የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን በሥሩ የሚገኙ ለመኖሪያ/ ገስት ሀውስ አገልግሎት የሚውሉ ቤቶችን አወዳድሮ ማከራየት ይፈልጋል – test3.diretenders.com

የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን በሥሩ የሚገኙ ለመኖሪያ/ ገስት ሀውስ አገልግሎት የሚውሉ ቤቶችን አወዳድሮ ማከራየት ይፈልጋል


Addis Zemen (Jun 09, 2026)

6 ዙር የመኖሪያ/ገስት ሀውስ ቤቶች ኪራይ

የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ መለያ ቀጥር .ቤ.ኮ/ብ.ግ.ጨ/አገ/12/09/2018

1. የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን በሥሩ የሚገኙ ውስጥ ለመኖሪያ/ ገስት ሀውስ አገልግሎት የሚውሉ ቤቶችን በጨረታ መለያ ቁጥር ፌ.ቤ.ኮ/../አገ/12/09/2018 ተጫራቾችን አወዳድሮ ማከራየት ይፈልጋል።

2 ኮርፖሬሽኑ ለሚያከናውነው የመኖሪያ/ ገስት ሀውስ ቤቶች ኪራይ ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሰነዳቸውንና የመወዳደሪያ ተመን ዋጋ በአንድ ፖስታ ማቅረብ አለባቸው።

3. ጨረታው የሚከናወነው በብሔራዊ ግልጽ ጨረታ ሥነዲሞክራሲያዊ ሥርዓትና ይኸንኑ አስመልክቶ በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ሪፐብሊክ የፌደራል ቤቶች ኮርፖሬሽን መመሪያ መሠረት ነው።

4. ማንኛውም ፍላጎት ያለው ተጫራች የተሟላ የጨረታ ሰነዱን ከሰኔ 01 ቀን 2018 .. እስከ ሰኔ 22 ቀን 2018 .. ቅዳሜን ጨምር ባሉት 21 ተከታታይ ቀናት ዘወትር በሥራ ሰዓት ከሰኞ እስከ አርብ 200 እስከ 1100 ቅዳሜ ከጠዋቱ 200 እስከ 600 ድረስ የማይመለስ ብር 500.00 /አምስት መቶ ብር/ በካሽ በመክፈል የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድን ለገሐር በሚገኘው በኮርፖሬሽኑ ዋና /ቤት በአካል በመቅረብ መግዛት ይችላሉ::

5. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዶቻቸውን በኮርፖሬሽኑ ዋና /ቤት በሚገኘው ዋና የመሰብሰቢ አደራሽ 1 ፎቅ ለዚሁ ታሽጎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ጨረታው በመጀመሪያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 21ኛው ቀን ወይም ሰኔ 22 ቀን 2018 .. ከሰዓት 1100 ሰዓት ድረስ እንዲያቀርቡ ሆኖ ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ብር 25,000.00 /ሃያ አምስት ሺሕ ብር/ በሁኔታዎች ላይ ያልተመሠረተ .. በፌደራል ቤቶች ኮፖሬሽን ስም ከጨረታ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው። ከጨረታው መክፈቻ ዕለትና ጨረታው ሰዓት ዘግይቶ የቀረበ የጨረታ ሰነድ ውድቅ ይደረጋል፤ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በጨረታ ሰነዱ ክፍል 1 ላይ በተገለጸበት ቀንና ሰዓት ይከፈታል።

6. ተጫራቾች ቤቶቹን በአካል ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ማብቂያው ቀን ድረስ በሥራ ቀናት ከጠዋቱ 3:00 እስከ ቀኑ 1100 ሰዓት ቤቶቹ በሚገኙበት አድራሻ ድረስ በመቅረብና ለዚሁ ሥራ በሚመደቡ ባለሙያዎችና በሚወጣው ፕሮግራም መሠረት ቤቶቹን መመልከት ይችላሉ።

7 ኮርፖሬሽኑ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::

ለተጨማሪ መረጃ

በስልክ ቁጥር 0910-48-59-48 0922-49-18-85 ወይም 0922-98-7633 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል::

ዌብሳይት/ website www.fhc.gov.et

የፖ... PO Box 299

ፋክስ ቁጥር፡ 011-5-54-60-45 / 011-5-52-46-46

የፌደራል ቤቶች ኮርፖሬሽን


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *