በኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ የየማነ ብርሃን አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት በግቢ ውስጥ ለሚሰሩ የግንባታ ስራ በጨረታ መሳተፍ የሚፈልጉ ተቋራጮችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል – test3.diretenders.com

በኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ የየማነ ብርሃን አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት በግቢ ውስጥ ለሚሰሩ የግንባታ ስራ በጨረታ መሳተፍ የሚፈልጉ ተቋራጮችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል


Addis Zemen (Sep 20, 2026)

የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር የማ/ብ/002/2019 የጨረታ ቁጥር የማ/1/02/2010

በኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ የየማነ ብርሃን አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት በግቢ ውስጥ ለሚሰሩ የግንባታ ስራ በጨረታ መሳተፍ የሚፈልጉ ተቋራጮችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡

 በመሆኑም ለሥራው አስፈላጊ የሆኑ ግብአቶችን፣ የተሟላ የሰው ሃይል እና ማሽነሪዎች በማቅረብ በተጠቀሰው ቀናት ውስጥ ስራውን ማጠናቀቅ የሚችልና የሚከተሉትን መስፈርቶች በማሟላት የጨረታ ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ፡፡

.

 

የስራ ቦታ

 

ወረዳ

 

የጨረታ ዋስትና ብር መጠን

የተቋራጭ ደረጃ

 

ጨረታው ፀንቶ የሚቆይበት ጊዜ

1

የየማነብርሃን አጠቃላይ 2 ደረጃ /ቤት በግቢ ውስጥ የሚሰራ የህንፃ ዙሪያ የድጋፍ ግንብ እና 31 ስፖርት ሜዳ አጥር ስራ

06

 

50,000.00

 

ደረጃ Gc7 /BC6 እና ከዚያ በላይ የሆነ ተቋራጭ

60 ቀን

 

1. ለስራው የንግድ ምዝገባና ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ኖሯቸው የዘመኑን ግብር የከፈሉ የታደሰ ንግድ ፈቃድ እና የብቃት ማረጋገጫ የምዝገባ የምስክር ወረቀት ያላቸው ከፌደራል ከተማ ልማት እና ኮንስትራክሸን ሚንስቴር የምዝገባ የምስክር ወረቀት እና ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ግንባታ ፈቃድና ቁጥጥር ባለስልጣን ገቢዎች በጨረታ መሳተፍ የሚያስችል ክሊራንስ ከሚመለከተው አካል ማቅረብ የሚችሉ፣ የአቅራቢነት ምዝገባ ያላቸው/supplier list/፣ ቫት ተመዝጋቢ የሆኑና የግብር መለያ ቁጥር ያላቸው ከሚሰራው ስራ ጋር ተመሳሳይነት ይዘት ያለውና የመልካም ስራ አፈፃፀም ማስረጃ ከመንግስት ተቋም ማቅረብ የሚችሉ፡፡

2. ተጫራቾች የጨረታ ውድድር ቴክኒካል እና ፋይናንሻል ግምገማ ስለሚኖረው ቴክኒካል ኦርጅናል አንድ ፖስታ እና ቴክኒካል ኮፒ ሁለት ፖስታ እና ፋይናንሺያል ኦርጅናልና አንድ ፋይናንሺያል ኮፒ ሁለት ፖስታ በድምሩ ስድስት ሰነድ ለየብቻ በታሸገ ፖስታ የድርጅቱ ፊርማ ማህተም እና የሚወዳደሩበትን ሰነድ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ወይም /Bid bond or bid security/ ለብቻ በታሸገ ፖስታ ላይ የድርጅቱን ፊርማ እና ማህተም በማድረግ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ በተጨማሪም የታሸገውን ሶስት ፖስታ የፋይናንሻል ሰነድ በአንድ ፖስታ በማሸግ የድርጅቱን ማህተም ፊርማና የሚወዳደሩበትን የግንባታ ስም በመፃፍ ታሽጎ መቅረብ ኖርበታል፡፡ ጨረታው ከላይ በተጠቀሰው ቀንና ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ወይም ሙሉ በሙሉ ባይገኙም የሚከፈት ይሆናል፡፡

3. ተጫራቾች ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ20 ተከታታይ የስራ ቀናት የሚቆይ ሲሆን ተጫራቾች የሚጫረቱትን የግንባታውን አይነት፣ ዝርዝር መግለጫ፣ ስራ ዝርዝር፣ መመሪያ ወይም ሰነድ ከመ/ቤታችን ግዥ ቢሮ ቁጥር 4 የማይመለስ ብር 300.00 /ሶስት መቶ ብር ብቻ/ በመክፈል መውሰድ ይችላሉ፡፡

4. ማሳሰቢያ ተጫራቾች የገዙትን የጨረታ ሰነድ ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 21ኛው ቀን ጠዋት 4፡00 ሰዓት ድረስ ለዚህ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ ጨረታ ሳጥኑ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ እለት 4፡30 ሰዓት ላይ የሚከፈት ይሆናል፡፡ 

5. ተጫራቾች ጨረታው ፀንቶ የሚቆይበት ጊዜ 60 ቀናት/ ለስልሳ ቀናት እና የጨረታ ማስከበሪያ ፀንቶ የሚቆይበት ጊዜ 28/ ሀያ ስምንት ቀናት/ ጨምሮ በድምሩ 88 ቀናት/ሰማንያ ስምንት ቀናት የሚያገለግል ወይም የሚቆይ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ወይም /Bid bond or bid security/ በባንክ ትዕዛዝ ወይም /CPO/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና /unconditional bank Guarantee/ በኮ/ቀ/ክ/ከ የማነብርሃን አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ስም የማቅረብ ግዴታ አለበት፡፡በተጨማሪም ጥቃቅንና አነስተኛ ማህበራት ካደራጃቸው የመንግስት ተቋም የሚሰጥ የጨረታ ማስከበሪያ የድጋፍ ደብዳቤ የጨረታ ማስከበሪያው ዋስትና የተሰጠበትን የገንዘብ መጠን በመጥቀስ በመስሪያ ቤቱ የበላይ ኃላፊ የተፈረመ መሆን አለበት፡፡ ተጫራቾች በጨረታ የሚያቀርቡት ዋጋ ወቅታዊ የገበያ ሁኔታን ያለገናዘበ እጅግ የተጋነነ እና ዝቅተኛ ወይም ከፍተኛ ዋጋ የሚሰራውን ስራ ያላማከለ ከሆነ ተጫራቾች የዋጋ ትንታኔ |cost break down/ ከተገቢው መረጃ ጋር ማቅረብ ይኖርቦታል፡፡ሆኖም የቀረበው ዋጋ ከስራው ጋር ያልተመጣጠነ/ unbalanced rate/ ከሆነ ተጫራቾች ከጨረታ ውድድር ውጪ ይደረጋል፡፡

6. ተጫራቾች ለጨረታ ያስገቡት ፋይናንሻል ሰነድ ነጠላ ዋጋ ላይ ያልተፈረመበት ዝርዝ ድልዝ እና ፍሉድ መጠቀም ከጨረታ ተወዳዳሪነት ያሰርዛል፡፡

7. በስራ ዝርዝር ላይ ነጠላ ዋጋ ሳይሞላ ከተገኘ ስራውን በነፃ እንደሚሰራ ይወሰዳል፡፡

8. ተጫራቾች የጨረታ ሰነድን የተጫራቾች መመሪያ በሚያዘው መሰረት ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡

9. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ለበለጠ ማብራሪያ ካስፈለገ በኮ/ቀ/ክ/ከ አስተዳደር የማነብርሃን አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት መጠየቅ ይቻላል፡፡
አድራሻ ፡- ኮ/ቀ/ክ/ከተማ ወረዳ 06 ወይራ ሰፈር አደባባይ ገባ ብሎ የማነብርሃን አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት
ስ.ቁ. 011 369 6814/011 349 0998

የማነብርሃን አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *