የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልላዊ መንግስት የመንገድና ትራንስፖርት ቢሮ የመንጃ ፈቃድ ማተሚያ ማሽን፤ ፋርጎ ፖሊጋርድ ኦቨር ላሚኔት፤ ሪቫን፤ ሆሎግራፊክስ ስትሪፕ ካርድ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል – test3.diretenders.com

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልላዊ መንግስት የመንገድና ትራንስፖርት ቢሮ የመንጃ ፈቃድ ማተሚያ ማሽን፤ ፋርጎ ፖሊጋርድ ኦቨር ላሚኔት፤ ሪቫን፤ ሆሎግራፊክስ ስትሪፕ ካርድ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል


Addis Zemen (Sep 25, 2026)

የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ  ቁጥር 02/2019

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልላዊ መንግስት የመንገድና ትራንሰፖርት ቢሮ በ2019 በጀት አመት በአሽ/ተሸ/ብ/ዳሬክቶሬት ሥር ለሚያከናውናቸው ሥራዎች የመንጃ ፈቃድ ማተሚያ ማሽን፤ ፋርጎ ፖሊጋርድ ኦቨር ላሚኔት፤ ሪቫን ፤ ሆሎግራፊክስ ስትሪፕ ካርድ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

በዚሁ መሰረት፡–

  1.  በመስኩ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው እና በበጀት ዓመቱ የንግድ ፈቃዳቸው የታደሠ፤ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑ ፤ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያላችሁ፣ እንዲሁም በአቅራቢነት የተመገባችሁ መሆናችሁ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ እንዲሁም እቃዎቹን ውል ከተገባ በኃላ በ20 ቀን ውስጥ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  2. በመስኩ ስራ ላይ ለመሰማራታቸው ህጋዊ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ ሁሉ ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ላይ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የጨረታውን ዝርዝር መግለጫ ሠነድ የያዘ ዶክመንት የማይመለስ ብር 500.00 (አምስት መቶ ብር) በመክፈል አስፈላጊውን ማስረጃ ከታደሰ ንግድ ፈቃድ ጋር በማድረግ አሶሳ በሚገኘው መንገድና ትራንስፖርት ቢሮ የግዥና ንብ/አስ/ዳ ዳሬክተር ቢሮ ቁጥር 10 በመቅረብ መውሰድ የምትችሉ መሆኑን፡፡
  3. የጨረታ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 10 ቀናት (አስር ቀናት) አየር ላይ ቆይቶ በ11ኛው (አስራ አንደኛው) ቀን ከቀኑ በ8፡00 ሰዓት ታሽጎ በዚሁ ዕለት ከቀኑ 8፡30 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት አሶሳ በሚገኘው መንገድና ትራንስፖርት ቢሮ የግዥና ንብ/አስ/ዳ/ ዳሬክተር ቢሮ  ቁጥር 10 ይከፈታል፡፡
  4. የጨረታው መክፈቻ ቀን የህዝብ በዓላት ወይም ቅዳሜ እና እሁድ ላይ ከሆነ በቀጣይ የሥራ ቀን እንዲከፈት ይደረጋል፡፡
  5.  ተጫራቾች የጨረታ ሰነዳቸውን በታሸገ ኤንቬሎፕ አንድ ኦርጅናል እና ሁለት ኮፒ ዶክመንት ለየብቻ በማድረግ እና በማዘር ኤንቨሎፕ በማሸግ አሶሳ በሚገኘው መንገድና ትራንስፖርት ቢሮ የግዥና ንብ/አስ/ዳ/ ዳሬክተር ቢሮ ቁጥር 10 ድረስ በአካል ሠነዱን ይዞ በመቅረብ ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  6. የጨረታው ማስከበሪያ ገንዘብ 100,000.00 /አንድ መቶ ሺህ/ በመ/ቤታችን ስም በተዘጋጀ CPO ብቻ ማቅረብ አለባቸው፤ CPO ሲታሸግ ለብቻው ከፋይናንሻል ወይም ቴክኒካል ውጪ ታሽጎ መቅረብ አለበት፡፡
  7. ተጫራቾች በሚያቀርቡት የነጠላ ዋጋ (ጠቅላላ ዋጋ) ስርዝ ድልዝ እና በእርሳስ የተሞላ ሠነድ ተቀባይነት የለውም፡፡ የሚቀርበው ዋጋ ከ15% ቫት ጋር ወይም ከ15% ቫት በፊት ተብሎ በግልጽ ተጽፎ መቀመጥ አለበት፤ ይህ ካልሆነ ተቀባይነት አይኖረውም፡፡
  8. ተጫራቾች የጨረታ ሠነድ ለመግዛት ሲመጡ የንግድ ፈቃድና የተጨማሪ እሴት ታክስ እና በአቅራቢነት የተመዘገቡበት ሰርቲፊኬት ኮፒውን ይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
  9. የእቃዎች መረካከቢያ ቦታ አዲስ አበባ ሆኖ በባለሙያ ከተረጋገጠ በኋላ ይሆናል ፡፡
  10. መ/ቤታችን የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

 ለበለጠ መረጃ በስልክ፡– 0577752622/0911130761 ዘወትር በስራ ሰዓት ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፡፡

የቤ/ጉ/ክልላዊ መንግስት የመንገድና ትራንስፖርት ቢሮ /አሶሳ


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *