የደ/ኤልያስ ከተማ መሪ ማዘጋጃ ቤት በከተማችን የዉስጥ የመንገድ ዳር ፓዉዛ ማቅረብ እና ማሰራት ስለተፈለገ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል – test3.diretenders.com

የደ/ኤልያስ ከተማ መሪ ማዘጋጃ ቤት በከተማችን የዉስጥ የመንገድ ዳር ፓዉዛ ማቅረብ እና ማሰራት ስለተፈለገ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል


Be'kur (Sep 14, 2026)

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

በምስ/ጎጃም ዞን በደ/ኤልያስ ወረዳ የሚገኘው የደ/ኤልያስ ከተማ መሪ ማዘጋጃ ቤት በ2019 በጀት ዓመት ከተያዘዉ ከመሰረተ ልማት ከወጭ መደብ 6324 (6257) የመብራት ዝርጋታ መሰረት በከተማችን የዉስጥ የመንገድ ዳር ፓዉዛ ማቅረብ እና ማሰራት ስለተፈለገ በግልዕ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች በጨረታው መሳተፍ የሚችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡

  1.  የዘመኑን ግብር የከፈሉ እና በዘርፋ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
  2.  የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ቲን ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  3.  የግዥ መጠኑ ከ200‚000 (ሁለት መቶ ሺህ) ብር በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚገልጽ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  4.  ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ የተጠቀሱትን እና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከጨረታ ሠነዶች ጋር አያይዞ ማቅረብ አለባቸው፡፡
  5.  የሚሰራዉ የመንገድ ዳር ፓዉዛ ዝርዝር መግለጫ ወይም ስፔስፋኬሽን ከጨረታ ሠነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
  6.  ተጫራቾች የጨረታ ሠነዱን በማይመለስ ብር 400 (አራት መቶ) ብር በመክፈል ከቢሮ ቁጥር 05 ማግኘት ይችላሉ፡፡
  7. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ለሚወዳደሩበት የመንገድ ዳር ፖዉዛ ጠቅላላ ዋጋ አንድ በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ ወይም ሲፒኦ ማስያዝ አለባቸው፡፡
  8. የጨረታ ሠነድ የሚሸጥበት ቦታ ደ/ኤልያስ ከተማ መሪ ማ/ቤት ቢሮ ቁጥር 05 ነው፡፡
  9. ጨረታው በጋዜጣ ታትሞ የሚቆየው ጋዜጣው ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 የስራ ቀናት ይሆናል፡፡
  10.  ተጫራቾች የገዙትን ሠነድ መመለስ የሚችሉት በጋዜጣ ከታተመበት እስከ 10 ኛው ቀን እስከ 11፡30 ድረስ በፖስታ በማሸግ ቢሮ ቁጥር 01 ድረስ በተዘጋጀ ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ ስለሆነም በ10ኛው ቀን ከቀኑ 11፡40 የጨረታ ሳጥኑ ይታሽጋል፡፡
  11. ጨረታው በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የሚከፈት ሲሆን ተጫራቾችም ሆነ ወኪሎቻቸው ባይገኙም እንኳን ጨረታው በእለቱ ደ/ኤልያስ ከተማ መሪ ማዘጋጃ ቤት አዳራሽ የሚከፈት ይሆናል።
  12. ጨረታው የሚከፈትበት ቀን በበአላት ቀን ከሆነ ቀጥሎ ባለው የሥራ ቀን ይሆናል፡፡
  13. የተጫራቾች ሰነዱ ስርዝ ድልዝ የሌለበትና ተነባቢ መሆን ይኖርበታል፡፡
  14.  በተጫራቾች ዋጋ ላይ ተንተርሶ ማቅረብ አይቻልም
  15. ውድድሩ በሎት ወይም ጥቅል ዋጋ የሚለይ ይሆናል፡፡
  16.  መ/ቤቱ ጨረታውን የተሻለ አማራጭ ካገኘ በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  17.  ጨረታዉ በመሰረዙ ተጫራቾች በጨረታዉ ለመወዳደር ላወጡት ወጭ መ/ቤቱ ሃላፊነት አይወስድም፡፡
  18. ቦታው ከምስ/ጎጃም ዞን ከደ/ማርቆስ ከተማ በምዕራብ አቅጣጫ 42 ኪ.ሜትር ርቀት ላይ የሚገኝ ሲሆን ተጨማሪ ማብራሪያ ካስፈለገ በከተማው መሪ ማዘጋጃ ቤት በአካል ቀርበው ወይም በስልክ ቁጥር 058 250 02 30/668 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡

የደ/ኤልያስ ከተማ መሪ ማዘጋጃ ቤት


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *