በአብክመ በኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር ዞን የጅ/ጥ/ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት የሚውሉ የመኪና ጎማ፣ የተሽከርካሪ መለዋወጫ ዕቃ/ስፔር/ እና ጌጣጌጥ በመደበኛ በጀት በብሄራዊ ግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል – test3.diretenders.com

በአብክመ በኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር ዞን የጅ/ጥ/ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት የሚውሉ የመኪና ጎማ፣ የተሽከርካሪ መለዋወጫ ዕቃ/ስፔር/ እና ጌጣጌጥ በመደበኛ በጀት በብሄራዊ ግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል


Addis Zemen (Jul 11, 2026)

የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 1/2019

በአብክመ በኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር ዞን የጅ/ጥ/ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ሰንበቴ ከተማ ከአዲስ አበባ በደሴ ከተማ መስመር በ265 ኪ/ሜ ላይ የምትገኝ ሲሆን፤በ2019 በጀት አመት በወረዳው አስተዳደር ስር ላሉ ሴክተር መስሪያ ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ የመኪና ጎማ፣ የተሽከርካሪ መለዋወጫ ዕቃ/ስፔር/ እና ጌጣጌጥ በመደበኛ በጀት በብሄራዊ ግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

በዚሁ መሠረት

  1. በጨረታው ለመወዳደር የምትፈልጉ በዘርፉ የተሠማሩ የዘመኑን ግብር የከፈሉበት ንግድ ፈቃድ ፣ የምስክር ወረቀትና የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር / TIN NO/ እና የVAT ተመዝጋቢ ደረሰኝ ያላቸው መሆን አለበት።
  2. በጨረታው ለመሣተፍ የሚፈልጉ ለተዘጋጀው የጨረታ ሠነድ የማይመለስ ብር 200/ ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል የተዘጋጀውን ሰነድ ከጅ/ጥ/ወ/ገ/ጽ/ቤት ገንዘብ ያዥ ቢሮ ቁጥር 3 ከ 4/11/2018 እስከ 18/i1/2018 መግዛት ይችላሉ። በጨረታው ሰነድ ላይ ዝርዝር ማብራሪያዎችን ያገኛሉ።
  3. ተጫራቾች የሚጫረቱበትን የጨረታ ሰነድ ዋጋ በመሙላት በታሸገ ፖስታ የአቅራቢው የባለቤት ስምና አድራሻ የሚገልፅ ኦርጅናልና ኮፒውን በመለየት እስከ 19/11/2018 ዓ.ም ጠዋት 4፡00 ሰዓት ድረስ ጅ/ጥ/ወ/ገ/ፅ/ቤት ቢ.ቁ 10 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው። በዚሁ እለት 4፡05 ሰዓት ይታሸጋል።
  4. ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በዚሁ እለት 19/11/2018 ዓ.ም 4፡30 ላይ የጨረታ ሣጥኑ ይከፈታል።
  5. ጨረታውን በየእያንዳንዱ ሎት አይነት የምናወዳድር መሆኑን እንገልፃለን።
  6.  ተጫራቾች ለሚሞሉት ጠቅላላ ዋጋ የጨረታ ማስከበሪያ ለመኪና ጎማ 50,000 /ሃምሳ ሺህ ብር/ ለተሽከርካሪ መለዋወጫ ዕቃ/ስፔር/ እና ጌጣጌጥ 70,000 /ሰባ ሺህ ብር /በCPO ወይም በጥሬ ገንዘብ በማስያዝ ቢሮ ቁጥር 3 ደረሰኝ በመቁረጥ ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል፡
  7.  መሥሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሠረዝ መብት አለው፡፡

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 0331180062/37 ደውለው መጠየቅ ይቻላሉ።

በአብክመ በኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር ዞን የጅ/ጥ/ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *