Addis Zemen (Jun 28, 2026)
የጨረታ ማስታወቂያ
ግልጽ ጨረታ ቁጥር NCB/OCC‐024/2026
የኦሮሚያ ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን (OCC) በ2019 ዓ.ም በኦሮሚያና በሌሎች ከልሎች ለሚያካሂደው
- ለመንገድ ሥራ ግንባታ፣ ለሕንጻ ሥራ ግንባታ፣ ለመስኖ ሥራ ግንባታ፣ ለውሃ ሥራ እና ለውሃ ቁፋሮ ሥራ ግንባታ እና
- በክሬሸር ማምረቻ አገልግሎት የሚውሉ
- የኮንስትራክሽን ማሽነሪዎችን፣
- ፕላንቶችን፤
- ከባድ መኪኖችን እና አነስተኛ የመስክ መኪኖችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለማከራየት ይፈልጋል::
የሚፈለገው የመሳሪያ ዓይነት ዝርዝር በተጫራቾች በሚሸጠው የጨረታ መመሪያ ሠነድ ውስጥ ተካቷል።
በመሆኑም በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች ማሟላት ያለባቸው መስፈርቶች፡–
- ከሥራው ጋር አግባብነት ያለው እና የታደሰ የንግድ ሥራ ፍቃድ ፣ የሚፈለግባቸውን የመንግስት የግብር ግዴታ ስለመወጣቱ የሚያመለክት ጊዜው ያላለፈበት ማስረጃ (ታክስ ክሊራንስ) ከሚመለከታቸው አካላት ማቅረብ የሚችል፤ የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት)፣የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) እና ከግዥና ንብረት አስወጋጅ ባለስልጣን ድረ–ገጽ ላይ የተመዘገቡ እና የተመዘገቡበትን የአቀራቢዎች ምዝገባ የምስክር ወረቀት ማስረጃዎችን ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ ዘወትር በሥራ ሰዓት የማይመለስ ብር 500(አምስት መቶ ብር) በመከፈል የጨረታ ሰነዱን ከመ/ቤታችን አንደኛ ፎቅ ኮርፖሬት ግዥ ቡድን ክፍል መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በሲፒኦ “CPO” ወይም በቅድመ ሁኔታዎች ላይ ያልተመሠረቱ የባንክ ዋስትና (unconditional & rrevocable Bank Guarantee)ማስያዝ አለባቸው::
- ተጫራቾች የሚያቀርቧቸው የኮንስትራክሽን ማሽነሪዎች፣ ፕነቶች እና ተሽከርካሪዎች ከአካባቢ ጥበቃ ደህንነት(Environment) ጋር የሚጣጣሙ መሆን አለባቸው፡፡ እንዲሁም ሠራተኞችን ሊያጋጥሙ ከሚችሉ የሥራ ላይ አደጋዎች እና ደህንነት (OSH) ጋር በተያያዘ የሚቀርቡ ማሽነሪዎቸ አቋማቸው የተሟላ መሆን አለበት፡፡
- ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን አገልግሎት ዓይነት ድርጅታችን ባዘጋጀው የዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ ላይ በመሙላት በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ለዚሁ በተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን ውስጥ እስከ ሐምሌ 9 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ ብቻ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ ጨረታው በዚሁ ዕለት ማለትም ሐምሌ 9 ቀን 2018 ዓ.ም ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ተወካዮቻቸው በተገኙበት በኮርፖሬሽኑ የስብሰባ አዳራሽ ይከፈታል፡፡
- ኮርፖሬሽኑ የተሻለ ዜዴ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
አድራሻ፡– አቃቂ ቃሊቲ ወረዳ 05 ከአሽከርካሪዎች ማሰልጠኛ ማዕከል ፊት ለፊት OCC ሕንጻ 1ኛ ፎቅ
ኮርፖሬት ግዥ ቡድን ክፍል::
ስልክ ቁጥር +251-0114-39-04-22/0114-39-13-07
የኦሮሚያ ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን(OCC)