Addis Zemen (Sep 25, 2026)
የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ
የፍ/ ባለበት ቅስት ሙሉጌታ እና የፍ ባለዕዳ እረጋ ወንድሙ መካከል ስላለው የፍርድ አፈጻጸም ጉዳይ በፌ/መ/ደ/ፍ/ቤት በመ/ቁጥር 160684 በ16/08/2017ዓ/ም እና በኮ/መ/ቁ/169580 በ6/2/2018 ም በዋለው ችሎት በሰጠው ትዕዛዝ መሠረት 1ኛ በልደታ ክ/ከተማ ወረዳ 09 የልደታ ብርሃን ብሎክ 1-14 የቤት ባለቤቶች ኃ/የተ/የግ/ማህበር ውስጥ ብሎከ 14 የቤት ቁጥር 401 በ4ኛፎቅ የሚገኝ ባለ 3 መኝታ ኮንደሚኒየም ቤት የቦታ ስፋት በካርታቸው መሰረት 91.90 ካ/ሜ የሐራጅ መነሻ ዋጋ ብር 4,389.971 (እራት ሚሊዮን ሶስት መቶ ሰማንያ ዘጠኝ ሺህ ዘጠኝ መቶ ሰባ አንድ) ሆኖ የትራንዛክሽን ታክስ ገዥ የሚከፍል መሆኑ ታውቆ ጥቅምት 19 ቀን 2019 ዓ.ም በሐራጅ ይሸጣል። የተጫራቾች ምዝገባ 4፡00 ሰዓት ተጀምሮ የቀረቡ ተጫራቾች ተመዝግበው እንደተጠናቀቀ ወዲያውኑ ጨረታው የሚካሄድ ይሆናል።
2ኛ በሎሚ ኩራ ክ/ከተማ ወረዳ 09 የሚገኝ ቤት እና ይዞታ በካርታ ቁጥር ቦሌ 15/222/79 –8015/60 የሴሪያል ቁጥር 024137 የይዞታ ስፋት 105 ካ/ሜ የሆነ G+3 መኖሪያ ቤት የሐራጅ መነሻ ዋጋ ብር 9,703.320 (ዘጠኝ ሚሊዮን ሰባት መቶ ሶስት ሺህ ሶስት መቶ ሃያ) ሆኖ የትራንዛክሽን ታከስ ገዥ የሚከፍል መሆኑ ታውቆ ጥቅምት 19 ቀን 2019 ዓ/ም በሐራጅ ይሸጣል። የተጫራቾች ምዝገባ 4፡30 ሰዓት ተጀምሮ የቀረቡ ተጫራቾች ተመዝግበው እንደተጠናቀቀ ወዲያውኑ ጨረታው የሚካሄድ ይሆናል።
የሐራጁ ሺያጭ የሚካሄደው በፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈፃፀም ጽ/ቤት የጨረታ አዳራሽ ውስጥ ሲሆን፤ ንብረቱን ተጫርተው ለመግዛት የሚፈልጉ ተጫራቾች ከጨረታው ቀደም ብሎ ባሉት አራት የሥራ ቀናቶች ውስጥ ባለመብቱ ለማስጎብኘት በሚመርጧቸው ሶስት የስራ ቀናት በፌፍ ቤቶች የፍርድ አፈፃፀም ጽ/ቤት ሐራጅ ክፍል ድረስ ከጠዋቱ በ3፡30 ብቻ በመገኘትና ባለመብቱ በሚያቀርበው ትራንስፖርት ንብረቱን ባለበት ቦታ ድረስ በመውሰድ ለመጐብኘት የሚችሉ ሲሆን እያንዳንዱ ተጫራች በሚጫረትበት ወቅት የንብረቱን መነሻ ግምት ¼ ኛውን በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተረጋገጠ CPO ማስያዝ ይኖርበታል። ከ1/4ው አስበልጦም ሆነ አሳንሶ የሚመጣ ተጫራች በጨረታው አይካፈልም፡፡ በጨረታው አሸናፊ የሆነው ግለሰብ አሸናፊ የሆነበትን ገንዘብ በአጠቃላይ ጨረታውን ከአሸነፈበት ቀን ጀምሮ በፍ አፈ ጽ/ቤት ስም CPO አሰርቶ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ብቻ ሙሉ ገንዘቡን በ15 ቀናት ውስጥ ገቢ ማድረግ አለበት በጨረታ አሸናፊ የሆነ በጨረታ ያሸነፈበትን ገንዘብ ገቢ ሳይደረግ ቀርቶ በቀጣይ ጨረታ ተደርጎ ጨረታው ከበፊቱ ጨረታው ቀንሶ ከተሸጠ ገዥው በልዩነት ተጠያቂ እንደሚሆን የፍ አፈ ጽ/ቤት ንብረቱን በህጋዊ መንገድ በሐራጅስለመሸጡ ለሚመለከተው አካል ማስረጃ ከመጻፍ ባለፈ ስም የማዛወር ግዴታ የሌለበት መሆኑን እንገልጻለን።
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር +251112730852 በመደወል መጠየቅ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን።
በፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈፃፀም ጽ/ቤት