በማዕከላዊ ጎንደር ዞን በታች አርማጭሆ ወረዳ የሳንጃ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል በ2019 ዓ.ም ለመ/ቤቱ አገልግሎት የሚውል 1hz-k79 አንቡላንስ መኪና መለዋወጫ እቃ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል – test3.diretenders.com

በማዕከላዊ ጎንደር ዞን በታች አርማጭሆ ወረዳ የሳንጃ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል በ2019 ዓ.ም ለመ/ቤቱ አገልግሎት የሚውል 1hz-k79 አንቡላንስ መኪና መለዋወጫ እቃ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል


Be'kur (Sep 07, 2026)

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

በማዕከላዊ ጎንደር ዞን በታች አርማጭሆ ወረዳ የሳንጃ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል በ2019 ዓ.ም ለመ/ቤቱ አገልግሎት የሚውል 1hz-k79 አንቡላንስ መኪና መለዋወጫ እቃ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ይችላሉ።

  1. በዘመኑ ታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸው።
  2. የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።
  3. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው።
  4. አሽናፊዉ ተለይቶ ዉል ከወሰደበት ጊዜ ጀምሮ እስከ ሰኔ 30/2019 ዓ.ም ተቋሙ ሲፈልግ ለማቅረብ ዉል መዉሰድ የሚችል።
  5. የግዥው መጠን ከብር 100,000 (አንድ መቶ ሽህ ብር) እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ።
  6. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር 1-5 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከማጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።
  7. የሚገዙ የመለዋወጫ እቃ አይነትና ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ።
  8. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል የሳንጃ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ግ/ፋ/ን/አስ/ቢሮ መውሰድ ይችላሉ። ጨረታው ከወጣበት ከጳጉሜ 02/2018 ዓ/ም እስከ መስከረም 11/2019 ዓ/ም ለተከታታይ 15 ቀናት ይቆያል።
  9. የጨረታው ሳጥን የሚታሸገው መስከረም 12/2019 ከረፋዱ 3፡30 ይሆናል።
  10. ጨረታው የሚከፈተው ሁሉም ተጫራቾች ወይም ወኪሎች በተገኙበት በሳንጃ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል አዳራሽ መስከረም 12/2019 ዓ/ም ከረፋዱ 4፡00 ይሆናል። ነገር ግን ተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸዉ ባይኖርም የሚከፈት ይሆናል፡፡
  11. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ለሚወዳደሩበት አንድ በመቶ የሞሉትን ጠቅላላ ዋጋ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው።
  12. ማንኛውም ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በሁለት ፖስታ ኦርጀናልና ኮፒውን በተለያየ ለየብቻ በመለየት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
  13. አሸናፊው ድርጀት በዓ/ህግ ጽ/ቤት ቀርቦ ውል መውሰድ የሚችል።
  14. ከጨረታ ሰነዱ ላይ ከተቀመጠው የዋጋ መሙያ ፎርም በስተቀር በማሳሰቢያ የሚሞሉ የዋጋና ሌሎች አላስፈላጊ መረጃዎችን የማንቀበል መሆኑን እንገልፃለን።
  15. አሸናፊ ድርጅት የውል ማስከበሪያ የጠቅላላ ዋጋውን 10 በመቶ ማስያዝ የሚችል።
  16. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  17. ጨረታው የሚከፈትበት ቀን ብሄራዊ በዓል ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይሆናል።
  18. የሚያቀርቡት የመኪና መለዋወጫ እቃ ሁሉም እቃዎች ኦርጀናል መሆን አለባቸው። ኦርጂናል ለመሆኑ በባለሙያ (በሹፌር) እየተረጋገጠ ወደ ንብረት ክፍል ገቢ ይደረጋል። በመሆኑም እንዲያቀርቡ የተጠየቀዉን እቃ በአንድ ቀን ዉስጥ ማቅረብ የሚችል።
  19. ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 09 18 19 85 88 /09 34 62 32 87 ደውለው መረጃ መጠየቅ ይችላሉ።

የሳንጃ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *