የኢሉአባቦር ዞን ገንዘብ ጽ/ቤት በሥሩ ላሉት መ/ቤቶች ለ2019 ዓ.ም. የበጀት ዓመት አገልግሎት የሚውል ዕቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል – test3.diretenders.com

የኢሉአባቦር ዞን ገንዘብ ጽ/ቤት በሥሩ ላሉት መ/ቤቶች ለ2019 ዓ.ም. የበጀት ዓመት አገልግሎት የሚውል ዕቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል


Addis Zemen (Sep 09, 2026)

የጨረታ ማስታወቂያ

የኢሉአባቦር ዞን ገንዘብ /ቤት በሥሩ ላሉት /ቤቶች 2019 . የበጀት ዓመት አገልግሎት የሚውል

  • የተለያዩ የጽሕፈት መሳሪያዎች፣
  • የጽዳት ዕቃዎች፣
  • ፈርኒቸሮች፣
  • ኤሌክትሮኒክሶች፣
  • የተለያዬ መጠን ያላቸዉ የመኪና ጎማዎች ከነ ከለመዳሪያዎቻቸው፤
  • የእርሻ መገልገያ መሣሪያዎች እና
  • የተለያዩ የሠራተኞች የደንብ ልብስ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

ስለዚህ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ ነጋዴዎች መወዳደር ትችላላችሁ።

  1. በዘርፉ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፍቃድ ያለው፤የዘመኑን ግብር የከፈለና ማስረጃ አያይዞ ማቅረብ የሚችል እና የቫት (VAT) ተመዝጋቢ የሆነ፡፡
  2. በአቅራቢነት ዝርዝር የተመዘገበ እና ማስረጃ ማቅረብ የሚችል፡፡
  3. ለጨረታ ማስከበሪያ 70,000.00 (ሰባ ሺህ) ብር በስንቄ ባንክ ሂሣብ ቁጥር 1052194231219(ILU ABA BOR ZONE CENTERAL TREASURY) ገቢ በማድረግ የባንክ ደረሰኝ ለእያንዳንዱ ዶክመንት ማስያዝ የሚችልና ጨረታውን ካሸነፈ በኋላ ለውል ማስከበሪያ ያሸነፈበትን ዕቃ ጠቅላላ ዋጋ 10 % በባንክ በተመሰከረ በገንዘብ ብቻ ማስያዝ የሚችል፡፡
  4. ተጫራቹ ጨረታውን ካሸነፈ ደብዳቤ ከደረሰው ቀን ጀምሮ በተከታታይ 15 ቀን ውስጥ ቀርቦ ውል ለመፈረም ፈቃደኛ የሆነና ዕቃዎቹን በራሱ ሙሉ ወጪ በታዘዘ (በተሰጠው) ጊዜ ውስጥ እስከ /ቤቱ ለማቅረብና ቆጥሮ ለማስረከብ ፈቃደኛ የሆነ ፡፡
  5. ተጫራቹ የዕቃው ሞዴል ባልተገለጸበት ቦታ በጨረታው ዝርዝር ላይ አብራርቶ መግለጽ አለበት፡፡
  6. ተጫራቹ የተፈለገውን ዕቃ ጥራትና ብዛት አሟልተው የማቅረብ ግዴታ አለበት።
  7. ተጫራቹ ለሚያቀርባቸው የደንብ ልብሶች እና መሰሎች ናሙና ማቅረብ  የሚችል።
  8. ተጫራቹ የሚያቀርበው ዋጋ ቫትን ያካተተ ሆኖ ክፍያ ከከፈለው /ቤታችን ግማሹን (7.5) የሚቆርጥ መሆኑን እንገልጻለን ፡፡
  9. ተጫራቾች እያንዳንዱን የጨረታውን ሰነድ በማይመለስ አምስት መቶ(500) ብር ከኢሉአባቦር ዞን ገንዘብ /ቤት አንደኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 8 መግዛት ይችላሉ።
  10. በሌላ ተጫራች ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ ክልክል ነው ፡፡
  11. የሚወዳደሩበት ሰነድ ስርዝ ድልዝ የሌለው እና ግለጽ ሆኖ የሚነበብ መሆን አለበት፡፡
  12. ጨረታው ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 15 የሥራ ቀናት በአየር ላይ የሚቆይ ሲሆን 16 ቀን ከጠዋቱ 400 ሠዓት ላይ ተጠናቆ በዚሁ ቀን 430 ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸዉ በተገኙበት በግልጽ ይከፈታል፡፡ ይሁን እንጂ 16ኛው ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሣሣይ ሰዓት የሚከፈት ይሆናል፤፤
  13.  ተወዳዳሪዎች ዋጋን የሚገልጽ ሰነድ ኦሪጂናል እና ኮፒ ለየብቻ ፍቃድንና የተለያዩ ተፈላጊ ሰነዶችን የሚገልጽ ኦሪጂናል እና ኮፒ ለየብቻ በስንቄ ባንክ ሂሣብ ቁጥር 1052194231219(LU ABA BOR ZONE CENTERAL TREASURY) ገቢ የተደረገበት የባንክ ደረሰኝ ኦርጅናል ለብቻ በታሸገ ኤንቨሎፕ በተለያየ ፖስታ በማሸግ የሚጫረቱበትን መወዳደሪያ የአንዱን ዋጋ በመሙላት ለጨረታው በተዘጋጀ ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርበታል።
  14.  /ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ለበለጠ መረጃ፡/ ቁጥር — 047441 1125/047 141 0399

በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት መስተዳድር የኢሉአባቦር ዞን ገንዘብ /ቤት