የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ሐረሪ ሪጅን የፕሪንተር ቀለም (ቶነር) እቃዎች እና የተሽከርካሪ ቅባት ውጤቶች በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል – test3.diretenders.com

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ሐረሪ ሪጅን የፕሪንተር ቀለም (ቶነር) እቃዎች እና የተሽከርካሪ ቅባት ውጤቶች በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል


Addis Zemen (Jun 09, 2026)

የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር EEU/S.C&PGS/NCB-008/2018

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ሐረሪ ሪጅን ክዚህ በታች የተዘረዘሩትን ዕቃዎች በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

ተ.ቁ

የዕቃው አይነት

የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ

የጨረታ መዝጊያ እና መክፈቻ ቀን

1

የፕሪንተር ቀለም (ቶነር) እቃዎች ግዢ ጨረታ

67,100.00

 

መዝጊያ ሰኔ 18 ቀን 2018 ዓ.ም ጠዋት 4፡00

መዝጊያ ሰኔ 18 ቀን 2018 ዓ.ም ጠዋት4፡30

2

የተሸከርካሪ ቅባት ውጤቶች ግዢ ጨረታ

72,236.40

 

መዝጊያ ሰኔ 18 ቀን 2018 ዓ.ም ጠዋት 4፡00

መዝጊያ ሰኔ 18 ቀን 2018 ዓ.ም ጠዋት 4፡30

  1. ለሎት 1 እንዲሁም ለሎት 2 በዘርፉ የተሰማራ የዘመኑን ግብር የተከፈለበት የንግድ ፈቃድ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያለው በጨረታው መሳተፍ ይችላሉ።

2. ተጫራቾች የመንግስት ድርጅቶች በሚያወጡት ጨረታ ላይ ለመሳተፍ እንዲችሉ በግዥ ኤጀንሲ ዌብሳይት ላይ የተመዘገቡ መሆኑን ማረጋገጫ ማቅረብ አለባቸው።

3. ተጫራቾች ዝርዝር መግለጫ የያዘውን የጨረታ ሰነድ ጨረታው ከወጣበት ሰኔ 02 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰዓት 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 207 በመምጣት የማይመለስ ብር ለሎት 1- እስከ ሎት-2 ብር 300.00 /ሦስት መቶ ብር/ የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ።

4. አድራሻ፡- ሐረር ራስ ሆቴል ጀርባ የሐረሪ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ሪጅን ፅ/ቤት 2ኛ ፎቅ ሰፕላይቼን እና ፕሮፐርቲ ጀነራል ሰርቪስ ቢሮ ቁጥር 207።

5. ተጫራቾች ከጨረታ ዋስትና ማስከበሪያ የሚያቀርቡት የገንዘብ መጠን ብር፡-

ሀ. ለሎት-1 ብር 67,100.00 (ስልሳ ሰባት ሺህ አንድ መቶ ብር) ብቻ በተረጋገጠ /CPO/ ማስያዝ ይኖርባቸዋል።

ለሎት-2 ብር 72,236.40 (ሰባ ሁለት ሺህ ሁለት መቶ ሰላሳ ስድስት ብር ከ10/100) ብቻ በተረጋገጠ /CPO/ ማስያዝ ይኖርባቸዋል።

6. ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሰነዳቸውን በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ቴክኒካል “ኦሪጅናል እና ኮፒ” እና ፋይናንሻል “ኦሪጅናል እና ኮፒ” በማለት በተለያየ ፖስታ በማሸግ እና ሁለቱን አንድ ትልት ፖስታ በማድረግ ጨረታ ቁጥር EEU/S.C&PGS /NCB– 008/2018 የሚል ምልክት በማድረግ እስከ ሰኔ 18 ቀን 2018 ዓ.ም. ለሎት 1 እና ለሎት 2 ከጠዋቱ 4፡00 ድረስ ከላይ በተጠቀሰው አድራሻ ቢሮ ቁጥር 207 ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።

7. ጨረታው ከላይ በተጠቀሱት ቀንና ሰዓት ተዘግቶ በተመሳሳይ ቀን ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ባይገኙም ሰኔ 18 ቀን 2018 ዓ.ም ለሎት 1 እና ለሎት 2 ከጠዋቱ 4፡30 ላይ ይከፈታል።

8. ተጫራቾች ተጨማሪ ማብራሪያ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር 025 466 3575 መደወል ይችላሉ።

9. ድርጅቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ሐረሪ ሪጅን


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *