በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ ጤና ጽ/ቤት የገላን ጉራ ጤና ጣቢያ የ2019 ዓ.ም በጀት ዓመት ቋሚ እቃ፣ የደንብ ልብስ፣ አላቂ የፅዳት እቃዎች፣ አላቂ የቢሮ እቃዎች፣ ልዩ ልዩ መሳሪያዎች እና የህትመት ስራዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል – test3.diretenders.com

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ ጤና ጽ/ቤት የገላን ጉራ ጤና ጣቢያ የ2019 ዓ.ም በጀት ዓመት ቋሚ እቃ፣ የደንብ ልብስ፣ አላቂ የፅዳት እቃዎች፣ አላቂ የቢሮ እቃዎች፣ ልዩ ልዩ መሳሪያዎች እና የህትመት ስራዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል


Addis Lessan (Sep 11, 2026)

ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር አቃ////10///////001/2019 .

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በአቃቂ ቃሊቲ /ከተማ ጤና /ቤት የገላን ጉራ ጤና ጣቢያ 2019 . በጀት ዓመት ሎት 1ቋሚ እቃ ሎት 2የደንብ ልብስ ሎት 3አላቂ የፅዳት እቃዎች ሎት 4አላቂ የቢሮ እቃዎች ሎት 5ልዩ ልዩ ማሳሪያዎች ሎት 6የህትመት ስራዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

በዚሁ መሰረት ተጫራቾች

1. የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣ በአቅራቢዎች ምዝገባ ዝርዝር የተመዘገቡ፣ የቲን እና የቫት ተመዝጋቢ የሆኑና የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡ ጥቃቅንና አነሰተኛ በራሳቸው ሰርተው ለሚያቀርቡ እቃዎች ብቻ የተፃፈ የድጋፍ ደብዳቤ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

2. ተጨራቾች የሚወዳደሩባቸውን እቃዎች ለእያንዳንዱ ከቫት ጋር ያለውን ዋጋ ማስቀመጥ ይጠበቅባቸዋል።

3. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን በየሎቱ በመለየት ፖስታ ላይ በመግለፅ አሽገው ኦሪጅናል እና ኮፒ ብለው በመፃፍ ለይተው የድርጅታቸውን ማሕተም እና ፊርማ በማድረግ በጤና ጣቢያው የግዢ ቡድን ቢሮ ቁጥር -405- ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።

4. ተጨራቾች ለጨረታው የተዘጋጀውን ሰነድ በየሎቱ የማይመለስ 200 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል በጤና ጣቢያው የግዢ ቡድን ቢሮ ቁጥር -405- መውሰድ ይችላሉ።

5. ይህ ጨረታ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 10 ተከታታይ የስራ ቀናት አየር ላይ የሚውል ሲሆን የጨረታው ሳጥን 11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4:00 ሰዓት ላይ ታሽጎ በዚሁ ቀን ከጠዋቱ 430 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የሚከፈት ሲሆን ምናልባት 11ኛው ቀን የህዝብ በዓል ወይም ከመንግስት የስራ ሰዓት ውጭ ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት የሚከፈት ይሆናል።

6. የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተመሰከረለት ቼክ ወይም CPO መጨረሻ ተመላሽ የሚሆን ለሎት 1ቋሚ እቃ 34000 ለሎት 2የደንብ ልብስ 25000 ለሎት 3አላቂ የፅዳት እቃዎች 21000 ለሎት 4አላቂ የቢሮ እቃዎች 8000 ለሎት 5ልዩ ልዩ መሳሪያዎች 2000 ለሎት 6የሕትመት ስራዎች 5000 ማስያዣ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

7. በጨረታ ሰነዱ ላይ የተገለጸው ሙሉ ዝርዝር ሁኔታ የጨረታው መመሪያ ሆኖ ችግሮች ካጋጠሙ በጊዜው መመሪያ የሚዳኝ ይሆናል።

8. አሸናፊ ተጫራቾች ያሸነፉባቸውን እቃዎች በራሳቸው ትራንስፖርት ግዥ ፈጻሚው መስራያ ቤት ድረስ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።

9. የጨረታ ዋጋ የሚሞላው በተቀመጠለት መለኪያ ብቻ ሲሆን ከመለኪያው ውጪ የተሞላ ዋጋ እንዲሁም ስርዝ ድልዝ ወይም በፍሉድ የተነካካ ዋጋ ሙሉ በሙሉ ከጨረታው ውድቅ ይደረጋል።

10. ተጨራቾች ለሚጫራቱት እቃዎች ሙሉ በሙሉ ናሙና ማቅረብ እና በሚያቀርቡት ናሙና ላይ ምልክት ወይም ድርጅቱን የሚገልጽ ምልክትም ሆነ ማሕተም ማድረግ የለባ ቸውም፡፡ ተጨራቾች የሚያቀርቡት ናሙና ከሚያስገቡት እቃ ጋር ፍጹም የተለየ መሆን የለበትም።

11. ጨረታውን አሸነፊ ሆነው ከተገኙ በኃላ 10% ባሸነፉት እቃ መጠን የውል ማስከበሪያ ማስያዝ ይኖርባቸዋል።

12. /ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡ በተጨማሪ ለማብራሪያ ጥያቄ ለጨረታው ከቀረቡ የእቃዎች ዝርዝር ውስጥ /ቤቱ እስከ 25 በመቶ ለመጨመር ወይም ለመቀነስ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር፡– 0901 259 401 / 0975 995 034 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።

አድራሻ፡ከጎሮ ወደ ኮየ በሚወስደው መንገድ 11 አደባባይ 2 ኪሎ ሜትር ገባ ብሎ

በአቃ////10 ገላን ጉራ ጤና ጣብያ

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮ አቃቂ ቃሊቲ /ከተማ ወረዳ 10 የገላን ጉራ ጤና ጣቢያ