የቡሬ ወረዳ ፍ/ቤት የድርጅት ቤት የሐራጅ ጨረታ ማስታወቂያ አውጥቷል – test3.diretenders.com

የቡሬ ወረዳ ፍ/ቤት የድርጅት ቤት የሐራጅ ጨረታ ማስታወቂያ አውጥቷል


Be'kur (Sep 14, 2026)

በድጋሜ የወጣ የሐራጅ ጨረታ ማስታወቂያ

አፈ/ከሳሽ ምንታምር አዝመራው ጠበቃ ደምስ ሹመቴ እና አፈ/ተከሳሽ ስለሞን አስራት መካከል ስላለው የአፈጻጻም ክስ ክርክር ጉዳይ በቡሬ ከተማ አስተዳድር 02 ቀበሌ የሚገኝ አዋሳኝ በምሥራቅ መንገድ፣ በምዕራብ መንገድ፣ በሰሜን ሀሰን ነጋሽ፣ በደቡብ አያሌው ፈንታ መካከል ተዋስኖ የሚገኘውን 1000 ካ/ሜትር ቦታ ላይ የሚገኘውን የድርጅት ቤትና ንብረትነቱ የአፈጻጸም ከሳሽና ተከሳሽ የሆነውን መነሻ ዋጋውን ሳይጠብቅ በ0 /በዜሮ/ ማጫረት ይፈልጋል፡፡

ስለሆነም የጨረታ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ከመስከረም 04/2019 ዓ/ም ጀምሮ እስከ ጥቅምት 04/2019 ዓ/ም በማዋል ጥቅምት 05/2019 ዓ/ም ከረፋዱ 3፡30 እስከ 5፡00 ባለው ጊዜ ተጫራቾች የሚመዘገቡበት ሰዓት ሲሆን ጨረታው የሚካሄድበት ሰዓት ደግሞ ከረፋዱ 5፡00 እስከ 6፡00 ከፍተኛ ዋጋ ላቀረበ ተጫራች ይሸጣል፡፡

ተጫራቾች የግምቱን ¼ ኛውን በባንክ በተረጋገጠ (ሲፒኦ) በመያዝ ቡሬ ከተማ 02 ቀበሌ አስ/ጽ/ቤት ድረስ በመገኘት መጫረት የምትችሉ መሆኑን ፍ/ቤት አዝዟል፡፡

የቡሬ ወረዳ ፍ/ቤት


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *