Addis Lessan (Jul 11, 2026)
የሕንፃ ኪራይ ጨረታ ማስታወቂያ
ኬኬ ኃላ.የተ.የግል ኩባንያ ካስገነባቸው ዘመናዊ ሕንፃዎች መካከል የአፍሪካ ገበያ ማዕከል በሆነው ከመርካቶ በቅርብ ርቀት በሚገኘው በተለምዶ ጨው በረንዳ ተብሎ በሚጠራው እና በአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ወረዳ 6 ውስጥ ባለ 5 ወለል ዘመናዊ ህንፃ አጠናቆ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ሙሉ ሕንፃውን ለአንድ ተጫራች ማከራየት ይፈልጋል።
ሕንፃው የውሃ፣ የኤሌትሪክ ፣ የኢንተርኔት ዝርጋታ የተሟላለት ከመሆኑም በላይ ለአካል ጉዳተኞች እና ለአቅመ ደካሞች ዘመናዊ ሊፍት የተገጠመለት ሲሆን የመኪና ማቆሚያ አያሳስቦት ከ50 በላይ መኪኖችን ማስተናገድ የሚችል የመኪና ፓርኪንግ ያካተተ ነው።
ለሚከራዩት ሕንፃ ከስርቆት ስጋት ነፃ እንዲሆኑ ኬኬ በራሱ ወጪ አስተማማኝ የ24 ሰዓት ጥበቃ እና ዘመናዊ ካሜራ አስገጥሟል። እናስ ምን ይጠብቃሉ? ይፍጠኑ ይህን እንከን የለሽ ዘመናዊ ሕንፃ ሳያመነቱ ይከራዩ፡፡ ሕንፃው ለባንክ አገልግሎት፣ ለኢንሹራንስ፣ ለገንዘብና ብድር ተቋማት እንዲሁም ለትምህርትና ለጤና አገልግሎት ምቹ በመሆኑ ፍላጎት ያላችሁ በጨረታው እንድትሳተፉ ተጋብዛችኋል።
የጨረታ ሰነዱን ለማግኘት ሕንፃው በተገነባበት ጨው በረንዳ በሚገኘው ቢሮአችን በመምጣት ለጨረታ ሰነዱ መግዣ የማይመለስ ብር አንድ ሺህ (1,000) ብር በመክፈል ሰነዱን ማግኘት ትችላላችሁ
ጨረታው ይሕ ማስታወቂያ ከወጣበት ወይም ከተነገረበት ከሰኔ 26 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ ለአስር ተከታታይ የስራ ቀናቶች ክፍት ሆኖ የሚቆይ ሲሆን ጨረታው ሐምሌ 9 ቀን 2018 ዓ.ም. ምሽት 11 ሰዓት ላይ ተዘግቶ በበነጋታው ሐምሌ 10 ቀን 2018 ዓ.ም. ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ይከፈታል።
ኬኬ ኃላ/የተ/የግል ኩባንያ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ተጨማሪ ማብራሪያ በጨረታ ሰነዱ ላይ ያገኛሉ።
ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 09 39-42 23 24 / 09 11- 24 83 33 በስራ ሰዓት ብቻ ይደውሉ።
ኬኬ ኃላ/የተ/የግል ኩባንያ