Addis Zemen (Sep 13, 2026)
የጨረታ ማስታወቂያ
በኦሮሚያ ፖሊስ የተዘጋጃ ግ/ጨ/02/2019 የበጀት ዓመት
የኦሮሚያ ፖሊስ በ2019 የበጀት ዓመት ለክልሉ ፖሊስ ዋና ቢሮ ስራ አገልግሎት የሚውል የተለያዩ የቴክኖሎጂ መሳሪያዎች በተዘጋጁ እስፔስፍኬሽን መሰረት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
በዚሁ መሰረት የግዥው አይነት፡-
- 1. Server
- 2. Server Rack 42U
- 3. KVM
- 4. Wireless Access Point (wifi)
- 5.POE Switch 8 port
- 6.SFP Module
- 7. Smart Digital Podium
- 8.Video Wall/indoor Screen For Meeting Room (Module Screen)
- 9.Data Center Cooling System (AC Cooling System)
በመሆኑም በዘርፉ የተሰማሩ ብቃት ያላቸው ተወዳዳሪዎችን ለውድድር ይጋብዛል።
1. ተጫራቾች ህጋዊ የታደሳ ንግድ ፍቃድ ያላቸው፤
2. የዘመኑን ግብር የከፈሉ እና ስለመክፈላቸው የሚያሳይ ማስረጃ ማቅረብ የሚችል፤
3. በአቅራቢዎች ዝርዝር የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚገልጽ ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው።
4. ማንኛውም ተወዳዳሪ የሚወዳደርበት ኦርጅናል ካታሎግ ማቅረብ አለባቸው::
5. ኦርጅናል ካታሎግ ያለቀረባ ተወዳዳሪ ከውድድሩ ውጭ ይሆናል።
6. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና 2% ሆኖ የሚያስዙት ዋስትና ከ500,000.00 (አምስት መቶ ሺህ) ብር በላይ ከሆነ 500,000.00 (አምስት መቶ ሺህ) ብር ብቻ በባንክ የተረጋገጣ ሲፒኦ ወይም የባንክ ጋራንት ብቻ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
7. የጨረታ ሰነዱ በአድስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በተከታታይ ለ15 (አስራ አምስት) ቀናት ከፋይናንስ መምሪያ በመቅረብ የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) ብቻ በመክፈል መግዛት ይችላሉ።
8. አሸናፍ ድርጅት ያሸነፈባቸውን ዕቃዎችን በራሱ ወጪ የማጎጎያዣ፤መጫኛ እና ማውረጃ ወጪዎችን ሸፍነው በኦሮሚያ ፖሊስ ዋና መስሪያቤት ድረስ በማቅረብ እንስታሌሽኑን በማጠናቀቅ ማስረከብ ይጠበቅባቸዋል።
9. ማንኛውም ተወዳዳሪ የመወዳደሪያ ሰነድ ስያዘጋጅ እና ስያስገባ ቴክኒካል እና ፋይናንሻል በመለያት ማቅረብ ይጠበቅበታል፤ ማለትም ቴክኒካል ኦርጅናል እና ኦርጅናል ካታሎግ፣ቴክኒካል ኮፒ፣ፋይናንሻል ኦርጅናል፣ፋይናንሻል ኮፒ እና ሲፒኦ ለየብቻ በማሸግ ሁሉንም ፖስታዎች በአንድ ትልቅ ፖስታ በማሸግ ማቅረብ አለበት።የህንን ያላሟላ ተወዳዳሪ ከውድድሩ ውጭ ይሆናል።
10. ማንኛውም ተጫራች የመወዳደሪያ ሰነድ ስያዘጋጅ ቫት እና ማንኛውንም ወጭን ጨምሮ መሙላት አለበት፤ ይህ ካልሆነ የቀረበ ዋጋ ሁሉንም ወጪዎች አካቶ እንደተሞላ ተደርጎ ይቆጠራል።
11. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዳቸውን የሚያስገቡበት የመጨረሻ ቀነ ገደብ 22/01/2019 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ይሆናል።
12. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት 22/01/2019 ዓ.ም በኦሮሚያ ፖሊስ ግዥ አገልግሎት መምሪያ ውስጥ በ4፡30 ሰዓት ይከፈታል።
13. ኮሚሽኑ የተሻላ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
የኦሮሚያ ፖሊስ፡-
አድራሻ፡-ኦሮሚያ ፖሊስ አ/አባበ ክ/ከተማ ቂርቆስ ላንቻ አከባቢ
ለተጨማሪ መረጃ፡-0913 108 990 ወይም 0996 054 778 መደወል ይችላሉ።
በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት መስተዳደር የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን ቁ3