Reporter (Sep 09, 2026)
የምግብ አቅርቦት የጨረታ ማስታወቂያ
ተስፋ ድርጅት አገር በቀል መንግስታዊ ያልሆነ ግብረ ሠናይ ድርጅት ሲሆን በአገራችን በተለያዩ ክልሎች ማለትም በጋምቤላ፣ በአሶሳ፣ በኦሮሚያ፣ በአማራና ደቡብ ክልል እንዲሁም በአዲስ አበባ ባሉን ቅርንጫፎች በትምህርት፣ በሙያ ስልጠና እና በእለት እርዳታ ዙሪያ የሰብአዊ አገልግሎት ሥራ እየሠራ ይገኛል።
ድርጅቱ ለሚረዳቸው ተማሪዎቹ፤
1. በኦሮሚያ ክልል በዝዋይ ዱግዳ ሂራራ ቀበሌ በሚገኘው ት/ቤት ለሚማሩ 260 ለሚጠጉ ተማሪዎች
2. በኦሮሚያ ክልል አርሲ ነገሌ ወረዳ ሮጌ ቀበሌ በሚገኘው ት/ቤት ለሚማሩ 600 ለሚጠጉ ተማሪዎች
3. በሲዳማ ክልል በውጅግራ ወረዳ ሲንታሮ ቀበሌ ት/ቤት ለሚማሩ 615 ለሚጠጉ ተማሪዎች ቁርስና ምሳ ምግብ የሚያቀርቡ ተጫራቾችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል።
በዚሁ መሰረት ህጋዊ የታደሰ የንግድ ፈቃድ እንዲሁም ቲን ሰርተፊኬት ማቅረብ የሚችል ተወዳዳሪ የመወዳደሪያ ቅጽ/ሰነድ ከተስፋ ድርጅት ዋናው መ/ቤት ብር 100 በመግዛት ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ መስከረም 6 ቀን 2019፣ ከቀኑ 6.00 ሰአት ድረስ በማህተም በተረጋገጠ እና በታሸገ ፖስታ ማስገባት እንደምትችሉ እናስታውቃለን።
በህጋዊ ማህተም ያልተሸገ ፖስታ ከውድድሩ ውድቅ ይሆናል።
ጨረታው መስከረም 6 ቀን 2019 ከቀኑ 8:00 ሰአት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪላቸው በተገኙበት በድርጅቱ መሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል።
ማሳሰቢያ፡– ድርጅቱ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው። በተጨማሪም አሸናፊ ተጫራጮች ለአንድ የትምህርት አመት 2019 ዓ.ም. ባቀረቡት ዋጋ ምግቡን የማቅረብ እና የመጨረስ ሀላፊነት አለባቸው።
ከአማካይ ምግብ ዋጋ ዝቅተኛ ወይም በጣም ከፍተኛ ዋጋ ማቅረብ ከጨረታ ሊያሰርዙ ይችላሉ።
ለበለጠ መረጃ፡ አ.አ ዋናው መስሪያ ቤ/ት አየር ጤና፣ ሳሚ ካፌ ፊት ለፊት
ስልክ ቁጥር 011 348 2537 የመሳጥን ቁጥር 30153 አዲስ አበባ ወይም
ድርጅቱ