ቤቱ ያረፈበት ስፋት 179 ካ/ሜ በጠቅላላ በፕሮፖርሽን የሚደርሰው የቦታ ስፋት 211 ካ/ሜ ቤት የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ – test3.diretenders.com

ቤቱ ያረፈበት ስፋት 179 ካ/ሜ በጠቅላላ በፕሮፖርሽን የሚደርሰው የቦታ ስፋት 211 ካ/ሜ ቤት የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ


Addis Zemen (Sep 11, 2026)

የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ

የፍ/ባለመብት እነ / ሮዛ አብዱልቃድር እና በፍ/ባለዕዳ እነ አቶ ከድር አብዱልቃድር መካከል ስላለው የፍርድ አፈጻጸም ጉዳይ የፌ////ቤት በኮ//.203842 21/06/2014 . እና የፌ////ቤት በኮ//.228875 26/11/2014. በዋለው ችሎት በተሰጠው ትዕዛዝ መሰረት በአራዳ /ከተማ ወረዳ 01 የቤት ቁጥር 376 የካርታ ቁጥር /02/24/3187/00/00 የይዞታ መለያ ቁጥር AA000010100045 የሆነው ቤቱ ያረፈበት ስፋት 179 / በጠቅላላ በፕሮፖርሽን የሚደርሰው የቦታ ስፋት 211 / የሐራጅ መነሻ 7,863,731 (ሰባት ሚሊዮን ስምንት መቶ ስልሳ ሶስት ሺህ ሰባት መቶ ሰላሳ አንድ) ሆኖ የትራንዛክሽን ታክስ ገዥ የሚከፍል መሆኑ ታውቆ ጥቅምት 2 ቀን 2019 / በሐራጅ ይሸጣል፡፡ የተጫራቾች ምዝገባ 800 ሰዓት ተጀምሮ የቀረቡ ተጫራቾች ተመዝግበው እንደተጠናቀቀ ወዲያውኑ ጨረታው የሚካሄድ ይሆናል፡፡

የሐራጁ ሽያጭ የሚካሄደው በፌደራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም /ቤት የጨረታ አዳራሽ ውስጥ ሲሆን፣ ንብረቱን ተጫርተው ለመግዛት የሚፈልጉ ተጫራቾች ከጨረታው ቀደም ብሎ ባሉት አራት የሥራ ቀናቶች ውስጥ ባለመብቱ ለማስጎብኘት በሚመርጧቸው ሦስት የሥራ ቀናት በፌ//ቤቶች ፍርድ አፈፃፀም /ቤት ሐራጅ ክፍል ድረስ ከጠዋቱ 330 ብቻ በመገኘትና ባለመብቱ በሚያቀርበው ትራንስፖርት ንብረቱን ባለበት ቦታ ድረስ በመውሰድ ለመጐብኘት የሚችሉ ሲሆን እያንዳንዱ ተጫራች በሚጫረትበት ወቅት የንብረቱን መነሻ ግምት 1/4 ኛውን በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተረጋገጠ CPO ማስያዝ ይኖርበታል፡፡ 1/4 አስበልጦም ሆነ አሳንሶ የሚመጣ ተጫራች በጨረታው አይካፈልም፡፡ በጨረታው አሸናፊ የሆነው ግለሰብ አሸናፊ የሆነበትን ገንዘብ በአጠቃላይ ጨረታውን ከአሸነፈበት ቀን ጀምሮ በፍ/ አፈ//ቤት ስም CPO አሠርቶ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ብቻ ሙሉ ገንዘቡን 15 ቀናት ውስጥ ገቢ ማድረግ አለበት በጨረታ አሸናፊ የሆነ በጨረታ ያሸነፈበትን ገንዘብ ገቢ ሳይደረግ ቀርቶ በቀጣይ ጨረታ ተደርጎ ጨረታው ከበፊቱ ጨረታው ቀንሶ ከተሸጠ ገዥው በልዩነት ተጠያቂ እንደሚሆን የፍ/አፈ//ቤት ንብረቱን በሕጋዊ መንገድ በሐራጅ ስለመሸጡ ለሚመለከተው አካል ማስረጃ ከመጻፍ ባለፈ ስም የማዛወር ግዴታ የሌለበት መሆኑን እንገልፃለን፡፡

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር +251 112 730 852 በመደወል መጠየቅ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡

የፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈፃፀም /ቤት


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *