የጃዊ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል የግ/ፋ/ንብ/አስ/የስራ ሂደት ለሆስፒታሉ አገልግሎት የሚውሉ ፈርኒቸር የአገር ውስጥ እና ህትመት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል – test3.diretenders.com

የጃዊ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል የግ/ፋ/ንብ/አስ/የስራ ሂደት ለሆስፒታሉ አገልግሎት የሚውሉ ፈርኒቸር የአገር ውስጥ እና ህትመት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል


Be'kur (Jun 08, 2026)

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

የጃዊ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል የግ/ፋ/ንብ/አስ/የስራ ሂደት ለሆስፒታሉ አገልግሎት የሚውሉ ሎት 1. ፈርኒቸር የአገር ውስጥ ሎት 2. ህትመት በግልጽ ጨረታ አወዳድር መግዛት ይፈልጋል፡፡ 

ስለሆነም መወዳደር የምትፈልጉ ተጫራቾች የሚከተሉትን መስፈርቶች ማሟላት ይኖርባችኋል፡፡

1. በዘመኑ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ማቅረብ የሚችሉ፡፡

2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ሰርተፊኬት ማቅረብ የሚችሉ፡፡

3. ከብር 200,000 (ሁለት መቶ ሺህ ብር) በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡

4. የጨረታ ሰነዱን ዋናውንና ኮፒውን በፖስታ በማሸግ በሁሉም  ሰነዶች ላይ የድርጅቱን ህጋዊ ማህተም ሙሉ አድራሻ፣ ስልክ ቁጥር በማስፈር ለዚሁ በተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡

5. አሸናፊው ድርጅት ማሸነፉ ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ ባሉት 5 ተከታታይ ቀናት ውስጥ የውል ማስከበሪያ 10 በመቶ ማስያዝ አለባቸው፡፡

6. በጨረታ ሰነዱ ላይ የተዘረዘሩትን እቃዎች ሙሉ በሙሉ ዋጋቸውን ያልሞላ ተጫራች ከጨረታ ውጭ ይሆናል፡፡

7. የጨረታ አሸናፊ ድርጅት የሚለየው በጠቅላላ ድምር ውጤት ነው፡፡

8. የጨረታ ማስከበሪያ በኢትዮጲያ ብሄራዊ ባንክ በተመሰከረለት (ሲፒኦ) ወይም በጥሬ ገንዘብ የዋጋውን አንድ በመቶ ማስያዝ ይኖርበታል፡፡

9. ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምር ከሰኔ 1/2018 ዓ.ም እስከ ሰኔ 15/2018 ዓ.ም ባሉት ተከታታይ ቀናት ድረስ የጨረታ ሰነዱን ከጃዊ የመጀ/ደ//ግ/ፋ/ንብ/አስ/ደ/የስራ ሂደት መግዛት ይችላሉ፡፡

10. የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 300 (ሶስት መቶ ብር) ብቻ  በመክፈል መግዛት ይችላሉ፡፡

11. የጨረታ ሳጥኑ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ሰኔ 16/2018 ዓ/ም በ4:00 ታሽጎ 4:30 ይከፈታል፡፡

12. ተቋሙ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

13. ተጫራቾች የጨረታ ዝርዝሩን (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ላይ  ያገኙታል፡፡

14. እቃውን ጃዊ የመ/ደ/ሆ መካዝን ድረስ ማቅረብ የሚችሉ፡፡

15. ተቋሙ የጨረታውን ከጠቅላላ ድምሩ 20 በመቶ የመቀነስና የመጨመር መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

16. ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 058 278 03 05 በመደወል መረጃ መጠየቅ ይችላሉ፡፡

የጃዊ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *