የቤት የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ – test3.diretenders.com

የቤት የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ


Addis Zemen (Jul 10, 2026)

የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ

በፍርድ ባለመብት ዳይናሚክ ማይክሮፋይናንስ ተቋም ኢማ እና በፍርድ ባለእዳ አቶ ሽመልስ ከበደ መካከል ስላለው አፈፃፀም የፌደራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በመ/ 96068 በቀን 11/04/2016. በኮ//.99200 በቀን 14/05/2018. በዋለው ችሎት በሰጠው ትእዛዝ በኮ///ከተማ ወረዳ 6 የቤት ቁጥር 817 የሆነ ቤት የይዞታ ልዩ መለያ ቁጥር AA000090607345 የይዞታ ስፋት 150. የሆነ ይዞታ አቶ ሽመልስ ከበደ ስም ተመዝግቦ የሚገኝ የቤቱ የሽያጭ ዋጋ መነሻ ግምት ብር 6,545,700( ስድስት ሚሊዮን አምስት መቶ አርባ አምስት ሺህ ሰባት መቶ ብር)ሆኖ የትራዛክሽን ታክስ ገዥ የሚከፍል መሆኑ ታውቆ ነሐሴ 7 ቀን 2018/ በሐራጅ ይሸጣል፡፡ የተጫራቾች ምዝገባ 400 ሰዓት ተጀምሮ የቀረቡ ተጫራቾች ተመዝግበው እንደተጠናቀቀ ወዲያዉኑ ጨረታው የሚካሄድ ይሆናል፡፡

የሐራጁ ሽያጭ የሚካሄደው በፌደራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም /ቤት የጨረታ አዳራሽ ውስጥ ሲሆን፣ ንብረቱን ተጫርተው ለመግዛት የሚፈልጉ ተጫራቾች ከጨረታው ቀደም ብሎ ባሉት አራት የሥራ ቀናቶች ውስጥ ባለመብቱ ለማስጎብኘት በሚመርጧቸው ሶስት የስራ ቀናት በፌ//ቤቶች ፍርድ አፈፃፀም /ቤት ሐራጅ ክፍል ድረስ ከጠዋቱ 330 ብቻ በመገኘትና ባለመብቱ በሚያቀርበው ትራንስፓርት ንብረቱን ባለበት ቦታ ድረስ በመውሰድ ለመጐብኘት የሚችሉ ሲሆን፤እያንዳንዱ ተጫራች በሚጫረትበት ወቅት የንብረቱን መነሻ ግምት 1/4 ኛውን በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተረጋገጠ CPO ማስያዝ ይኖርበታል፡፡ 1/4 አስበልጦም ሆነ አሳንሶ የሚመጣ ተጫራች በጨረታው አይካፈልም፡፡ በጨረታው አሸናፊ የሆነው ግለሰብ አሸናፊ የሆነበትን ገንዘብ በአጠቃላይ ጨረታውን ከአሸነፈበት ቀን ጀምሮ በፍ/አፈ//ቤት ስም CPO አሰርቶ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ብቻ ሙሉ ገንዘቡን 15 ቀናት ውስጥ ገቢ ማድረግ አለበት፡፡ በጨረታ አሸናፊ የሆነ በጨረታ ያሸነፈበትን ገንዘብ ገቢ ሳይደረግ ቀርቶ በቀጣይ ጨረታ ተደርጎ ጨረታው ከበፊቱ ጨረታው ቀንሶ ከተሸጠ ገዥው በልዩነት ተጠያቂ እንደሚሆን የፍ/አፈ//ቤት ንብረቱን በህጋዊ መንገድ በሐራጅ ስለመሸጡ ለሚመለከተው አካል ማስረጃ ከመጻፍ ባለፈ ስም የማዛወር ግዴታ የሌለበት መሆኑን እንገልፃለን፡፡

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር +251 112 730 852 በመደወል መጠየቅ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡

የፌደራል /ቤቶች የፍርድ አፈፃፀም /ቤት


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *