በየካ ክ/ከተማ ወረዳ 05 ት/ፅ/ቤት ለት/ቤቱ አገልግሎት የሚውል የተለያዩ እቃዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል – test3.diretenders.com

በየካ ክ/ከተማ ወረዳ 05 ት/ፅ/ቤት ለት/ቤቱ አገልግሎት የሚውል የተለያዩ እቃዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል


Addis Zemen (Sep 13, 2026)

ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ

የግዥ መለያ ቁጥር 001/2018 ዓ.ም

በየካ ክ/ከተማ ወረዳ 05 ት/ፅ/ቤት ስር የሚገኘው የቡቃያ ቅድመ 1ኛ እና 1ኛ ደረጃ ት/ቤት በ2019 በጀት ዓመት ለት/ቤቱ አገልግሎት የሚውል የተለያዩ እቃዎችን በ1ኛ ዙር በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

  • ሎት 1/ የደንብ ልብስ፣
  • ሎት 2/ አላቂ የጽህፈት እቃዎች ፤
  • ሎት 3/ የህክምና አቃዎች፣
  • ሎት 4/ የህትመት ስራዎች ፤
  • ሎት 5 አላቂ የትምህርት እቃዎች ፤
  • ሎት 6/ አላቂ የፅዳት እቃዎች ፤
  • ሎት 7/ ቋሚ እቃዎች፤ ከላይ የተጠቀሱትን እቃዎች ማቅረብ የምትፈልጉ ተጫራቾች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን።

1.የዘመኑ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ፤ የንግድ ምዝገባ ሰርተፍኬት፤ ቲን/ቁ ማቅረብ የሚችሉ።

2.የዘመኑ ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣

3.የተጨማሪ እሴት ታክስ(VAT) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስከር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፣

4.ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከተ.ቁ-3 የተጠቀሱትን ማስረጃዎች ማያያዝ ይጠበቅባቸዋል።

5.ተጫራቾች ናሙና እንዲያቀርቡ ለተጠየቀባቸው እቃዎች የጨረታ ሰነዶችን ሊያስገቡ የተገለፀውን ናሙና ማቅረብ ግዴታ አሰበት፡፡

6. ለተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ሎት የደንብ ልብስ 4000.00 (አራት ሺህ ብር) ፤ ሎት2/ አላቂ የፅህፈትእቃዎች 4000.00 (አራት ሺህ ብር) ፤ ሎት3/ የህክምና አቃዎች 2000.00(ሁለት ሺህ ብር) ፤ ሎት4/ የህትመት ስራዎች 2000.00 (ሁለት ሺህ ብር) ሎት5/ አላቂ የትምህርት እቃዎች 3000.00(ሶስት ሺህ ብር) ፤ ሎት 6/ አላቂ የፅዳት እቃዎች 4000.00(አራት ሺህ ብር) ሎት7/ ቋሚ እቃዎች 5000.00(አምስት ሺህ ብር) መሳሪያዎች(እቃዎች) 4000.00(አራት ሺህ ብር)፤ በባንክ የተመሰከረስት ሲፒኦ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡

7.ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ 200.00 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል መውሰድ ይችላሉ፡፡

8.ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በሚገባ በመሙላት ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ አየር ላይ ከዋለበት ጊዜ ጀምሮ በ10 ተከታታይ የስራ ቀናት ዘወትር በስራ ሰዓት በቡቃያ ቅድመ 1ኛ ፤ መካከለኛ እና 1ኛ ደረጃ ት/ቤት ፋይ/ግዥ ክፍል ለዚሁ በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ኦርጅናል እና ኮፒውን በተለያየ በታሸገ ኤንቨሎፕበማድረግ ዋና እና ኮፒ መሆኑን በመግለጽ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ ተጫራቾች ተቋሙ የሸጠው ሰነድ መመለስ አለባቸው ከዛ ውጪ ተሞልተው የሚመጡ ሰነዶች ተቀባይነት የላቸውም::

9.ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ ስርዝ ድልዝ የሌለበት እና ቫትን ያካተተ መሆን አለበት ነገር ግን ቫትን ያካተተ መሆን አለመሆኑን የማይገለፅ ከሆነ የቀረበ ዋጋ ቫትን እንዳካተተ ተደርጎ ይወሰዳል፡፡

10.የጨረታው አሸናፊዎች ያሸነፉበትን እቃ 10% የውል ማስከበሪያ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡

11.የጨረታ ሳጥኑ በ10ኛ ቀን 11፡30 ታሽጎ በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4:30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ4፡30 በት/ቤቱ ፋይ/ግዢ ክፍል ውስጥ ይከፈታል፡

12.ከላይ የተዘረዘሩትን መስፈርቶች ያላሟላ ሰነድ ተቀባይነት የለውም፡፡

13.ት/ቤቱ በጨረታ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ ለሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው፡፡

አድራሻ፦ ከኬንያ ኢምባሲ 500 ሜትር ወደ ላይ በሚወስደው አስፓልት ገባ ብሎ ዳዊት ጋራዥ አጠገብ

ለተጨማሪ መረጃ፡- ስ/ቁ 0116663282/0666277

የቡቃያ ቅድመ 1ኛ፣ መካከለኛና 1ኛ ደረጃ ት/ቤት