የቦታው ስፋት 494 ካ.ሜ የሆነ ቤት የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ – test3.diretenders.com

የቦታው ስፋት 494 ካ.ሜ የሆነ ቤት የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ


2merkato.com (Sep 21, 2026)

የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ

በፍርድ ባለመብት ህጻን ክርስቲያን መታሰቢያ እና በፍርድ ባለእዳ እነ እየሩስ ቁምላቸው መካከል ስላለው አፈፃፀም የፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በመ/ 107164 በቀን 13/4/2018.ም፣ በኮ//.107164 26/8/2018. በዋለው ችሎት በሰጠው ትእዛዝ በቂርቆስ /ከተ/ወረዳ 02 የቤት ቁጥር 299 የካርታ ቁጥር AA00004020/00 የቦታ ስፋት 494 / የሽያጭ ዋጋ መነሻ ግምት ብር 25,594,159 (ሃያ አምስት ሚሊየን አምስት መቶ ዘጠና አራት ሺህ አንድ መቶ ሃምሳ ዘጠኝ) ሆኖ የትራንዛክሽን ታክስ ገዥ የሚከፍል መሆኑ ታውቆ መስከረም 26 ቀን 2019 / በሐራጅ ይሸጣል። የተጫራቾች ምዝገባ 500 ሰዓት ተጀምሮ የቀረቡ ተጫራቾች ተመዝግበው እንደተጠናቀቀ ወዲያውኑ ጨረታው የሚካሄድ ይሆናል።

የሐራጁ ሽያጭ የሚካሄደው በፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈፃፀም ዳይሬክቶሬት የጨረታ አዳራሽ ውስጥ ሲሆን፣ ንብረቱን ተጫርተው ለመግዛት የሚፈልጉ ተጫራቾች ከጨረታው ቀደም ብሎ ባሉት አራት የሥራ ቀናቶች ውስጥ ባለመብቱ ለማስጎብኘት በሚመርጧቸው ሶስት የስራ ቀናት በፌ//ቤቶች የፍርድ አፈፃፀም ዳይሬክቶሬት ሐራጅ ክፍል ድረስ ከጠዋቱ 330 ብቻ በመገኘትና ባለመብቱ በሚያቀርበው ትራንስፓርት ንብረቱን ባለበት ቦታ ድረስ በመውሰድ ለመጐብኘት የሚችሉ ሲሆን እያንዳንዱ ተጫራች በሚጫረትበት ወቅት የንብረቱን መነሻ ግምት 1/4 ኛውን በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተረጋገጠ CPO ማስያዝ ይኖርበታል። ከ1/4 አስበልጦም ሆነ አሳንሶ የሚመጣ ተጫራች በጨረታው አይካፈልም። በጨረታው አሸናፊ የሆነው ግለሰብ አሸናፊ የሆነበትን ገንዘብ በአጠቃላይ ጨረታውን ከአሸነፈበት ቀን ጀምሮ በፍ/አፈ// ስም CPO አሰርቶ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ብቻ ሙሉ ገንዘቡን 15 ቀናት ውስጥ ገቢ ማድረግ አለበት በጨረታ አሸናፊ የሆነ በጨረታ ያሸነፈበትን ገንዘብ ገቢ ሳይደረግ ቀርቶ በቀጣይ ጨረታ ተደርጎ ጨረታው ከበፊቱ ጨረታው ቀንሶ ከተሸጠ ገዥው በልዩነት ተጠያቂ እንደሚሆን የፍ/አፈ/ዳይሬክቶሬት ንብረቱን በህጋዊ መንገድ በሐራጅ ስለመሸጡ ለሚመለከተው አካል ማስረጃ ከመጻፍ ባለፈ ስም የማዛወር ግዴታ የሌለበት መሆኑን እንገልጻለን።

በለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር +251 11 273 0852 በመደወል መጠየቅ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን።

 የፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈፃፀም /ቤት


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *