Be'kur (Sep 07, 2026)
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
በማዕከላዊ ጎንደር በታች አርማጭሆ ወረዳ የሳንጃ የመጀመሪያ ደርጃ ሆስፒታል ለ2019 ዓ.ም ከመስከረም 01/2019 እስከ ሰኔ 30/ 2019 ዓ.ም ለመ/ቤቱ አገልግሎት የሚውል ለሰራተኞች ሰርቪስ የሚሰጥ መኪና በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ በአቃቢ ህግ ውል ወስዶ ማሰራት ይፈልጋል።
ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ይችላሉ።
- በዘመኑ ታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸው።
- የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው።
- መኪናዉ የሚፈለግባቸዉን ወጭዎች ከናፍጣ ጀምሮ ሙሉ በሙሉ ባለንብረቱ የሚሸፍን ይሆናል።
- የመኪናዉ የምርት ዘመን ከ2017 ጀምሮ የመጫን አቅሙ 45 ወንበር እና ከዚያ በላይ መጫን የሚችል ማንኛዉም የህዝብ ማጓጓዣ፤
- የመኪና ሊብሬ ያላቸው ሆኖ ሆስፒታሉ ዝቅተኛ ዋጋ የሞላ ተወዳዳሪ አሸናፊዉን የሚለይ ይሆናል።
- ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር 1-6 የተጠቀሱትንና የሚመስከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከማጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር እያይዘው ማቅረብ አለባቸው።
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል የሳንጃ የመጀመሪያ ደርጃ ሆስፒታል ግ/ፋን/አስ/ቢሮ መውሰድ ይችላሉ። ጨረታው ከወጣበት ከጳጉሜ 02/2018 ዓ/ም እስከ መስከረም 11/2019 ዓ/ም ለተከታታይ 15 ቀናት በጋዜጣ ይቆያል።
- የጨረታ ሳጥን የሚታሸገው መስከረም 12/2019 ከረፋዱ 3፡30 ይሆናል።
- ጨረታው የሚከፈተው ሁሉም ተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸው ባሉበት በሳንጃ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል አዳራሽ መስከረም 12/2019 ዓ/ም ከረፋዱ 4፡00 ይሆናል። ነገር ግን ተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸው ባይኖርም የሚከፈት ይሆናል።
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ለሚወዳደሩበት ብር አንድ በመቶ የእቃውን ጠቅላላ ዋጋ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንከ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው።
- ማንኛውም ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ኦርጅናልና ኮፒውን በተለያየ ለየብቻ በመለየት በጥንቃቄ በታሸገ ፓስታ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ሰዓት ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- ከጨረታ ሰነዱ ላይ ከተቀመጠው የዋጋ መውያ ፎርም በስተቀር በማሳሰቢያ የሚሞሉ የዋጋና ሌሎች አላስፈላጊ መረጃዎችን የማንቀበል መሆኑን እንገልፃለን።
- አሸናፊ ድርጅት የውል ማስከበሪያ የጠቅላላ ዋጋውን 10 በመቶ ማስያዝ የሚችል።
- ሆስፒታሉ የሚገኘዉ ሰርቪስ ከሚጀምርበት ቦታ ጀምር 3 ኪሎ ሜትር ርቀት አለዉ በመሆኑም ጠዋቱ 1፡50 ወደ ስራ ለምሳ 6፡30 ከምሳ መልስ 8፡20 እንዲሁም ማታ ወደ ቤት 11፡30 በድምሩ አራት ዙር እና አሁድና ቅዳሜ 2፡30 ወደ ቢሮ 11፡30 ወደ ቤት በድምሩ 2 ዙር ማመላለስ አለበት፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር፡- 09 18 19 85 88 /09 34 62 32 67 ደውለው መረጃ መጠየቅ ይችላሉ።
የሳንጃ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል