Addis Zemen (Jun 09, 2026)
የጨረታ ማስታወቂያ
ኩባንያችን ጢስ እሳት ውሃ ሥራዎች የኤሌክትሮ ሜካኒካል እቃዎች ፤ በጸሀይ ሀይል የሚሠራ የኤሌክትሮ ሜካኒካል እቃዎች አቅርቦት እና ተከላ (ጠላቂ ፓምፕ)፤ ቧንቧና የቧንቧ መገጣጠሚያ ፊቲንጎች እንዲሁም የማሽነሪ መለዋወጫዎች እና ኢንጅን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል።
|
ሎት |
የእቃው አይነት |
የጨረታ ማስከበሪያ |
የማቅረቢያ ቀን |
|
ሎት 1 |
የኤሌክትሮ ሜካኒካል እቃዎች |
100,000.00 |
ከ30-45 ቀን |
|
ሎት 2 |
በጸሀይ ሀይል የሚሠራ የኤሌክትሮ ሜካኒካል እቃዎች አቅርቦት እና ተከላ (ጠላቂ ፓምፕ) |
200,000.00 |
ከ45-60 ቀን |
|
ሎት 3 |
ቧንቧና የቧንቧ መገጣጠሚያ ፊቲንጎች |
100,000.00 |
ከ30-45 ቀን |
|
ሎት 4 |
የማሽነሪ መለዋወጫዎች እና ኢንጅን |
100,000.00 |
ከ30-45 ቀን |
ስለዚህ ማንኛውም በዘርፉ የተሰማራና በጨረታው መሳተፍ የሚፈልግ አቅራቢ ድርጅት ዝርዝር የጨረታ ሰነዱን በድርጅታችን ዌብ ሳይት www.tisisat.com ማግኘት ይችላል፡፡
የተጫራቾች መመሪያ፤
1. ተጫራቾች የዘመኑን ግብር ከፍለው የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የንግድ ምዝገባ የምስክር ወረቀት፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ እና የTIN ሰርተፍኬት፣ በዘርፉ ለመሰማራት የተሰጣቸውን ፈቃድ እና ተያያዥነት ያላቸውን ማስረጃዎች ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
2. ጨረታው ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ21ኛው ቀን ከቀኑ 9፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ቀን ከቀኑ 9፡30 ሰዓት ባህርዳር ከተማ አባይ ማዶ ቴዲ የአሽከርካሪዎች ማሰልጠኛ ጎን በሚገኘው ዋናው መ/ቤት ተጫራቾች እና ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ የጨረታው መዝጊያና መክፈቻ ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ ጨረታው በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሣሣይ ሰዓት ተዘግቶ ይከፈታል፡፡
3 ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በድርጅታችን ዌብ ሳይት www.tisisat.com ማግኘት ይችላሉ።
4. ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ በሰንጠረዥ የተመለከተውን ገንዘብ በCPO ወይም ያለቅድመ ሁኔታ እንደተጠየቀ ለገዥ የሚከፈል (unconditional Bank Guarantee) ማስያዝ አለባቸው፡፡
5.ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ የሚያወጡት ወጪ በተጫራቹ የሚሸፈን ይሆናል፡፡
6. ተጫራቾች የዋጋ ማቅረቢያቸውን እና ቴክኒካል ሰነዳቸውን ለየብቻ በተለያየ ፖስታ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ ተጫራች ድርጅቶች ለሚያቀርቡት ዋጋ ለእያንዳንዱን እቃ ነጠላ ዋጋ እና ጠቅላላ ዋጋ በትክክል ሞልተው በግልፅ ማስቀመጥ አለባቸው፡፡
7. ይህ ጨረታ በኩባንያችን የግዥ መመሪያ PR–03/2017 መሰረት ተፈፃሚ ይሆናል፡፡
8. ኩባንያው በጨረታ ሰነዱ ላይ ከተገለፀው መጠን 25% ቢጨምር ወይም ቢቀንስ የጨረታ አሸናፊው ውል የመያዝ ግዴታ ይኖርበታል፡፡
9. የጨረታው አሸናፊ አሸናፊነቱ በጽሁፍ ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ በ05 ቀናት ውስጥ የጠቅላላ ዋጋውን 10% የውል ማስከበሪያ ያለቅድመ ሁኔታ ለገዥ የሚከፈል (unconditional Bank Guarantee) በማሰራት ውል የመያዝ ግዴታ ይኖርበታል፡፡
10. የማቅረቢያ ጊዜ ከላይ በሰንጠረዡ ላይ በተገለፀው መሠረት መሆን አለበት። የአቅራቢዎች ዋጋ ቢያንስ ለ90 ቀናት ጨረታው ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ ፀንቶ መቆየት አለበት፡፡
11. ኩባንያው የተሻለ አማራጭ ካገኘ በዚህ ጨረታ አይገደድም ወይም ጨረታውን በሙሉ ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
12. ዕቃው ወይም አገልግሎቱ የሚቀርብበት ቦታ ባህር ዳር ከተማ የኩባንያው ጽ/ቤት መሆን አለበት።
13. ማሳሰቢያ፡- እንደ ኩባንያችን ፍላጎት ውድድሩ በሎት ወይም በእያንዳንዱ እቃ ነጠላ ዋጋ መሠረት ሊሆን ይችላል።
14. ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥራችን 058-220-48-26 /058-320-25-48/ በፋክስ ቁጥራችን 0582204830 መጠየቅ ይችላሉ፡፡
ጢስ እሳት ሥራዎች ኃ/የተ/የግ/ማህበር