በሀገር መከላከያ ሚኒስቴር የሰሜን ምዕራብ ዕዝ ደ/3 ሆ/ል የሰርቪስ አገልግሎት የሚሰጡ የተለያዩ መኪናዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ አገልግሎት ግዥ መግዛት ይፈልጋል – test3.diretenders.com

በሀገር መከላከያ ሚኒስቴር የሰሜን ምዕራብ ዕዝ ደ/3 ሆ/ል የሰርቪስ አገልግሎት የሚሰጡ የተለያዩ መኪናዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ አገልግሎት ግዥ መግዛት ይፈልጋል


Addis Zemen (Jun 02, 2026)

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር A-01/2019

በሀገር መከላከያ ሚኒስቴር የሰሜን ምዕራብ ዕዝ ደ/3 ሆ/ል ለ2019 በጀት ዓመት አገልግሎት የሚውሉ የሰርቪስ አገልግሎት የሚሰጡ የተለያዩ መኪናዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ አገልግሎት ግዥ መግዛት ይፈልጋል፡፡ 

ስለሆነም በዚህ ጨረታ መወዳደር የምትፈልጉ ተጫራቾች ለ2019 በጀት ዓመት በተሽከርካሪ በኩል መሟላት ያለባቸው መረጃዎች

  • ለተሽከርካሪ ማህበራትም ይሁኑ አቅራቢ ባለንብረቶች ሲመጡ ስለንብረቱ ገላጭ የሆነ አግባብ ያለው መረጃ የታደሰ ንግድ ፍቃድ፣ ቲን ነምበር፣ የንግድ የምዝገባ ምስክር ወረቀት፣ የሶስተኛ ወገን ኢንሹራንስ ፣ተሽከርካሪውን በተመለከተ ሁሉንም ማስረጃዎች ማቅረብ የሚችል፣ ሁሉም ማስረጃዎች ንግድ ፍቃዶች /በተናጠል ኮፒ ተደርጎ በሌላ ፖስታ ታሽገው መቅረብ አለባቸው፡፡ የአንዱን ጨረታ ሰነድ ዋጋ የማይመለስ ብር 250.00 ሁለት መቶ ሃምሳ ብር/ ብቻ በመከፈል ዘወትር በስራ ሰዓት ባህርዳር ከተማ በሰ/ምዕ/ ዕዝ ደ/3 ሆል መኮድ ካምፕ ግዥ ቢሮ ቁጥር 19 ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡ የጨረታ ማስከበሪያ /BID BOND-CPO ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመስረተ የባንክ ዋስትና GARANTE ማስያዝ አለበት፡፡
  • የሰርቪስ አገልግሎት የሚሰጡ የተለያዩ መኪናዎች ባለ 60 ወንበር 04 አውቶቢስ ብር 190,968.00 የአንድ አመት
  • የሰርቪስ አገልግሎት የሚሰጥ መኪና ባለ 24 ወንበር 01 ኮስትር ብር 39,326. 56 የአንድ አመት
  • የሰርቪስ አገልግሎት የሚሰጥ መኪና ባለ 14 ወንበር 01 ዶልፊን ብር 38,684.53 የአንድ አመት
  • የሰርቪስ አገልግሎት የሚሰጥ መኪና ባለ 12 ወንበር 01 ሚኒባስ ብር 38,684.53 የአንድ አመት
  • የቴክኒክ ምርመራን ማለፍ የሚችል እንዲሁም ተሽከርካሪው በግዥው (በተከራይ) መስሪያ ቤቱ በተሰየመው ኮሚቴ በባለሙያ ተፈትሾ ማለፍ የሚችል መሆን አለበት።
  • ማህበራት በማህበሩ ስም ተሽከርካሪ ያላቸው ከሆነ ተሽከርካሪያቸውን ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው፡፡
  • በማህበር የታቀፉ የተሽከርካሪ ባለቤት መመረት ያለበት ከሆነ ማህበሩ የሰጠውን ህጋዊ ውክልና በስም ይዞ መቅረብ የሚችል መሆን አለበት፡፡
  • ግለሰቦች በራሳቸው ንብረት ብቻ የሚጫረቱ ይሆናል የራሱ ያልሆነን ንብረት የራስ አስመስሎ መጫረት የተከለከለ ነው።
  • ማህበራትም ይሁኑ ግለሰቦች ተሽከርካሪ ያቀረቡ ባለንብረቶች የተለያዩ ወጭዎችን በራሳቸው የሹፌር የነዳጅ የመሳሰሉትን በራሳቸው የሚሸፍኑ ይሆናል።
  • ማህበራትም ይሁኑ ግለሰቦች ውል ይዘው ያልሰሩበትን ቀን እና ሰአት ካለ ተከራይ መስሪያ ቤቱ አይከፍላቸውም (የመክፈል) ግዴታ የለበትም ።
  • ማህበራትም ይሁኑ ተወዳዳሪ ግለሰቦች በስማቸው የታተመ የዘመኑን ኪው አር ኮድ (QR CODE/ ያለው ደረሰኝ ማቅረብ የሚችል መሆን አለበት።
  • የማህበራት ደረሰኝ ከሆነ ውክልና የተሰጠው ግለሰቡ ማህበሩ የወከለበትን ህጋዊ ውክልና ማቅረብ መቻል አለበት፡፡
  • የዋጋ ማሻሻያን በተመለከተ በተከራይና በአከራይ ወገን አሳማኝ የሆነ ምክንያት ሲገኝ በሁለቱ ስምምነት መሰረት ዋጋ የመቀነስም ይሁን የመጨመር ተፈፃሚነት ይኖረዋል፡፡ ጨረታው ማክሰኞ ግንቦት 25/2018 ዓ.ም እስከ ስኞ ሰኔ 08/2018 ዓ/ም ከቀኑ 10፡00 ሰዓት የጨረታ ሰነድ ተሸጦ የሚያልቅበት ቀን ሲሆን ማክሰኞ ሰኔ 09/2018 ዓ/ም ከረፋዱ 3፡30 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ቀን ከረፋዱ 3፡45 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በሰ/ምዕ/ዕዝ ደ/3 ሆ/ል ትንሹ መሰብሰቢያ አዳራሽ ውስጥ በቅደም ተከተል ይከፈታል።
  • መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  • በጨረታው ላይ ያልተገለፀ ዝርዝር ሁኔታዎችን ከፈለጉ ቅፅ 1 ጥር 1998 ዓም በአገር
    ውስጥ ለሚፈፀሙ እቃዎችና ተዛማች አገልግሎቶች ግዥ የሚውል መደበኛ የጨረታ ሰነድ ከገንዘብና የኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር የመንግስት ግዥ ኤጀንሲ ድረ ገፅ ላይ ወይም ከመስሪያ ቤቱ በሚገዙት መደበኛ የጨረታ ሰነድ ማየት ይችላሉ።
    ስልክ ቂጥር፡-058 321 46 98

በሀገር መከላከያ ሚኒስቴር የሰሜን ምዕራብ ዕዝ ደ/3 ሆ/ል 


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *