ፀደይ ባንክ (አ.ማ) እንጅባራ ቅርንጫፍ ንብረቶችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል – test3.diretenders.com

ፀደይ ባንክ (አ.ማ) እንጅባራ ቅርንጫፍ ንብረቶችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል


Be'kur (Jun 08, 2026)

ለ2ኛ ጊዜ የወጣ የሐራጅ ጨረታ ማስታወቂያ

ፀደይ ባንክ (አ.ማ) እንጅባራ ቅርንጫፍ ለአቶ ሃይለማርያም አላምረው እና ወ/ሮ እመቤት አማረ ለሰጠው ብድር በዋስትና በሰንጠረዥ ከዚህ በታች የተገለፁ መያዣዎችን ለመጀመሪያ ጊዜ በአዋጅ ቁጥር 97/90 እና በተሻሻለው አዋጅ ቁጥር 216/92 በተሰጠው ስልጣን መሰረት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡

የተበዳሪው ስም

 

የመያዣ ሰጪ ስም

 

የካርታ ቁጥር / የይዞታው መለያ ቁጥር

 

ቤቱ የሚገኝ በት ቦታ

 

የቦታው ስፋት በካ/

 

የንብረቱ አይነትና አገልግሎት

የጨረታ መነሻ ዋጋ

 

የጨረታ ቀንና ሰአት

 

ጨረታ የወጣው

 

/ማርያም አላምራው እና እመቤት አማረ

/ማርያም አላምራው እና እመቤት አማረ

 

AM010011520007

እንጅባራ ከተማ

 

517.13

ለእንጨትና ብረታ ብረት

 

ብር

6,026,077.71

 

02/11/2018 / 400-600

 

2ተኛ ጊዜ

 

በመሆኑም ተጫራቾች ለጨረታ ከመቅረባቸው በፊት የሚከተሉትን ደንቦች መገንዘብ ይኖርባቸዋል፡፡

  1. ተጫራቾች የቤቱን የጨረታ መነሻ ዋጋ 1/4 (በጥሬ ገንዘብ ወይም ሲፒኦ በፀደይ ባንክ አ/ማ ስም በማሰራት ለጨረታ ማስከበሪያ በማስያዝ በጨረታው መሳተፍ ይችላሉ፡፡
  2.  ተጫራቾች በሐራጅ ለመሳተፍ ሲመጡ ማንነታቸውን የሚገልጽ መታወቂያ መያዝ ይገባችዋል፡፡ በጨረታው የሚሳተፈው በሕግ ሰውነት ያገኘ ሰው ከሆነ የፀደቀ የድርጅቱ መመሥረቻ ጽሑፍ ወይም መተዳደሪያ ደንብ፣ ሕጋዊ ሰውነት ያገኘበት የምዝገባ የምስክር ወረቀት፣ ቃላ ጉባኤ ወይም ሕጋዊ የውክልና ሠነድ ማቅረብ አለበት፡፡
  3. የጨረታ አሸናፊው አሸናፊነቱ የሚረጋገጠው የጨረታው ውጤት በሚመለከተው አካል ጸድቆ በባንኩ ደብዳቤ ሲሰጠው ይሆናል፡፡
  4. የጨረታው አሸናፊ አሸናፊነቱ ከባንኩ በደብዳቤ ከተገለፀለት ቀን ጀምሮ ያሸነፈበትን ጠቅላላ ዋጋ በ15 ቀን ውስጥ አጠቃልሎ ከፍሎ በጨረታ ያሸነፈበትን ንብረት መረከብ ይኖርበታል፡፡ በእነዚህ ቀናት ውስጥ ካልከፈለ ጨረታው ተሰርዞ ለጨረታ ማስከበሪያ በሲፒኦ ወይም በጥሬ ገንዘብ ያስያዘው ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ይሆናል፡፡ በተጨማሪም ንብረቱ ድጋሜ ለሐራጅ ሲቀርብ ለሚታየው የዋጋ ልዩነት ይጠየቃል፡፡ ላላሸነፉት ተጫራቾች ያስያዙት ሲፒኦ ይመለስላቸዋል፡፡
  5. የጨረታ አሸናፊው ከሚገዛው ንብረት ጋር የተያያዙ ማናቸውንም ለመንግሥት የሚከፈሉ ክፍያዎች፣ ግብር 15 በመቶ ተጨማሪ እሴት ታክስ የሚከፈል ከሆነ እንዲሁም ከስም ዝውውር ጋር የሚገናኙ ማናቸውንም ወጭዎች ይከፍላል፡፡
  6. ተጫራቾች ቤቱን በባንኩ አማካኝነት ጨረታው ከመካሄዱ በፊት አስቀድሞ ቀጠሮ በማስያዝ መጎብኘት ወይም ማየት ይችላሉ፡፡
  7. የጨረታው ቦታ በእንጅባራ ከተማ፣ 01 ቀበሌ በሚገኘው የፀደይ ባንክ አ.ማ እንጅባራ ዲስትሪከት 3ኛ ፎቅ በሚገኘው አዳራሽ ውስጥ ነው፡፡
  8. ባንኩ ለሽያጭ ያቀረበውን ንብረት የሚሸጠው በጥሬ ገንዘብ ወይም በከፊል ብድር ሲሆን አሸናፊው በባንኩ የብድር ፖሊሲ መሰረት አስፈላጊውን
    መስፈርቶች ካሟላ ንብረቱን በከፊል ብድር ለመግዛት መጠየቅ ይችላል፡፡
  9. የተጫራቾች ምዝገባ ከሐራጁ መዝጊያ ሰዓት 30 ደቂቃ በፊት ይጠናቀቃል፡፡
  10. ከፍተኛ ዋጋ የሰጠው ተጫራች የጨረታው አሸነፊ ነው የሚባለው ከባንኩ አሸናፊነቱን የሚገልጽ ደብደቤ በፁሁፍ ሲደርሰው ብቻ ነው፡፡
  11. ንብረቱ በገዥው ስም እንዲዞር ባንኩ ለሚመለከተው መንግስታዊ አካል ደብደቤ ይጽፋል፡፡
  12. ባንኩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር፡- 058 227 07 08 እና 09 10 30 20 03 በመደወል መረጃ መጠየቅ ይችላሉ፡፡
ፀደይ ባንክ (አ.ማ) እንጅባራ ቅርንጫፍ


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *