የቦታ ስፋቱ 130 ካ.ሜ የሆነ ቤት የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ – test3.diretenders.com

የቦታ ስፋቱ 130 ካ.ሜ የሆነ ቤት የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ


Addis Zemen (Sep 12, 2026)

የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ

የፍ/ ባለመብት ወ/ሮ ገነት መገርሳ እና የፍ /ባለዕዳ እነ መድሃኒት መገርሳ መካከል ስላለው የፍርድ አፈጻጸም ጉዳይ በፌ/ መ/ደ/ፍ/ቤት በመ ቁጥር 330138 30/07/2018 ዓም እና በኮ// 332538 በ10/9/2018 / በዋለው ችሎት በሰጠው ትዕዛዝ መሠረት በልደታ /ከተማ ወረዳ 03 የቤት ቁጥር 279 የቦታ ስፋት 130 ካ.ሜ የሰፈር መንገድ 20 / ይነካዋል፡፡ የሐራጅ መነሻ ዋጋ ብር 3,418,6530 (ሶስት ሚሊዮን አራት መቶ አስራ ስምንት ሺህ ስድስት መቶ ሰላሳ) ሆኖ የትራዛክሽን ታከስ ገዥ የሚከፍል መሆኑ ታውቆ ጥቅምት 4 ቀን 2019 / በሐራጅ ይሸጣል፡፡ የተጫራቾች ምዝገባ 400 ሰዓት ተጀምሮ የቀረቡ ተጫራቾች ተመዝግበው እንደተጠናቀቀ ወዲያውኑ ጨረታው የሚካሄድ ይሆናል፡፡

የሐራጅ ሽያጭ የሚካሄደው በፌደራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም /ቤት የጨረታ አዳራሽ ውስጥ ሲሆን፣ ንብረቱን ተጫርተው ለመግዛት የሚፈልጉ ተጫራቾች ከጨረታው ቀደም ብሎ ባሉት አራት የሥራ ቀናቶች ውስጥ ባለመብቱ ለማስጎብኘት በሚመርጧቸው ሶስት የስራ ቀናት በፌ//ቤቶች ፍርድ አፈፃፀም ቤት ሐራጅ ከፍል ድረስ ከጠዋቱ 33 ብቻ በመገኘትና ባለመብቱ በሚያቀርበው ትራንስፖርት ንብረቱን ባለበት ቦታ ድረስ በመውሰድ ለመጐብኘት የሚችሉ ሲሆን እያንዳንዱ ተጫራች በሚጫረትበት ወቅት የንብረቱን መነሻ ግምት 1/4ኛውን በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተረጋገጠ CPO ማስያዝ ይኖርበታል፡፡ ከ1/4ኛው አስበልጦም ሆነ አሳንሶ የሚመጣ ተጫራች በጨረታው አይካፈልም፡፡ በጨረታው አሸናፊ የሆነው ግለሰብ አሸናፊ የሆነበትን ገንዘብ በአጠቃላይ ጨረታውን ከአሸነፈበት ቀን ጀምሮ በፍ/አፈ//ቤት ስም C.PO አሰርቶ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ብቻ ሙሉ ገንዘቡን 15 ቀናት ውስጥ ገቢ ማድረግ አለበት በጨረታ አሸናፊ የሆነ በጨረታ ያሸነፈበትን ገንዘብ ገቢ ሳይደረግ ቀርቶ በቀጣይ ጨረታ ተደርጎ ጨረታው ከበፊቱ ጨረታው ቀንሶ ከተሸጠ ገዥው በልዩነት ተጠያቂ እንደሚሆን የፍ/አፈ//ቤት ንብረቱን በህጋዊ መንገድ በሐራጅ ስለመሸጡ ለሚመለከተው አካል ማስረጃ ከመጻፍ ባለፈ ስም የማዛወር ግዴታ የሌለበት መሆኑን እንገልፃለን፡፡

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር +251112730852 በመደወል መጠየቅ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡

የፌደራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም /ቤት


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *