Addis Zemen (Jul 19, 2026)
የመጀመሪያ ዙር ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
001/2019 ዓ.ም
በቂርቆስ ክ/ከተማ የፈለገ ዮርዳኖስ ቅድመ አንደኛ አንደኛ እና መ/ደ/ት/ቤት ለ2019 ዓ.ም በጀት ዓመት አገልግሎት የሚውሉ ከዚህ በታች የተዘረዘሩ ልዩልዩ እቃዎችን አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
- የደንብ ልብስ
- የህትመት ስራዎች
- አላቂ የቢሮ እቃዎች
- አላቂ የትምህርት እቃዎች
- የጽዳት እቃዎች
- የህንጻ ቀለም አድሳትና ጥገና ስራዎች
- ፕላንት ና ማሽነሪ እድሳት
- ቋሚ እቃዎች
- አላቂ የህክምና እቃዎች
1. በዘርፉ የተሰማሩበት ንግድ ፈቃድ ያላቸው::
2. የዘመኑ ግብር አጠናቀው የከፈሉ ለዚህም ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።
3. የተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት መዝገብ ያላቸውና ማቅረብ የሚችሉ።
4. ጨረታ ሰነዱን ለእያንዳንዱ 300.00 (ሦስት መቶ ብር) የማይመለስ ብር በመክፈል ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት እስከ 11፡00 ሰዓት ድረስ የፈለገ ዮርዳኖስ ቅድመ አንደኛ አንደኛ እና መ/ደ/ት/ቤት ቢሮ.ቁ 30 በግንባር በመቅረብ መግዛት ይቻላል።
5. በአቅራቢዎች ዝርዝር የተመዘገቡና ለዚህም ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።
6. ለጨረታ ማስከበሪያ የሚውል በባንክ በተረጋገጠ ቼክ (CPO) 8000.00 /ስምንት ሺህ ብር/ ማቅረብ የሚችሉ።
7. በአነስተኛ እና ጥቃቅን የተደራጁ የውል ማስከበሪያ ደብዳቤ እና ጨረታ የሚሳተፉበት ከአደረጃጀት ወረዳ 2019 ዓ.ም ደብዳቤ ማምጣት አለባቸው።
8. የጨረታ ሰነዱ ኮፒና ኦርጅናል በመለየት በታሸገ ኤንቨሎፕ በተለያየ ፖስታ አሽገው ሲመጡ (CPO) ደግሞ ጨረታው ኮፒ ባለበት ፖስታ ውስጥ በማስገባት አሽገው ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
9. የጨረታ ሳጥን ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው ቀን በት/ቤቱ ቅጥር ግቢ ፋይናንስ ከፍል ይከፈታል። በ11ኛው ቀን በዓል ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን 4፡00 ሰዓት ይከፈታል፡፡
10. የጨረታ አሸናፊ ያሸነፈበትን እቃ የጠቅላላ ዋጋ 10% ዋስትና በባንክ በተረጋገጠ ቼክ (CPO) ማስያዝ አለበት።
11. ት/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
12. የእድሳትና ጥገና ተወዳዳሪዎች ደረጃ 7 (ሰባት) መሆን አለባቸው።
አድራሻ፡- ቂርቆስ ክ/ከተማ ወረዳ 11 ከቂርቆስ ቤተክርስትያን ዝቅ ብሎ
ስልክ ቁጥር፡- 0114701490/0114161936
የፈለገ ዮርዳኖስ ቅድመ አንደኛ አንደኛ እና መ/ደ/ት/ቤት