የሀዋሳ ማዕከላዊ ማረሚያ ተቋም ለቢሮ አገልግሎት የሚውል የጽህፈት መሳሪያ ለመግዛት ይፈልጋል – test3.diretenders.com

የሀዋሳ ማዕከላዊ ማረሚያ ተቋም ለቢሮ አገልግሎት የሚውል የጽህፈት መሳሪያ ለመግዛት ይፈልጋል


Addis Zemen (Sep 09, 2026)

የጨረታ ማስታወቂያ

የሀዋሳ ማዕከላዊ ማረሚያ ተቋም ለቢሮ አገልግሎት የሚውል የጽህፈት መሳሪያ በዘርፉ ከተሠማሩ ህጋዊ ነጋዴዎች አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል ::

በዚሁ መሠረት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ነጋዴዎች መወዳደር ይችላሉ፡-

1.በዚህ ዘርፍ የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያላቸው የዘመኑ ግብር የከፈሉ፣ተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ፣ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር ያላቸውና ለአቅራቢነት የተመዘገቡ የንግድ ምዝገባ ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡

2. በጨረታው የሚሳተፉ ተጫራቾች ከላይ የተጠቀሱትን የጽህፈት መሳሪያ የሚፈለገው መጠን ጥራትንና ደረጃውን በጠበቀ መልኩ ተቋሙ ቅጥር ግቢ ድረስ አምጥተው ማስረከብ ይኖርባቸዋል፡፡

3. ማንኛውም ተጫራች በተራ ቁጥር 1 የተገለፁትን ህጋዊ ማስረጃዎች ለጨረታው ከሚቀርበው ዋጋ ጋር ዋናውንና ኮፒውን አያይዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡

4. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ማስከበሪያ በሁኔታዎች ላይ ያልተመሠረተ በባንክ በተረጋገጠ CPO 100,000 (መቶሺህ) ብር ከዋናው ሰነድ ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

5. የጨረታው ሰነድ ዋናውንና ኮፒውን በሰም በታሸገ ኢንቨሎኘ በሰነድ ላይ በተገለፀው አድራሻ በተከታታይ 15 ቀናት ለዚሁ በተዘጋጀ ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡

6. የጨረታው ሳጥን የሚታሸገው በአስራ አምስተኛ ቀን በ 4፡00 ሰዓት ሲሆን የጨረታ ሳጥን የሚከፈተው በዕለቱ ከጠዋቱ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበትም ሆነ ባልተገኙበት ይከፈታል ይህ ቀን የበዓልም ቅዳሜ ወይም እሁድ ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ከላይ በተገለፀው ተመሳሳይ ሰዓት ታሽጎ ይከፈታል፡፡

7. ማንኛውም ተጫራች የጽህፈት መሳሪያ ናሙና ጨረታው ከመከፈቱ አንድ ቀን ቀደም አድርጎ በማስገባት ጥራቱን ለጨረታ ኮሚቴ ማሳየት አለበት፡-

8. ተጫራቾች ከሀዋሳ ማዕከላዊ ማረሚያ ተቋም ግ/ፋ/ንብ/አስ/ደ/ሥ/ሂደት ቀርበው ዝርዝር ሰነዱን 200 (ሁለት መቶ) ብር በማይመለስ በመክፈል መግዛት ይኖርባቸዋል፡ ማሳሰቢያ፦ መ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉም ሆነ በክፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ተጨማሪ መረጃ ፡- በስልክ ቁጥር ፡-046-212-87-47 መደወል ይችላሉ ፡፡
የሲዳማ ብሔራዊ ክልል መንግሥት ሀዋሳ ማዕከላዊ ማረሚያ ተቋም


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *