Addis Zemen (Aug 28, 2026)
የጨረታ ማስታወቂያ 01/2018
የኮልፌ ቀራንዮ ክ/ከተማ የየማነብርሃን ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት
- ሎት 1. የደንብ ልብስ………………………10,000.00
- ሎት 2. አላቂ የቢሮ ዕቃዎች………………..2,500.00
- ሎት 3. ህትመት……………….1,000.00
- ሎት 4 አላቂ የትምህርት ዕቃዎች………………………15,000.00
- ሎት 5. አላቂ የፅዳት ዕቃዎች………………………10,000.00
- ሎት 6. ኤሌክትሮኒክስ እድሳትና ጥገና………………………1,500.00
- ሎት 7. የኮምፒውተርና ተዛማች ዕቃዎች………………………5,000.00
- ሎት 8. ቋሚ ዕቃዎች……………………….4,000.00
- ሎት 9. የቀይ መስቀል ዕቃ ………………………1,000.00
1. በዘርፉ አግባብነት ያለው ህጋዊ የታደሰ ፈቃድ እና የዘመኑን ግብር የከፈለ።
2. በመንግስት ግዥ ኤጀንሲ በዕቃ አቅራቢነት የተመዘገበበትን ኮፒ ማቅረብ የሚችል።
3. የተጨማሪ እሴት ታከስ የምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል።
4. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት የማይመለስ 300 (ሶስት መቶ ብር) በመክፈል የጨረታውን ዝርዝር ሰነድ ቢሮ ቁጥር 4 ከግዥ ክፍል መውሰድ ይችላሉ።
5. ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዋጋ በገዙት ሰነድ ላይ ባለው የዋጋ ማቅረቢያ ቦታ በመሙላት በታሸገ ፖስታ ኦርጅናልና ኮፒ ማስገባት አለባቸው።
6. ተጫራቾች ከላይ በየሎቱ የተጠቀሱትን የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ብቻ ለእያንዳንዱ ሎት ማስያዝ አለባቸው።
7. ለሁሉም ዕቃዎች ናሙና ማቅረብ ግዴታ ሲሆን ናሙና ለማቅረብ የሚያስቸግሩትን በፎቶ እና የዕቃው መግለጫ (specification) አብሮ በመግለጽ ጨረታው ከመዘጋቱ ቀደም ብለው ማቅረብ ይኖርባቸዋል። ያስገቡት ናሙናዎች በጨረታው ለተሸነፉ ተጫራቾች ተመላሽ ይሆናል።
8. ጥቃቅንና አነስተኛ ዕቃ አቅራቢዎች ከሚመለከተው አካል በትምህርት ቤቱ ስም የተጻፈ ደብዳቤ እና የብር መጠን ተጠቅሶ የተፃፈ አያይዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
9. አሽናፊው ያሸነፈበትን ዕቃ የትምህርት ቤቱ የዕቃ መረከቢያ እስቶር ድረስ በራሱ ትራንስፖርት በማቅረብ ማስረከብ ይኖርበታል።
10. ጨረታው ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በአስረኛው(10ኛ) ቀን በአስራ አንድ ሰዓት (11፡00) ታሽጎ በአስራ አንደኛው (11ኛ) ቀን በአራት ሰዓት (4፡00) ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
11. አሸናፊው ውል ገብቶ ዕቃዎቹን ከማስገባቱ በፊት የውል ማስከበሪያ 10 በመቶ ማስያዝ አለበት ጥቃቅንና አነስተኛ ዕቃ አቅራቢዎች ከሚመለከተው አካል የዋስትና ደብዳቤ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
12. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ፡– ኮልፌ ቀራንዮ ክ/ከተማ ወረዳ 06 የማነብርሃን 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ወይራ ሰፈር አደባባይ ፊትለፊት ገባ ብሎ
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር፡– 011 369 6814 / 011 349 0998
በኮልፌ ቀራንዮ ክ/ከተማ የየማነብርሃን ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት