Addis Zemen (Sep 25, 2026)
የግስጽ ጨረታ ማስታወቂያ
ጨረታ ማስታወቂያ ቁ.04/2017
በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የገቢዎች ሚኒስቴር አዳማ ቅ/ጽ/ቤት በታከስ ዕዳ የያዛቸዉን ለቆዳ ማምረቻ የተዘጋጀውን ህንፃ ለመሸጥ የወጣ የግልጽ ጨረታ ማስታመቂያ ቁ.04/2017 የቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ግብር ከፋይ የሚጠበቅባቸውን የታከስ ዕዳ በታክስ ህጉ በተፈቀደዉ የጊዜ ገደብ ባለመክፈላቸዉ በታክስ አከፋፈል አዋጅ ቁጥር 983/2008 አንቀፅ 41 በተሠጠዉ ስልጣን መሠረት ጂዲ ኢንተርናሽናል ትሬዲንግ ኃ/የተ/የግ/ማህበር የተያዛ ህንጻ ባሉበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።
1.በግልጽ ጨረታዉ የሚፈልግ ማንኛዉም ተጫራች ማንነቱን የሚገልጽ የነዋሪነት መታወቂያ (ፓስፖርት) ኮፒ ከጨረታ ሰነድ ጋር አያይዞ በኢንቨሎፕ በማሸግ በግልጽ ጨረታ በተዘጋጀዉ ሳጥን ዉስጥ ማስገባት ይኖርበታል።
2. ተጫራቾች የጨረታዉን ሰነድ ይህ የግልጽ ጨረታ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰዓት ከሰኞ እስከ አርብ ከ2፡00 ሰዓት – 11፡00 ሰዓት እና ቅዳሜ ጠዋት ከ2፡00 – 6፡00 ሰዓት ከቴሌ ከፍ ብሎ ቅ/ጽ/ቤቱ አዲሱ ባስገነባዉ ህንጻ 4ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 403 ከግዥ ፋይናንስና ንብረት አስተዳደር ቢሮ የማይመለስ ብር 200.00(ሁለት መቶ ብር) በመክፈል የጨረታ ሰነዱን መዉሰድ ይኖርቦታል።
3. በግልጽ ጨረታ ለመሳተፍ ተጫራቾች ለሚወዳደሩባቸዉ ንብረቶች የሰጡትን ዋጋ 1/10ኛዉን ብቻ ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (CPO) በገቢዎች ሚኒስቴር አዳማ ቅ/ጽ/ቤት ስም (Ministry of Revenue Adama Branch Office) በባንክ አሰርተዉ ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
4. ተጫራቾች የሚከተለዉ የጨረታ ቀናት (ስኬጁል) መሰረት ሰነድ ገዝተዉ መጫረት ይችላሉ።
|
ተ.ቁ
|
የመ/ቤቱ ስም
|
ለጨረታ የቀረበዉ የንብረት ዓይነት |
የንብረቶቹ መመልከቻ ቀን |
የጨረታዉ የመዝጊያ እና የመክፈቻ ቀንና ሰዓት |
|
1
|
ገቢዎች ሚኒስቴር አዳማ ቅርንጫፍ
|
የቆዳ ማምረቻ ተዘጋጃ ህንጻ17,514.00 ካሬ ላይ ያረፈ. |
ማስታወቂያዉ በጋዜጣ ከወጠበት ቀን ጀምሮ ለ15 ቀናት |
ማስታወቂያዉ በጋዜጣ ወጥቶ 15 ቀን ከተጠናቀቀ በኋላ ቀጥሎ ባለዉ 16ኛ ቀን 3፡45 ተዘግቶ በዚያዉ ቀን በ4፡00 ሰኣት ይከፈታል። |
5. የጨረታ መክፈቻ ቦታ፡- በገቢዎች ሚኒስቴር አዳማ ቅ/ጽ/ቤት ከቴሌ ከፍ ብሎ ባስገነባው አዲሱ ህንጻ 4ኛ ፎቅ ከግዥ ፋይናንስና ንብረት አስተዳዳር ቢሮ ቁጥር 403 ሲሆን ተጫራቾች ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባሉበት ወይም ታዛቢዎች ባሉበት ይከፈታል።
6. የግልጽ ጨረታዉ መከፈቻና መዝጊያ 16ኛዉ ቀን የመ/ቤቱ የሥራ ቀን ካልሆነ በቀጣዩ ቀን የግልጽ ጨረታዉ መክፈቻና መዝጊያ ቀን ይሆናል።
7. ለጨረታዉ አሸናፊ ተጫራቾች ለጨረታዉ ማስከበሪያ ዋስትና ያስያዙት (CPO) ከሚከፈሉት ዋጋ ጋር እንደ አስፈላጊነቱ የሚታሰብላቸዉ ሲሆን ለተሸናፊ ተጫራቾች ደግሞ የግልጽ ጨረታ ኮሚቴዉ መረጃዉን አጣርቶ እንደጨረሰ በ5 የስራ ቀናት ዉስጥ ተመላሽ ይደረግላቸዋል።
8. የህንጻ ጨረታ ለሚያሸንፉ ተጫራቾች ከስመ-ንብረት ንብረት ዝዉዉር ጋር ተያያዥነት ላቸዉን ወጪዎች ሻጭን አይመለከትም።
9. አሸናፊ ተጫራቾች ማሸነፋቸዉን በደብዳቤ ከተገለጸለት ቀናት ጀምሮ ባሉት 15 ቀናት ዉስጥ ያሸነፉበትን ጠቅላላ ዋጋ ቅ/ጽ/ቤቱ በሚሰጠዉ አድራሻ ገቢ በማድረግ ሀብት ንብረት መረከብ ይኖርበታል።
10. ከላይ በተ.ቁ 9 በተገለጸዉ ቀናት ዉስጥ ከፍያዉን ገቢ በማድረግ ንብረታቸዉን ያልተረከቡ ተጫራቾች የግልጽ ጨረታዉ ተሠርዞ ለጨረታ ማስከበሪያ በ CPO ያስያዙት የዋስትና ገንዘብ ለመ/ቤቱ ገቢ ሆኖ ንብረቱ ተቆጥሮ በቀጣይ በድጋሚ ለሽያጭ ይቀርባል።
11. ቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ የግልጽ ጨረታዉን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነዉ።
ለተጨማሪ ማብራሪያ
ስልክ ቁጥር፡- 022-211-1873/ 022-211-1728 እና 022-211-0762 ደዉሎ መጠየቅ ይቻላል።
ገቢዎች ሚኒስቴር አዳማ ቅ/ጽ/ቤት