Addis Zemen (Sep 11, 2026)
የጨረታ ማስታወቂያ
የደብርሃን እንጨት ማቀነባበሪያ ኃ/የተ/የግል ማህበር ለሠራተኞች የስራ ልብስ የሚሆን
- ሎት 1፡– የተዘጋጀ የሥራ ልብስ (ጃኬትና ሱሪ) እና ሸርጥ እንዲሁም
- ሎት 2፡– ጓንት እና መጥረጊያ፣ በዘርፉ ከተሰማሩ ድርጅቶች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
በዚህ መሰረት፡–
1. በእያንዳንዱ ሎት ላይ በትከክለኛው የስራ መስክ የተሰማራና የንግድ ስራ ፈቃዱን ያሳደሰ
2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /ቲን ነምበር, ያላቸው
3. የቫት ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል።
4. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ ከተራ ቁጥር 1-3 የተጠቀሱትና ሌሎች የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።
5. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/ ለሎት1 ፡– 20,000.00 (ሃያ ሺህ ብር) ሎት 2፡– 10,000.00 (አስር ሺህ ብር) ለሁሉም ሎቶች ለእያንዳንዳቸው ከላይ የተጠቀሰውን የገንዘብ መጠን ለየብቻው በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትእዛዝ /CPO/ ማስያዝ አለባቸው።
6. ተጫራቾች በሚያቀርቡት ሰነድ ላይ ስማቸውን፣ ፊርማቸውንና አድራሻቸውን ማስፈርና የድርጅቱን ማህተም ማድረግ አለባቸው።
7. በመጫረቻ ሰነዱ ላይ ምንም አይነት ስርዝ ድልዝ መኖር የለበትም፤ ካለም አንድ ሰረዝ በማድረግ ፊርማቸውን ማስቀመጥ ይኖርባቸዋል።
8. በአንድ ሎት ውስጥ ከተዘረዘሩት እቃዎች መካከል ከፋፍሎ ወይም ቀንሶ መወዳደር አይቻልም።
9. ማንኛውም ተጫራች ኦሪጅናል የጨረታ ሰነድ ለሁሉም ሎቶች ለየብቻ ኦርጅናል ፓስታ በማዘጋጀት እና በጥንቃቄ ለየብቻ በማሸግ በካምፓኒው የፋይናንስ ቢሮ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ይህ ጨረታ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 16 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ የጨረታውን ሰነድ ገቢ ማድረግ ይችላሉ። ነገር ግን ሁለቱንም ሎቶች በ 1/በአንድ/ ፖስታ ማቅረብ አይቻልም።
10. አንድ ተጫራች የንግድ ሥራ መስኩ ከፈቀደለት በሁሉም ሎቶች ወይም የሚፈልገውን ሎት ብቻ መርጦ መወዳደር ይችላል።
11. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ16ኛው ቀን ጨረታው በተዘጋበት ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ላይ ታሽጎ 4፡30 ሰዓት ላይ በካምፓኒው የፋይናንስ ቢሮ ውስጥ በይፋ ይከፈታል። ተጫራቾች ባይገኙም ከመከፈት አይታገድም።
12. የመክፈቻ ቀኑ የህዝብ በዓል ወይም እሁድ ቀን ከዋለ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል።
13. አሸናፊ ሆኖ የተመረጠው ተጫራች አሸናፊ መሆኑ ሲገለፅለት የውል ማስከበሪያ የሚሆን ገንዘብ በሲፒኦ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና የአሸነፈበትን ጠቅላላ ዋጋ 10% ያስይዛል።
14. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ለእያንዳንዱ ሎት /የጨረታ ሰነድ/ ለየብቻ የማይመለስ ብር 200.00 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል ከካምፓኒው የፋይናንስ ቢሮ መውሰድ ይችላሉ።
15. አቅራቢ ድርጅቱ የማስጫኛ እና የማስወረጃ እንዲሁም ሌሎች ወጪዎችን ሸፍኖ ንብረቱን ለካምፓኒው ንብረት ክፍል ያስረክባል።
16. ካምፓኒው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር፡– 011637 58 03 ደውለው ይጠይቁ
የደ/ብርሃን እንጨት ማቀነባበሪያ ኃ/የተ/የግል ማህበር
ደ/ብርሃን