Reporter (Jul 19, 2026)
ለመጀመሪያ ጊዜ የወጣ ሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ
አቢሲንያ ባንክ አ.ማ ለሰጠው ብድር በመያዣ የያዛቸውንና በሠንጠረዡ የተመለከቱትን ቋሚ ንብረቶች በአዋጅ ቁጥር 97/90 (እንደተሻሻለው) መሠረት ባሉበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል። በመሆኑም ተጫራቾች ለጨረታ ከመቅረባቸው በፊት የሚከተሉትን ደንቦች መገንዘብ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ንብረት የጨረታ መነሻ ዋጋውን 1/4 (አንድ አራተኛ) በባንክ በተረጋገጠ ቼክ ወይም ሲ.ፒ.ኦ በአቢሲንያ ባንክ ስም በማሰራት ለጨረታ ማስከበሪያ በማስያዝ በጨረታው መሳተፍ ይችላሉ።
- የጨረታው አሸናፊ አሸናፊነቱ ከባንኩ በደብዳቤ ከተገለጸለት ቀን ጀምሮ ያሸነፈበትን ጠቅላላ ዋጋ በ15 (አስራ አምስት) ቀናት ውስጥ አጠቃሎ ከፍሎ በጨረታ ያሸነፈበትን ንብረት መረከብ ይኖርበታል። በእነዚህ ቀናት ውስጥ የሚፈለግትን ክፍያ ከፍሎ ንብረቱን ካልተረከበ ጨረታው ተሰርዞ ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዘው ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ይሆናል። በጨረታው ለተሸነፉት ተጫራቾች ያስያዙት ሲ.ፒ.ኦ ወዲያው ይመለስላቸዋል።
- ተበዳሪ/መያዣ ሰጪ በሐራጁ ቀንና ሰዓት በቦታው መገኘት ይችላሉ። ነገር ግን ባይገኙ ሐራጁ በሌሉበት ይካሄዳል።
- የጨረታው አሸናፊ ከሚገዛው ንብረት ጋር የተያያዙ ማናቸውም ለመንግስት የሚከፈሉ ክፍያዎችን፣ ግብር፣ በሽያጩ ዋጋ ላይ የሚታሰብ የተጨማሪ እሴት ታክስ 15% እንዲሁም ከስም ዝውውር ጋር የሚገናኙ ማናቸውም ወጪዎችን ይከፍላል።
- ንብረቶቹን በሥራ ሰዓት ፕሮግራም አስይዞ መጎብኘት ይቻላል።
- በባንኩ የብድር ፖሊሲ እና መመሪያ መሰረት መስፈርቱን ለሚያሟላ የጨረታው ከፍተኛ ዋጋ አቅራቢ /አሸናፊ/ ባንኩ ከፊል ብድር ሊያመቻች ይችላል።
- ጨረታው የሚካሄደው አዲስ አበባ ቂርቆስ ክ/ከተማ ወረዳ 7 ለገሀር በሚገኘው የአቢሲንያ ባንክ አ.ማ ዋና መስሪያ ቤት 4ኛ ፎቅ የፎርክሎዠርና ዴት ሊቲጌሽን ለጨረታ ባዘጋጀው ክፍል ውስጥ ነው።
- ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 011 515 0711 ወይም 011 515 1153 በመደወል መጠየቅ ይቻላል።
- ባንኩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
|
ተ.ቁ |
የተበዳሪዉ ስም |
የመያዣ ሰጪዉ ስም |
የንብረቱ አይነትና አገልግሎት |
የቦታው አጠቃላይ ስፋት በካሬ ሜትር |
የካርታ ቁጥር
|
ንብረቱ የሚገኝበት አድራሻ
|
የጨረታ መነሻ ዋጋ በብር
|
ጨረታዉ የሚካሄድበት ቀን |
የምዝገባ ሰዓት
|
የጨረታ ሰዓት
|
|
1 |
ቦሉ የምግብ ኮምፕሌክስ ኃ/የተ/የግ/ማህበር |
ተበዳሪው |
የፋብሪካ ህንጻ |
5,950 ካ.ሜ
|
293/99/A |
ኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት አዳማ ከተማ ቦኩ አዳማ ሸነን ክ/ከተማ |
76,248,147.93
|
ነሀሴ 13 ቀን 2018 ዓ.ም
|
4:30-5:30
|
5:30-6:00
|
|
2 |
ቦሉ የምግብ ኮምፕሌክስ ኃ/የተ/የግ/ማህበር |
ተበዳሪው |
ለቅይጥ አገልግሎት የሚውል ህንጻ |
500 ካ.ሜ
|
293/99/B
|
ኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት አዳማ ከተማ ቦኩ ሸነን ክ/ከተማ |
37,686,334.67
|
ነሀሴ 13 ቀን 2018 ዓ.ም |
8:30-9:30
|
9:30-10:00
|