የወልቂጤ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ እና ሳተላይት ካምፓስ የግቢውን አጥር ግንባታ ስራ ለማከናወን ተቋራጮችን አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል – test3.diretenders.com

የወልቂጤ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ እና ሳተላይት ካምፓስ የግቢውን አጥር ግንባታ ስራ ለማከናወን ተቋራጮችን አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል


Addis Zemen (Jun 04, 2026)

የጨረታ ማስታወቂያ

የወልቂጤ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ እና ሳተላይት ካምፓስ የግቢውን አጥር ግንባታ ስራ ለማከናወን ተቋራጮችን አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል። ስለዚህ በጨረታው መወዳደር የሚፈልጉ ተጫራቾች በማመልከቻ ሲጠይቁ ማሟላት የሚገባቸው መስፈርቶች

  1. ሕጋዊ ምዝገባ ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችሉ
  2. በደረጃው ቢሲ-5/ዲሲ-5 እና ከዚህ በላይ ፍቃድ ያላቸው
  3. የዘመኑን ንግድ ፍቃድ ያደሱ ሆነው ዋናውንና ኮፒውን ማቅረብ የሚችሉ፣
  4. የዘመኑ የኮንስትራክሽን ሚኒስቴር እና የቫት ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የምትችሉ።
  5. በጨረታ ለመወዳደር የሚፈልጉ ተወዳደሪዎች የሚገዙትን የጨረታ ሰነድ ጠቅሰው በማመልከቻ ሲጠይቁ ተወካዮች ከሆኑ ከድርጅቱ ህጋዊ ውክልና ይዘው መቅረብ አለባቸው።
  6. ተጫራቾች ከላይ የተገለጹት መስፈርት አሟልተው ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ተከታታይ 21ኛው ቀን 600 ሰዓት ድረስ የማይመለስ ብር 500/አምስት መቶ ብር/ በወልቂጤ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጁ ስም በተከፈተ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ገቢ አካውንት ቁጥር 1000026941737 ገቢ በማድረግ ከኮሌጁ ግዥና ንብረት ክፍል በመቅረብ መግዛት ይቻላል።
  7. ተጫራቾች የጨታው ቴክኒካልና ፋይናንሺያል ዶክመንት ሲያቀርቡ
    • ) ለቴክኒካል ዶክመንት አንድ ኦርጅናል እና ሁለት ፎቶ ግራፊክ ኮፒዎች እያንዳንዳቸውን በሰም በታሸገ የጨረታ ማስከበሪያ 300,000 /ሶስት መቶ ሺህ ብር/ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ወይም ሌሎች ተቀባይነት ያላቸው የጨረታ ማስከበሪያዎች ከኦርጅናል ዶክመንት ጋር በማድረግ በማሸግ ሁሉንም በአንድ ትልቅ እናት ፖስታ በማሸግ ቴክኒካል በሚል በመለየት
    • ) ለፋይናንሺያል ዶክመንት አንድ ኦርጅናልና ሁለት ፎቶ ግራፊክ ኮፒ በሰም በማሸግ ሁሉንም በአንድ ትልቅ እናት ፖስታ ውስጥ በማሸግ ፋይናንሺያል በሚል በመለየት እስከ ተከታታይ 21ኛው ቀን 800 ሰዓት ድረስ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።
  8. የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ በኮሌጁ ስም ሆኖ ከቴክኒካል ዶክመንት ኦሪጅናል አብሮ መቅረብ አለበት።
  9. ከተራ ቁጥር 1-8 የተጠቀሱት መስፈርቶች ሙሉ ለሙሉ ያላሟላ ተጫራች ከውድድሩ ውጪ ይሆናል።
  10. የጨረታው ቴክኒካል ዶክመንት 21ኛው ቀን ከቀኑ 830 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
  11. የፋይናንሺያል /የፕሮጀክቱ ግንባታ ዋጋ / ከቴክኒክ ግምገማ ውጤት በኋላ የቴክኒክ ግምገማውን ያለፉት ተጫራቾች ሰነድ ብቻ የጨረታው ኮሚቴው በማስታወቂያ በሚገለፀው ቀን ይከፈታል።
  12. መስሪያ ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ማሳሰቢያ

  1. የጉራጌ ዞን ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን መምሪያ ከሚከታተላቸው ፕሮጀክቶች ውስጥ በአፈፃፀማቸው ምክንያት 3 ዙር ማስጠንቀቂያ ተሰጥቷቸው ውል ያቋረጡ ተቋራጮች መወዳደር አይችሉም።
  2. ጨረታው የሚከፈትበት ቀን በዓል ወይም ቅዳሜና እሁድ የሆነ ከሆነ ወደሚቀጥለው የስራ ቀን ይዘዋወራል።
  3. በጨረታው ሂደት ውስጥ ተሻሽሎ የወጣው የክልሉ የግዢ መመሪያ ተግባራዊ የሚደረግ መሆኑን እንገልጻለን

ስልክ 011-365 8463

የወልቂጤ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ እና ሳተላይት ካምፓስ


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *