Addis Zemen (Sep 25, 2026)
የጨረታ ማስታወቂያ
ፌ.ቤ.ኮ/ብግጨ/ዕቃ/11/01/2019
የፌደራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ለሊፍት እና ለጋራዥ አገልግሎት የሚውሉ የኤሌክትሮ መካኒካል እቃዎች ግዥ በጨረታ መለያ ቁጥር ፌ.ቤ.ኮ/ብግጨ/ዕቃ/11/01/2019 ተጫራቾችን አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
1. ለኮርፖሬሽኑ አገልግሎት የሚያገለግል የብረታ ብረት እና ተዛማጅ እቃዎች ግዥ ተጫራቾች የመወዳደሪያ ቴክኒካል ሰነዳቸውንና ዋጋቸውን በተለያዩ በታሸጉ ኤንቨሎፖች ማቅረብ አለባቸው፡፡
|
ተ.ቁ |
የዕቃ ዝርዝር |
የጨረታ ማስከበሪያ |
|
1 |
የኤሌክትሮ መካኒካል እቃዎች ግዥ |
50,000.00 |
2. ጨረታው የሚከናወነው በብሔራዊ ግልጽ ጨረታ ሥነ–ሥርዓትና ይኼንኑ አስመልክቶ በፌደራል መንግስት ባለቤትነት የተያዙ የመንግስት የልማት ድርጅቶች የግዥ አፈፃፀም መመሪያ 1070/2017 ሲሆን ከሚፈለገው የኤሌክትሮ መካኒካል እቃዎች ግዥ ጋር የተዛመደ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸውና የግብር ከፋይ ማስረጃ የሚያቀርቡ መሆን ይኖርበታል፡፡
3. የተሟላ የጨረታ ሰነዶችን ማንኛውም ፍላጎት ያለው ተጫራች ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ15 ተከታታይ ቀናት ውስጥ የማይመለስ ብር 500.00 /አምስት መቶ ብር/ በመክፈል የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ለገሀር በሚገኘው ኮርፖሬሽኑ ዋና መ/ቤት ህንፃ 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 201 በኮርፖሬሽኑ ግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት በአካል በመቅረብ መግዛት ይችላሉ ፡፡
4. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዶቻቸውን በኮርፖሬሽኑ ግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 201 ለዚሁ ታሽጎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ጨረታው በመጀመሪያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15 ኛው ቀን ወይም እስከ ጥቅምት 3 ቀን 2019 ዓ.ም ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ እንዲያቀርቡ ሆኖ ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ በሁኔታዎች ላይ ያልተመሰረተ በባንክ በተመሰከረለት የባንክ ዋስትና ወይም ሲ.ፒ.ኦ በፌደራል ቤቶች ኮፖሬሽን ስም ከጨረታ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡ ከጨረታው መክፈቻ ዕለትና ሰዓት ዘግይቶ የቀረበ የጨረታ ሰነድ ውድቅ ይደረጋል፤ ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጥቅምት 3 ቀን 2019 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ቀን ከጠዋቱ 4፡15 ሰዓት የኮርፖሬሽኑ ግዥና ንብረት አስተደደር ዳይሬክተር 1ኛ ፎቅ በሚገኘው የስብሰባ አዳራሽ ይከፈታል፡፡
5. ኮርፖሬሽኑ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለተጨማሪ መረጃ
በስልክ ቁጥር 011-85-53-617 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፡፡
ዌብሳይት/Website WWW.ash.gov.et
የፖ.ሣ.ቁ. P.0. Box 299
የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን