Addis Zemen (Sep 15, 2026)
የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ
የፍ/ባለመብት ወ/ሪት ሄርሚላ ቴዎድሮስ እና የፍ/ባለዕዳ ወ/ሮ ሜሮን ለገሰ መካከል ስላለው የፍርድ አፈጻጸም ጉዳይ የፌደራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በመ/ቁጥር/109243 በ30/7/2016 ዓ/ም እና በኮ/መ/ቁ/111438 22/08/2016ዓ.ም በዋለው ችሎት በሰጠው ትዕዛዝ መሠረት ለማስፈፀም በአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ወረዳ 13 ውስጥ የሚገኝ የቤት ቁጥር 274 በካ /ቁ/ወ13/ 027101/30/661/00 በሰናይት ወርቅነህ እና ሄርሚላ ቴዎድሮስ ስም በተመዘገበ ይዞታ ውስጥ ከሚገኙ ቤቶች ውስጥ ሁለት ክፍል ቤት ከነማድ ቤቱ፤ሁለት ከፍል ዕቃ ቤቶች በብሎኬት የተሰሩ ሁለት ክፍል ቤቶች በብሎኬት የተሰሩ ሸንት ቤትና ሻውር ቆርቆሮ በቆርቆሮ የተሰራ አንድ ከፍል ቤት አጠቃላይ የቤቶቹ ስፋት 104.56 ካ/ሜ የሆነ አጠቃላይ የንፅፅር ድርሻ 121.83 ካ/ሜ በይዞታው ውስጥ የፍርድ ውሳኔ ያላረፈባቸው ቤቱ ያሉ መሆኑ የሐራጅ መነሻ ዋጋ ብር 5,083,125 (አምስት ሚሊዮን ሰማኒያ ሦስት ሺህ አንድ መቶ ሀያ አምስት ብር) ሆኖ የትራዛክሽን ታከስ ገዥ የሚከፍል መሆኑ ታውቆ ጥቅምት 6 ቀን 2019 ዓ/ም በሐራጅ ይሸጣል፡፡ የተጫራቾች ምዝገባ 4፡00 ሰዓት ተጀምሮ የቀረቡ ተጫራቾች ተመዝግበው እንደተጠናቀቀ ወዲያዉኑ ጨረታው የሚካሄድ ይሆናል፡፡
የሐራጁ ሽያጭ የሚካሄደው በፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት የጨረታ አዳራሽ ውስጥ ሲሆን፣ ንብረቱን ተጫርተው ለመግዛት የሚፈልጉ ተጫራቾች ከጨረታው ቀደም ብሎ ባሉት አራት የሥራ ቀናቶች ውስጥ ባለመብቱ ለማስጎብኘት በሚመርጧቸው ሶስት የስራ ቀናት በፌ/ፍ/ቤቶች ፍርድ አፈፃፀም ጽ/ቤት ሐራጅ ከፍል ድረስ ከጠዋቱ በ3፡30 ብቻ በመገኘትና ባለመብቱ በሚያቀርበው ትራንስፖርት ንብረቱን ባለበት ቦታ ድረስ በመውስድ ለመጐብኘት የሚችሉ ሲሆን ፤እያንዳንዱ ተጫራች በሚጫረትበት ወቅት የንብረቱን መነሻ ግምት 1/4 ኛውን በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተረጋገጠ CPO ማስያዝ ይኖርበታል፡፡ ከ1/4ው አስበልጦም ሆነ አሳንሶ የሚመጣ ተጫራች በጨረታው አይካፈልም፡፡ በጨረታው አሸናፊ የሆነው ግለሰብ አሸናፊ የሆነበትን ገንዘብ በአጠቃላይ ጨረታውን ከአሸነፈበት ቀን ጀምሮ በፍ/አፈ/ጽ/ቤት ስም CPO አሰርቶ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ብቻ ሙሉ ገንዘቡን በ15 ቀናት ውስጥ ገቢ ማድረግ አለበት፡፡ በጨረታ አሸናፊ የሆነ በጨረታ ያሸነፈበትን ገንዘብ ገቢ ሳይደረግ ቀርቶ በቀጣይ ጨረታ ተደርጎ ጨረታው ከበፊቱ ጨረታው ቀንሶ ከተሸጠ ገዥው በልዩነት ተጠያቂ እንደሚሆን የፍ/አፈ/ጽ/ቤት ንብረቱን በህጋዊ መንገድ በሐራጅ ስለመሸጡ ለሚመለከተው አካል ማስረጃ ከመጻፍ ባለፈ ስም የማዛወር ግዴታ የሌለበት መሆኑን እንገልፃለን፡፡
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር +251 112 730 852 በመደወል መጠየቅ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡
በፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈፃፀም ጽ/ቤት