Be'kur (Sep 14, 2026)
የሐራጅ ጨረታ ማስታወቂያ
በአፈፃፀም ከሳሽ ሀና ሆቴል እቁብ ማህበር እና በአፈፃፀም ተከሳሸ እነ ሙላት ላቀው መካከል ስላለው የገንዘብ አፈፃፀም ከስ ከርከር ጉዳይ፤ አፈፃፀም ተከሳሽ በፍርዱ መሰረት መፈፀም ባለመቻሉ ምክንያት የአፈፃፀም ተከሳሽ ንብረት የሆነውን በቲሊሊ ከተማ ቀበሌ 01 በምስራቅ እና በምእራብ መንገድ፣ በሰሜን የትዋለ አድማስ፣ በደቡብ ጸጋየ የትዋለ የሚያዋስነው ፤ በአቶ መርሻ መኩሪያ ስም የተመዘገበ ቤት ካርታ ቁጥር 7424/2006 እና 500 ካ.ሜ የሆነ ቤት፣ ግምቱ 2‚351‚547.10 (ሁለት ሚሊዩን ሶስት መቶ ሃምሳ አንድ ሽ አምስት መቶ አርባ ሰባት ብር ከአስር ሳንቲም) ስለሚሸጥ የጨረታ ማስታወቂያው መስከረም 4 ቀን 2019 ዓ/ም ጀምሮ ለ30 ተከታታይ ቀናት በጋዜጣ ታትሞ ቆይቶ ጥቅምት 04 ቀን 2019 ዓ/ም ከጥዋቱ 3፡00 እስከ 5፡00 ድረስ ስለሚሸጥ ተጫራቾች የግምቱን 1/4ኛ ገንዘብ ቀድማችሁ በሲፒኦ አስይዛችሁ በዕለቱ መጫረት የምትችሉ መሆኑን ፍ/ቤት አዝዟል፡፡
የጓጉሳ ሽኩዳድ ወረዳ ፍ/ቤት