዊ ተጫራቾች ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት ባህርዳር ከተማ ቀበሌ 08 በሚገኘዉ ውኃና ፍሳሽ አገልግሎት ዋና መስሪያ ቤት ህንጻ የፔ.ሳ.ፒ.ዬ ማስተባበሪያ ዩኒት ቢሮ ቁጥር 41 በአካል በመቅረብ የጨረታ ሰነዱን በነፃ በመውሰድ መወዳደር የሚችሉ መሆኑን እናሳዉቃለን፡፡
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 058 320 8786 በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡
የአብክመ ግብርና ቢሮ