Addis Zemen (Sep 25, 2026)
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት የምዕራብ ሐረርጌ ዞን ከፍተኛው ፍ/ቤት ለዞን ከፍተኛው ፍ/ቤት ስራ አገልግሎት የሚውሉ ቋሚ የቢሮ ዕቃዎች፣ የፅህፈት መሳሪያዎች፣ የፅዳት ዕቃዎች እና የደንብ ልብስ እንዲሁም የዳኞች ካባ በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
ስለሆነም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾችን በጨረታው አንዲሳተፉ ይጋብዛል።
1 ተጫራቾች ህጋዊ የንግድ ፈቃድ የታደሰና የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆኑን ህጋዊ ማስረጃ ማቅረብ የንግድ ፈቃድ የታደሰና የዘመኑን አለባቸው።
2. ተጫራቾች ባቅራቢዎች ዝርዝር የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚገልጽ ማስረጃ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
3. ተጫራቾች የተጨማሪ እሴት (VAT) ተመዝጋቢ የሆኑና ለዚሁ ማስረጃ የሚያቀርቡ መሆን አለባቸዉ። አሸናፊው ድርጅት ያሸነፈበትን ዕቃዎች በራሱ ትራንስፖርት እስከ ከፍተኛዉ ፍ/ቤት ዕቃ ግምጃ ቤት ድረስ ማቅረብ ይኖርበታል።
4. የጨረታ ማስከበሪያ 10000 (አስር ሺ ብር) በጥሬ ገንዘብ ወይም በባንክ በተረጋገጠ CPO ጨረታዉ ከመከፈቱ በፊት ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
5. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል ከላይ በተገለጸዉ የጽ/ቤት አድራሻ ቢሮ ቁጥር 104 በመቅረብ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር የመንግስት ስራ ሰዓት መግዛት ይችላሉ።
6. ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት እለት ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ የስራ ቀናት ለተጫራቾች ክፍት ይሆናል።
7. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የሚጫረቱበትን መወዳደሪያ የአንዱን ዋጋ በመጥቀስ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ውስጥ አድርገዉ እስከ 15ኛው ቀን 11፡30 ሰዓት ድረስ ቢሮ ቁጥር 104 ገቢ ማድረግ አለባቸው። ጨረታው በ15ኛዉ ቀን እለት 11፡30 ሰዓት ተዘግቶ ከረፋዱ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ በተገኙበት ይከፈታል። ተጫራቾቹ ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ ቢገኙም ባይገኙም ጨረታው ይከፈታል።
8. ተጫራቾች የተፈለገዉን ዕቃ ጥራትና ብዛት አሟልቶ የማቅረብ ግዴታ አለባቸው። የተጫረተበትን እቃ አሟልቶ ያላቀረበ እንደሆነ ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዘው ገንዘብ ለመንግስት ገቢ ሆኖ በሁለተኛ ደረጃ የተጫረተው እቃውን እንዲያቀርብ ይደረጋል።
9. በሽያጭ የቀረበዉ ዕቃ ጥራቱን ያልጠበቀ ከሆነ ነጋዴዉ (አሸናፊዉ ድርጅት በራሱ ወጪ ዕቃዉን የመለወጥ ወይም ገንዘቡን የመመለስ ግዴታ አለበት።
10. የማስጫኛና የማውረጃ ወጪ በተጫራቹ ይሸፈናል።
11. ጽ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻችን፡– ምዕ/ሐረርጌ ዞን ከፍተኛው ፍ/ቤት/ ጭሮ ሞባይል 0920454496/0942015828
የምዕ/ሐረርጌ ዞን ከፍተኛው ፍ/ቤት