Addis Zemen (Sep 18, 2026)
ድጋሚ የወጣ የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ
በፍ/ባለመብት ኑኑ ተሾመ እና በፍ/ባለዕዳ እነ ገነት ተሾመ መካከል ስላለው የፍርድ አፈጻጸም ጉዳይ የፌ/መ/ደ/ፍ/ቤት በኮ/መ/ቁ/37518 በ6/04/2007 ዓ.ም በኮ/መ/ቁ/115914 በ10/3/2017ዓ/ም በአቃቂ ቃሊቲ ከተማ ወረዳ 01 የቤ.ቁ 144 የሆነ በእነ ወ/ሮ ዘውዲቱ ተሾመ ባሕረ ስም ተደራጅቶ የሚገኝ የይዞታው ነባር ይዞታ ቢሆንም የይዞታ ማረጋገጫ ካርታ የሌለው (ሰነድ አልባ ይዞታ) አጠቃላይ የይዞታው ስፋት 1988ዓ.ም የGIS መረጃ መሠረት 2100 ካ/ሜ ሲሆን በአካል የተገኘ በተወሰደ ልኬት መሠረት 2055ካ/ሜ ሆኖ የሐራጅ ሽያጭ መነሻ ዋጋ ብር 58,339,755 (ሃምሳ ስምንት ሚሊዮን ሦስት መቶ ሰላሳ ዘጠኝ ሺህ ሰባት መቶ ሃምሳ አምስት) ሆኖ የትራንዛክሽን ታከስ ገዥ የሚከፍል መሆኑ ታውቆ ሐምሌ 22 ቀን 2018 ዓ.ም በሐራጅ ለመሸጥ ቀጠሮ ተይዞ በዕለቱ ተጫራች ባለመቅረቡ ምክንያት ጨረታው ሳይከናወን ቀርቷል፡፡ ስለሆነም በፌ/መ/ደ/ፍ/ቤት በኮ/መ/ቁ.115914 በ12/12/2018ዓ.ም በተሰጠው ትዕዛዝ መሠረት ድጋሚ ሐራጅ ሆኖ 1/4ኛ 14,584,938.75 (አስራ አራት ሚሊዮን አምስት መቶ ሰማንያ አራት ሺህ ዘጠኝ መቶ ሠላሳ ስምንት ከ75/00) ሆኖ የትራንዛክሽን ታክስ ገዥ የሚከፍል መሆኑ ታውቆ ጥቅምት 16 ቀን 2019 ዓ/ም በሐራጅ ይሸጣል፡፡ የተጫራቾች ምዝገባ 4፡00 ሰዓት ተጀምሮ የቀረቡ ተጫራቾች ተመዝግበው እንደተጠናቀቀ ወዲያውኑ ጨረታው የሚካሄድ ይሆናል፡፡
የሐራጁ ሽያጭ የሚካሄደው በፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት የጨረታ አዳራሽ ውስጥ ሲሆን፣ ንብረቱን ተጫርተው ለመግዛት የሚፈልጉ ተጫራቾች ከጨረታው ቀደም ብሎ ባሉት አራት የሥራ ቀናቶች ውስጥ ባለመብቱ ለማስጎብኘት በሚመርጧቸው ሦስት የሥራ ቀናት በፌ/ፍ/ቤቶች ፍርድ አፈፃፀም ጽ/ቤት ሐራጅ ክፍል ድረስ ከጠዋቱ በ3፡30 ጀምሮ በመገኘትና ባለመብቱ በሚያቀርበው ትራንስፖርት ንብረቱን ባለበት ቦታ ድረስ በመውሰድ መጎብኘት የሚችሉ ሲሆን፤ እያንዳንዱ ተጫራች በሚጫረትበት ወቅት የንብረቱን ግምት 1/4 ኛውን በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተረጋገጠ cPO ማስያዝ ይኖርበታል፡፡ ከ1/4ኛ አስበልጦም ሆነ አሳንሶ CPO የሚመጣ ተጫራች በጨረታው አይካፈልም፡፡ በጨረታው አሸናፊ የሆነው ግለሰብ አሸናፊ የሆነበትን ገንዘብ በአጠቃላይ ጨረታውን ከአሸነፈበት ቀን ጀምሮ በፍ/አ/ጽ/ቤት ስም CPO አሠርተው በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተከፈተ አሠርቶ ሙሉ ገንዘቡን በ15 ቀናት ውስጥ ገቢ ማድረግ አለበት በጨረታው አሸናፊ የሆነ በጨረታ ያሸነፈበትን ገንዘብ ገቢ ሳያደርግ ቀርቶ በቀጣይ ጨረታ ተደርጎ ጨረታው ከበፊቱ ጨረታ ቀንሶ ከተሸጠ ገዥው በልዩነት ተጠያቂ እንደሚሆን የፍ/አ/ጽ/ቤት ንብረቱን በሕጋዊ መንገድ በሐራጅ ስለመሸጡ ለሚመለከተው አካል ማስረጃ ከመፃፍ ባለፈ ስም የማዛወር ግዴታ የሌለበት መሆኑን እንገልፃለን፡፡ ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር +251112730852 በመደወል መጠየቅ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡
የፌዴራል ፍ/ቤቶች የፍርድ አፈፃጸም ጽ/ቤት