በኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ ኢትዮጵያ ፕላስቲክ ኢንዱስትሪ በጥበቃ አገልግሎት ዘርፍ የተሰማሩ ድርጅቶችን በግልፅ ጨረታ ለአንድ አመት ማሰራት ይፈልጋል – test3.diretenders.com

በኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ ኢትዮጵያ ፕላስቲክ ኢንዱስትሪ በጥበቃ አገልግሎት ዘርፍ የተሰማሩ ድርጅቶችን በግልፅ ጨረታ ለአንድ አመት ማሰራት ይፈልጋል


Addis Zemen (Sep 16, 2026)

በሦስተኛ ወገን የሚፈጸም የጥበቃ ብሔራዊ ግልፅ

ጨረታ ግዥ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር 002/2019

በኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ ኢትዮጵያ ፕላስቲክ ኢንዱስትሪ በጥበቃ አገልግሎት ዘርፍ የተሰማሩ ድርጅቶችን በግልፅ ጨረታ ለአንድ አመት ማሰራት ይፈልጋል፡፡

ኢንዱስትሪያችን በአዲስ አበባ በቦሌ ክፍለ ከተማ ውስጥ ለሚገኘው ኢንዱስትሪ የጥበቃ አገልግሎት አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል ፡፡

ስለሆነም በጨረታው መወዳደር የሚፈልጉ ተጫራቾች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች ማሟላት አለባቸው፤

  1. የ2018/2019 በጀት አመት ህጋዊ በዘርፉ የታደሰ የንግድ ስራ ፈቃድ ፣ የንግድ ምዝገባ የምስክር ወረቀት ፣ የጊዜ ገደቡ ያላለፈበት በጨረታ ለመሳተፍ የሚያስችል ከሚከተለው የገቢ ሰብሳቢ መስሪያ ቤት የተሰጠ ማስረጃ (Tax Clearances) ፣ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር ሰረተፍኬት (Tin) ፤ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ የምስክር ወረቀት (VAT) ፣ በመንግስት ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ ድህረ ገፅ በአገልግሎት አቅራቢነት ዝርዝር ውስጥ መመዝገቡን የሚያረጋግጥ ማስረጃ (PPA Website supplier list) ማቅረብአለባቸው ::
  2. የግል የጥበቃ ተቋማት የብቃት ማረጋጫ የምስክር ወረቀት ከፖሊስ ማቅረብ የሚችል ፡፡
  3. ከሰራተኛና ማህበራው ጉዳይ ቢሮ አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችል ፍቃድ ማቅረብ የሚችሉ ::
  4. የጥበቃ አገልግሎት የሰጠ እና የመልካም ስራ አፈፃፀም ደብዳቤዎች የሚያቀርብ ::
  5. በጥበቃ ጉድለት ለሚፈጠር አደጋ ዋስትና የሚወስድ ( የሚሰጥ) ኢንሹራንስ ያለው ::
  6. የጨረታው ማስታወቂያ በጋዜጣ ላይ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በሚቆጠር ተከታታይ 15 ቀናት አየር ላይ የሚቆይ ሆኖ የጨረታ ሳጥኑ ከመዘጋቱ በፊት ለዚህ ተብሎ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ግዥ ክፍል ቢሮ በመምጣት እንድታስገቡ ተደርጎ ጨረታው የሚዘጋው በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ሆኖ በእለቱ 4፡30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል ፡፡ በ15ኛው ቀን የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተጠቀሰው ሰዓት ተዘግቶ የሚከፈት ይሆናል ፡፡
  7. የጨረታ ሰነዱ የማይመለስ ብር 500.00 (አምስት መቶ) በመክፈል ዘወትር በስራ ሰዓት ከሰኞ-አርብ ጠዋት 2፡00-6፡00 ሰዓት ከሰዓት ከ7፡00-11፡00 ሰዓት ኢንዱስትሪያችን ቅጥር ግቢ በመቅረብ ሰነዱን ከግዥ ከፍል መግዛት ይችላሉ ::
  8. የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ብር 50,000 ( ሀምሳ ሺህ ) ብር በ CPO ወይም Bank garant ቢያንስ ለ88 ቀናት ፀንቶ የሚቆይ ማቅረብ ይጠበቅበታል ፡፡
  9. ጨረታው ፀንቶ የሚቆየው ጨረታው ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ ለ60 ቀናት ነው ፡፡
  10. ኢንዱስትሪው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  11. ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥራችን 0116670485/0118592286 ደውሎ መጠየቅ ይችላሉ፡፡
  12. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነድ ላይ በየገጹ ስምና ፊርማ ማስገባት አለባቸው

አድራሻችን በመገናኛ ወደ ገርጂ በሚወስደው መንገድ ከአምቼ ዝቅ ብሎ ኒያላ ሞተርስ ፊትለፊት

ኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ የኢትዮጵያ ፕላስቲክ ኢንዱስትሪ


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *