የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን የንግድ ድርጅት ቤቶችን ተጫራቾችን አወዳድሮ ማከራየት ይፈልጋል – test3.diretenders.com

የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን የንግድ ድርጅት ቤቶችን ተጫራቾችን አወዳድሮ ማከራየት ይፈልጋል


Addis Zemen (Jul 10, 2026)

የ16ኛ ዙር የንግድ /ድርጅት ቤቶች ጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ መለያ ቁጥር ፌቤ.ኮ/ብ/ግ.ጨ/አገ/12/11/2018

1.የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን በአዲስ አበባ ከተማ በተለያዩ ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች ስር የሚገኙ የንግድ ድርጅት ቤቶችን በጨረታ መለያ ቁጥር ፌ.ቤ.ኮ ብ.ግ.ጨ/አገ/12/11/2018 ተጫራቾችን አወዳድሮ ማከራየት ይፈልጋል፡፡

2. ኮርፖሬሽኑ ለሚያከናውነው የንግድ/ ድርጅት ቤቶች ኪራይ ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሰነዳቸውን እና የመወዳደሪያ የኪራይ ተመን ዋጋ በአንድ ፖስታ ማቅረብ አለባቸው፡፡

3. ጨረታው የሚከናወነው በብሔራዊ ግልጽ ጨረታ ሥነ ሥርዓትና ይህንኑ አስመልክቶ በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን መመሪያ መሰረት ነው፡፡

4 ማንኛውም ፍላጎት ያለው ተጫራች የተሟላ የጨረታ ሰነዱን ሐምሌ 3 ቀን 2018 ዓ.ም እስከ ሐምሌ 14 ቀን 2018 ዓ.ም ቅዳሜን ጨምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት ዘወትር በስራ ሰዓት ከሰኞ እስከ አርብ ከ 2፡00 እስከ 11፡00) ቅዳሜ ከጠዋቱ 2፡00 እስከ 6፡00 ድረስ የማይመለስ ብር 1000 አንድ ሺህ ብር በካሽ በመክፈል የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ በቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች በአካል በመቅረብ መግዛት ይችላሉ፡፡

5. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዶቻቸውን በኮርፖሬሽኑ ዋና መ/ቤት 1ኛ ፎቅ ላይ በሚገኘው የመሰብሰቢያ አዳራሽ ለዚሁ ታሽጎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ጨረታው በመጀመሪያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ሐምሌ 14 ቀን 2018 ዓ.ም ከሰዓት 11፡00 ሰዓት ድረስ እንዲያቀርቡ ሆኖ ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ብር 50000/ ሃምሳ ሺህ ብር/ በሁኔታዎች ላይ ያልተመሰረተ ሲ.ፒ.ኦ በፌደራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ስም ከጨረታ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡

ከጨረታው መክፈቻ ዕለትና ሰዓት ዘግይቶ የቀረበ የጨረታ ስነድ ውድቅ ይደረጋል፡፡ ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በጨረታ ሰነዱ ክፍል 1 ላይ በተገለፀበት ቀንና ሰዓት ይከፈታል፡፡ የጨረታ ሰነድ ሽያጭ በኮርፖሬሽኑ ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች የሚከናወን ይሆናል። 

6.ተጫራቾች የንግድ ቤቶቹን በአካል ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ማብቂያው ቀን ድረስ . በስራ ቀናት ከጠዋቱ 3፡00 እስከ ቀኑ 11፡00 ሰዓት ቤቶቹ በሚገኙበት አድራሻ ድረስ በመቅረብና ለዚሁ ስራ በሚመደቡ ባለሙያዎች እና በሚወጣው ፕሮግራም መሰረት ቤቶቹን መመልከት ይችላሉ።

7.ኮርፖሬሽኑ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለተጨማሪ መረጃ፡-
በስልክ ቁጥር 09-10-48-59-48 ወይም 0922-98-76-33 ወይም 0922-49-18-85 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፡፡
ዌብሳይት/ website www.fhc.gov.et 
የፖ.ሣ.ቁ. PO Box 299
ፋክስ ቁጥር፡ 011-5-54-60-45/ 011-5-52-46-46
የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *