Addis Zemen (Sep 10, 2026)
ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
በአ.ብ.ክ.መ. ደቡብ ወሎ አስተዳደር ዞን የሐይቅ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት ግዥ፣ ፋይናንስና ንብረት አስተዳደር ቡድን በ2019 በጀት ዓመት በUNDP በጀት በቀበሌ 2 አስተዳደር ክልል
- ሎት 1. ትምህርት ቤት መማሪያ ክፍል ግንባታ ስራ፤
- ሎት 2 የቀበሌ 2 ቢሮ አስተዳደር ግንባታ ስራ በግልፅ ጨረታ ማወዳደር ይፈልጋል፡፡
በዚህም መሠረት፤-
- በዘመኑ የታደሠ የንግድ ሥራ ፈቃድ እና የንግድ ምዝገባ ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችል፤
- የብቃት ማረጋገጫ ምሥክር ወረቀት ያላቸው ፤
- የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ወረቀት ማቅረብ የሚችል፤
- የኤክሳይዝ ታክስ የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያሳይ ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችል፤
- የበጀት አመቱ ተገቢውን የታክስ እና ግብር ግደታ የተወጡ መሆኑን የሚያሳይ የታክስ ክሊራስ ማቅረብ የሚችል
- የዕቃ ወይም የአገልግሎት ግዥው መጠን ብር 200,000.00 ( ሁለት መቶ ሺህ ብር) እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ /VAT/ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ሲገዙ ለእያንዳንዱ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 500.00 ( አምስት መቶ ብር ) በመክፈል ሐይቅ ከተማ አስ/ገንዘብ ጽ/ቤት ግዥ፣ ፋይ/ንብ/አስተዳደር ቡድን ቢሮ ቁጥር 8 ድረስ በመቅረብ መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ሎት 1 ትምህርት ቤት መማሪያ ክፍል ግንባታ ስራ ብር 52,500፣ ሎት 2 የቀበሌ 2 ቢሮ አስተዳደር ግንባታ ስራ ብር 47,500፤ በባንክ በተረጋገጠ ትዕዛዝ (CPO ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በባንክ የተረጋገጠ ቢድ ቦንድ ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- የጨረታ ሰነዱን ዋናና ቅጅ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፓስታ ሐይቅ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት ግዥ፣ ፋይ/ንብ/አስተዳደር ቡድን ቢሮ ቁጥር 8 ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 20 ቀናት ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው በ21ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ታሽጐ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል ( ባይገኙም ይከፈታል )ቅዳሜና ዕሁድ ወይም የህዝብ በዓል ቀን ከሆነ በቀጣዩ የሥራ ቀን በተመሣሣይ ሰዓት ይፈፀማል፡፡
- ማንኛውም ተጫራች ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ራሱን ከጨረታው ውድድር ማግለል የማይችል ሲሆን፤ በጨረታ ሠነዱ የሠጠውን ዋጋና መግለጫ መለወጥና ማሻሻል አይችልም፡፡
- የሂሳብ ስሌት ( አርቲሜቲክ ቴክ ) በዥ ፈፃሚው መ/ቤት ባለሙያ ከሚስተካከለው ውጭ በተጫራቾች የሚቀርበው የመጫረቻ ሠነድ ላይ በነጠላና ጠቅላላ ዋጋ ላይ ስርዝ ድልዝ ካለ ተጫራቹ ከጨረታ ውጭ ይሆናል፡፡
- ተጫራቾች ለሥራው የሚያስፈልጉ ማሽነሪዎችንና የሠው ኃይልን በሙሉ ራሣቸው ችለው ነው፣፣
- ተጫራቾች ከደረጃ 5 እና ከዚያ በላይ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡
- ጠቅላላ ሥራ ተቋራጭ የንግድ ሥራ ፈቃድ ያላቸው
- የህንፃ ሥራ ተቋራጭ የንግድ ሥራ ፈቃድ ያላቸው ፤
- አሸናፊው የሚለየው በሎት ጠቅላላ ዋጋ ሲሆን ፤ በቴክኒካልና ፋይናንሽያል ድምር ውጤት ነው፡፡
- በቴክኒካልና ፋይናንሽያል የሚቀርቡ መረጃዎች ግልፅና ጎላ ብለው የሚነበቡ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡
- ጽ/ቤቱ እንደ በጀቱ ሁኔታ በጨረታ ሰነዱ ላይ የተዘረዘሩትን ሥራዎች ብዛት 20% መጨመርም ሆነ መቀነስ ይችላል፡፡
- የትምህርት ቤት መማሪያ ክፍል ግንባታ ስራ፤ እና የቀበሌ 2 ቢሮ አስተዳደር ግንባታ ሥራዎች ጥራታቸው የተጠበቀ መሆን አለበት፡፡
- አሸናፊው ድርጅት ሥራውን ጥራቱን ጠብቆ እንዳጠናቀቀ ገንዘቡን ወጪ አድርጐ ይወስዳል፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 033-222-01 62 ደውሎ መጠየቅ ይችላል፡፡
በደቡብ ወሎ ዞን የሐይቅ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት
የግዥ ፋይናንስና ንብረት አስተዳደር ቡድን