Addis Zemen (Sep 12, 2026)
የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ
የፍ/ባለመብት አልማዝ ወርቁ እና የፍ/ባለዕዳ ጌታመሳይ ግርማ መካከል ስላለው የፍርድ አፈጻጸም ጉዳይ መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በኮ/መ/ቁ 214677 ሰኔ 27 ቀን 2017 ዓ.ም እና በኮ/መ/ቁ/274048 በ14/05/2018ዓ/ም በዋለው ችሎት በሰጠው ትዕዛዝ መሠረት በአራዳ ክ/ከተማ ወረዳ 7 የሚገኝ የቤ/ቁ 069 የሆነ ቤት በካርታ ቁጥር አ/13/46/7980/02 ሴሪ ቁጥር 031621 በአቶ ጌታመሳይ ግርማ ይመር ስም ተመዝግቦ የሚገኝ ተነፃፃሪ የቤት ባለቤትነት ማረጋገጫ ምስክር ወረቀት ያለው ቤቱ ያረፈበት 83 ካ.ሜ በፕሮፖርሽን ከግቢው ለቤቱ የሚደርሰው የቦታ ድርሻ ስፋት 60 ካሜ ጠቅላላ በፕሮፖርሽን ለግለሰቡ የሚደርሰው የቦታ ስፋት 143 ካ.ሜ አዋሳኞቹን በተመለከተ በሰሜን የመንግስት ቤት ፤በምስራቅ የመንግስት ቤት ፤ በደቡብ አቶ ሰለሞን በምዕራብ አቶ ደስታ ቤቱ/ ይዞታው አራት ኪሎ ቀበና ባለው የመንገድ የኮሪደር ፕላን ውስጥ ያረፈ በመሆኑ ለልማት የተያዘ መሆኑን የሆነው ቤት የሐራጅ መነሻ ዋጋ 7,391,918.00 (ሰባት ሚሊዬን ሶስት መቶ ዘጠና አንድ ሺህ ዘጠኝ መቶ አስራ ስምንት ብር ) ሆኖ የትራዛክሽን ታከስ ገዥ የሚከፍል መሆኑ ታውቆ ጥቅምት 4 ቀን 2019ዓ/ም በሐራጅ ይሸጣል፡፡ የተጫራቾች ምዝገባ 5፡00 ሰዓት ተጀምሮ የቀረቡ ተጫራቾች ተመዝግበው እንደተጠናቀቀ ወዲያዉኑ ጨረታው የሚካሄድ ይሆናል።
የሐራጁ ሽያጭ የሚካሄደው በፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት የጨረታ አዳራሽ ውስጥ ሲሆን፣ ንብረቱን ተጫርተው ለመግዛት የሚፈልጉ ተጫራቾች ከጨረታው ቀደም ብሎ ባሉት አራት የሥራ ቀናቶች ውስጥ ባለመብቱ ለማስጎብኘት በሚመርጧቸው ሶስት የስራ ቀናት በፌ/ፍ/ ቤቶች ፍርድ አፈፃፀም ጽ/ቤት ሐራጅ ክፍል ድረስ ከጠዋቱ በ3፡30 ብቻ በመገኘትና ባለመብቱ በሚያቀርበው ትራንስፓርት ንብረቱን ባለበት ቦታ ድረስ በመውሰድ ለመጐብኘት የሚችሉ ሲሆን እያንዳንዱ ተጫራች በሚጫረትበት ወቅት የንብረቱን መነሻ ግምት 1/4 ኛውን በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተረጋገጠ C.PO ማስያዝ ይኖርበታል፡፡ ከ1/4ኛው አስበልጦም ሆነ አሳንሶ የሚመጣ ተጫራች በጨረታው አይካፈልም፡፡ በጨረታው አሸናፊ የሆነው ግለሰብ አሸናፊ የሆነበትን ገንዘብ በአጠቃላይ ጨረታውን ከአሸነፈበት ቀን ጀምሮ በፍ/አፈ/ጽ/ቤት ስም C.PO አሰርቶ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ብቻ ሙሉ ገንዘቡን በ15 ቀናት ውስጥ ገቢ ማድረግ አለበት በጨረታ አሸናፊ የሆነ በጨረታ ያሸነፈበትን ገንዘብ ገቢ ሳይደረግ ቀርቶ በቀጣይ ጨረታ ተደርጎ ጨረታው ከበፊቱ ጨረታው ቀንሶ ከተሸጠ ገዥው በልዩነት ተጠያቂ እንደሚሆን የፍ/አፈ/ጽ/ቤት ንብረቱን በህጋዊ መንገድ በሐራጅ _ ስለመሸጡ ለሚመለከተው አካል ማስረጃ ከመጻፍ ባለፈ ስም የማዛወር ግዴታ የሌለበት መሆኑን እንገልፃለን፡፡ ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር +251112730852 በመደወል መጠየቅ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን።
የፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈፃፀም ጽ/ቤት