Reporter (Jul 19, 2026)
ብሔራዊ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የአዲስ አበባ ቀላል ባቡር ትራንስፖርት አገልግሎት ድርጅት በግዥ መለያ ቁጥር፦ 001/2019 ለባቡር እና ለባቡር መሰረተ-ልማት ጥገና ሰራተኞች ለደህንነት መጠበቂያ የሚሆን ደንብ ልብስ እና ለደንበኞች አገልግሎት የሚሆን ሙሉ ልብስ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል።
|
ተ/ቁ |
የግዥ ዓይነት |
የጨረታ ማስከበሪያ |
|
1 |
ለደህንነት መጠበቂያና ለስራ አገልግሎት የሚዉሉ ደንብ ልብስ ዕቃ/አገልግሎት ግዥ |
80,000 (ሰማኒያ ሺህ ብር) |
|
2 |
የተሸከርካሪ ጎማና ጌጣጌጥ |
50,000 (ሃምሳ ሺህ ብር) |
በጨረታው መሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች ማሟላት ያለባቸው
1.በዘርፉ ህጋዊ የታደሰ የንግድ ፈቃድ እና የንግድ ምዝገባ የምስክር ወረቀት ያላቸው፣
2. የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣
3. የተጨማሪ እሴት ታክስ/የቫት/ ተመዝጋቢ መሆናቸውን ማቅረብ የሚችሉ፣
4. የአቅራቢነት ሰርተፊኬት ያላቸው እና የግብር መክፈያ መለያ ቁጥር/ Tin No /ያላቸው
5. ተጫራቾች በባንክ የተረጋገጠ በመ/ቤታችን ስም የተዘጋጀ CPO ወይም የተረጋገጠ የባንክ ጋራንቲ በተቀመጠው መሰረት ማስያዝ አለባቸው። ነገር ግን CPO ወይም የባንክ ጋራቲ በተቀመጠዉ መጠን መሰረት ያላስያዘ ቢኖር ከጨረታ ውጪ ይሆናል፣
6. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ለመግዛት የሚችሉት በሪፖርተር ጋዜጣ ከሚወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ይሆናል።
7. ማንኛውም ተጫራች ከተራ ቁጥር 1 እስከ 6 የተጠቀሱትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ህጋዊ ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በሪፖርተር ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ተጫራቾች ሰነዱን የማይመለስ ብር 300(ሶስት መቶ ብር) በድርጅቱ ስም በተከፈተ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሂሳብ ቁጥር 1000493811049 በመክፍል ያስገቡበትን ዲፖዚት ስሊፕ ይዘዉ በመምጣት ዘውትር በስራ ሰዓት ቃሊቲ ማሰልጠኛ አካባቢ በሚገኘው የአዲስ አበባ ቀላል ባቡር ትራንስፖርት አገልግሎት ድርጅት መግዛት ይችላሉ።
8. አሸናፊው ድርጅት ጥራቱን የጠበቀ ዕቃ /አገልግሎት/ ካላቀረበ በራሱ ወጪ የመለወጥ ግዴታ አለበት፣
9. መ/ቤቱ ካቀረበው ሰነድ ውጪ በሌላ ሰነድ በአማራጭነት ማቅረብ አይቻልም፣ ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ቴክኒካል ኦርጅናልና ቴክኒካል ኮፒ እንዲሁም ፋይናንሽያል ኦርጅናልና ፋይናንሽያል ኮፒ ለየብቻ በፖስታ አሽገው የድርጅታቸውን ማህተምና ፊርማ በማድረግ ለጨረታ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፣
10. ተጫራቾች መ/ቤቱ ባዘጋጀው የጨረታ ሰነድ ዋጋ ላይ ስርዝ ድልዝ ሳይኖርበት በትክክል መሙላት አለባቸው፣
11. ጥቃቅንና አንስተኛ ተጫራቾች ለምትጫረቱባቸዉ ዕቃዎች የጨረታ ሰነዱን በነጻ ለመዉሰድ
ሀ. ከደራጃችሁ መ/ቤት ደብዳቤ ማምጣት አለበት
ለ. ሰነዱን በነጻ ለመዉሰድ በመመሪያ መሰረት ለምትወደደሩበት ዕቃ/አገልግሎት/ አምራች መሆን አለባቸሁ
12. ጨረታው ከተከፈተ በኋላ አሸናፊው ድርጅት ያሸነፈበትን ዕቃ ወይም አገልግሎት ዝርዝር ላይ የጠቅላላ ዋጋ 10% የውል ማስከበሪያ ማስያዝ ይኖርበታል። እንዲሁም አሸናፋው የሆነው ድርጅት አሸናፊነቱ እንደተገለፀለት በመ/ቤታችን ቀርቦ ውል መዋዋል አለበት ይህ ባይሆን ግን ለዋስትና ያስያዘው የጨረታ ማስከበሪያ ገንዘብ ለመንግሰት ገቢ ይሆናል።
13. ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዳቸውን በአዲስ አበባ ቀላል ባቡር ትራንስፖርት አገልግሎት ድርጅት በሚገኝው የጨረታ ሳጥን ውስጥ እስከ ሐምሌ 27/2018 ዓም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት በፊት በስራ ሰዓት ማስገባት ይኖርባቸዋል። ከተጠቀሰው ሰዓት ዘግይቶ የመጣ የጨረታ ሰነድ ተቀባይነት አይኖረውም።
14. ተጨራቾች ለሚጫረቱባቸው ዕቀዎች ናሙና ማቅረብ እና ናሙና ማቅረብ ለማይቻለዉ ዕቀዎች/ አገልግሎቶች ዝርዝር መግለጫ ማቅረብ አለባቸው፣
15. ጨረታው የሚከፈተው ሐምሌ 27/2018 ዓም ጠዋት 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በአዲስ አበባ ቀላል ባቡር ትራንስፖርት አገልግሎት ድርጅት በሚገኘው መሰብሰቢያ አዳራሽ ይሆናል።
16. መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ ጨረታውን የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።
በአዲስ አበባ ቀላል ባቡር ትራንስፖርት አገልግሎት ድርጅት
ስልክ ቁጥር 011 470 8116