Addis Zemen (Sep 12, 2026)
የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ
የፍ ባለመብት ጆሽዋ ሁለገብ ኃ/የተ/የግ/ማህበር እና የፍ/ባለዕዳ አልማዝ ታደሰ መካከል ስላለው የፍርድ አፈጻጸም ጉዳይ በፌ/መ/ደ/ፍ/ቤት በመ/ቁጥር 258796 በ2/2/2016ዓ/ም እና በኮ/መ/ቁ/315163 28/05/2017ዓ/ም በዋለው ችሎት በሰጠው ትዕዛዝ መሠረት በድሮ የካ ክ/ከተማ ወረዳ 13 በአዲሱ ለሚኩራ ክ/ከተማ በይዞታ መለያቁጥር AA0000513049 35 በሴሪያል ቁጥር 045078 በአልማዝ ታደሰ ስም የተመዘገበ መኖሪያ ቤት የቦታ ስፋት 512ካ/ሜ የቦታ ስፋት 161.98ካ/ሜ G+1 እና 89.65 ካ/ሜ ሰርቪስ ቤተ ከይዞታው በስተደቡብ አቅጣጫ 10 ሜትር የውስጥ ለውስጥ መንገድ ከጠቅላላ ይዞታ ላይ 37 ካ/ሜ የሚቆርጠው ሆኖ የሐራጅ መነሻ ዋጋ ብር 23,546,436 (ሃያ ሶስት ሚሊዮን አምስት መቶ አርባ ስድስት ሺህ አራት መቶ ሰላሳ ስድስት) ሆኖ የትራክሽን ታከስ ገዥ የሚከፍል መሆኑ ታውቆ ጥቅምት 5 ቀን 2019 ዓ/ም በሐራጅ ይሸጣል። የተጫራቾች ምዝገባ 5፡00 ሰዓት ተጀምሮ የቀረቡ ተጫራቾች ተመዝግበው እንደተጠናቀቀ ወዲያውኑ ጨረታው የሚካሄድ ይሆናል፡፡
የሐራጁ ሽያጭ የሚካሄደው በፌደራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት የጨረታ አዳራሽ ውስጥ ሲሆን፣ ንብረቱን ተጫርተው ለመግዛት የሚፈልጉ ተጫራቾች ከጨረታው ቀደም ብሎ ባሉት አራት የሥራ ቀናቶች ውስጥ ባለመብቱ ለማስጎብኘት በሚመርጧቸው ሶስት የስራ ቀናት በፌ/ፍ/ቤቶች ፍርድ አፈፃፀም ጽ/ቤት ሐራጅ ክፍል ድረስ ከጠዋቱ በ3፡30 ብቻ በመገኘትና ባለመብቱ በሚያቀርበው ትራንስፓርት ንብረቱን ባለበት ቦታ ድረስ በመውሰድ ለመጐብኘት የሚችሉ ሲሆን እያንዳንዱ ተጫራች በሚጫረትበት ወቅት የንብረቱን መነሻ ግምት 1/4ኛውን በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተረጋገጠ CPO ማስያዝ ይኖርበታል፡፡ ከ1/4ኛው አስበልጦም ሆነ አሳንሶ የሚመጣ ተጫራች በጨረታው አይካፈልም፡፡ በጨረታው አሸናፊ የሆነው ግለሰብ አሸናፊ የሆነበትን ገንዘብ በአጠቃላይ ጨረታውን ከአሸነፈበት ቀን ጀምሮ በፍ/አፈ/ጽ/ቤት ስም CPO አሰርቶ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ብቻ ሙሉ ገንዘቡን በ15 ቀናት ውስጥ ገቢ ማድረግ አለበት በጨረታ አሸናፊ የሆነ በጨረታ ያሸነፈበትን ገንዘብ ገቢ ሳይደረግ ቀርቶ በቀጣይ ጨረታ ተደርጎ ጨረታው ከበፊቱ ጨረታው ቀንሶ ከተሸጠ ገዥው በልዩነት ተጠያቂ እንደሚሆን የፍ/ አፈ/ጽ/ቤት ንብረቱን በህጋዊ መንገድ በሐራጅ ስለመሸጡ ለሚመለከተው አካል ማስረጃ ከመጻፍ ባለፈ ስም የማዛወር ግዴታ የሌለበት መሆኑን እንገልፃለን፡፡ ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር +251112730852 በመደወል መጠየቅ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡
በፌ/ፍ/ቤቶች ፍርድ አፈፃፀም ጽ/ቤት