Be'kur (Sep 14, 2026)
የሐራጅ ጨረታ ማስታወቂያ
በአፈፃፀም ከሳሽ ሀና ሆቴል እቁብ ማህበር እና በአፈፃፀም ተከሳሸ እነ ሙላት ላቀው መካከል ስላለው የገንዘብ አፈፃፀም ከስ ከርከር ጉዳይ፤ የአፈፃፀም ተከሳሽ በፍርዱ መሰረት መፈፀም ባለመቻሉ ምክንያት የተከሳሽ ንብረት የሆነውን በቲሊሊ ከተማ ቀበሌ 01 በምስራቅ መንገድ፣ በምዕራብ ከፍት ቦታ፣ በሰሜን በላቸው ደሴ፣ በደቡብ ካሳሁን በላይነህ ተዋስኖ የሚገኘውና በአቶ ሙላት ላቀው ስም የተመዘገበ ቤት፤ ካርታ ቁጥር 7980/2007 እና 200 ካ.ሜ የሆነ ቤት፣ በመነሻ ዋጋ 1,803,221.33 (አንድ ሚሊዮን ስምንት መቶ ሶስት ሺህ ሁለት መቶ ሃያ አንድ ብር ከሰላሳ ሶስት ሳንቲም) ስለሚሸጥ ማስታወቂያው መስከረም 4 ቀን 2019 ዓ/ም ጀምሮ ለ30 ተከታታይ ቀናት በጋዜጣ ታትሞ ቆይቶ ጥቅምት 04 ቀን 2019 ዓ/ም ከጥዋቱ 3፡00 እስከ 5፡00 ድረስ ስለሚሸጥ ተጫራቾች የግምቱን 1/4ኛ ገንዘብ ቀድማችሁ በሲፒኦ አስይዛችሁ በዕለቱ መጫረት የምትችሉ መሆኑን ፍ/ቤት አዝዟል፡፡
የጓጉሳ ሽኩዳድ ወረዳ ፍ/ቤት