Be'kur (Sep 14, 2026)
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የአማራ ክልል ትም/ቢሮ በምዕራብ ጐጃም ዞን ት/መምሪያ በደጋ ዳሞት ትምህርት ጽ/ቤት ስር ለሚገኝ የፈረስ ቤት አጠ/2ኛ ደረጃ ት/ቤት ለመማር ማስተማር አገልግሎት የሚውሉ እቃዎችን
- ምድብ 1. የጽህፈት መሣሪያዎች፣ ወረቀትና የወረቀት ውጤቶች፣
- ምድብ 2. የኤሌክትሮኒክስ እቃዎችን በግልጽ ጨረታ መግዛት ይፈልጋል።
በጨረታው መሣተፍ የሚፈልጉ ድርጅቶች የሚከተሉትን መስፈርቶች በማሟላት መወዳደር ይችላሉ።
- በዘርፋ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
- የዘመኑን ግብር የከፈሉና የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር ሠርተፍኬት ማቅረብ የሚችሉ።
- ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በተከታታይ ለ15 ቀናት ፈ/ቤትአጠ/2ኛ/ደ/የከ/ትም መሠ/ት/ቤት ቢሮ ቁጥር 03 ድረስ በመቅረብ ለእያንዳንቸው የማይመለስ ብር 20 (ሀያ) ብር በመክፈል የተዘጋጀውን የእቃ ዝርዝር የያዘ የጨረታ ሠነድ መግዛት የሚችሉ ሲሆን ሠነዱ ስርዝ ድልዝ እና በፍሉድ የጠፋ ሣይኖረው በጥንቃቄ በመሙላትና በፖስታ በማሸግ የድርጅቱን አድራሻና ህጋዊ ማህተም ሙሉ ስምና ፊርማ በመጻፍ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን እስከ 16ኛው ቀን ከቀኑ 7፡30 ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- የመዘኑን ግብር የከፈሉ፡፡
- የግብር ከፋይነት ቲን ያላቸው፡፡
- ተወዳዳሪዎች ከ200,000 (ከሁለት መቶ ሺህ) ብር በላይ ከሆነ የቫት ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚገልጽ ሠርተፍኬት ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ የሚሆን ብር ከሞሉት ጠቅላላ ዋጋ ሁለት በመቶ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒዬ ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- ማንኛውም የጨረታ አሸናፊ ድርጅት ወይም ግለሰብ እቃዎችን ት/ቤቱ ድረስ በማምጣት በባለሙያ እያስፈተሸ ማስረከብ ይኖርበታል፡፡
- በጨረታ ሠነዱ ላይ በተገለጸው አይነትና እስፔስፊኬሽን መሰረት በትክክል ተሞልቶ መቅረብ ይኖርበታል፡፡
- የጨረታው ሣጥን በ16ኛው ቀኑ በ7፡30 ታሽጎ ከቀኑ 8፡00 ይከፈታል፡፡ በዚሁ እለት የበዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ቢሮ ቁጥር 03 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ቢገኙም ባይገኙም ጨረታው ይከፈታል፡፡
- ት/ቤቱ በውድድር የተገኘውን ዋጋ ሣይቀይር 20በመቶ ከፍ ዝቅ የማለት መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- የእቃዎች አሸናፊ የሚለየው በጥቅል ዋጋ ይሆናል፡፡
- የጨረታ አሸናፊው ማሸነፉ ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ ከ5 ቀን በኋላ በ3 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ያሸነፈበትን ዋጋ 10በመቶ የውል ማስከበሪያ በማስያዝ ውል መፈጸም ይኖርባዋቸዋል፡፡
- በጨረታው ለመሣተፍ የሚፈልጉ ስለጨረታው ዝርዝር ቢሮ ቁጥር 03 ድረስ በመገኘት ናሙና የማየት ግዴታ አለባቸው፡፡ ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ 09 18 55 0315 መደወል ይቻላል፡፡
- ት/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- በማስታወቂያው ያልተካተቱ ህጐችና ደንቦች በግዥ መመሪያው መሰረት ተፈጻሚ ይሆናሉ፡፡
የፈረስ ቤት አጠ/2ኛ ደረጃ ት/ቤት