Addis Zemen (Sep 25, 2026)
የጨረታ ማስታወቂያ አቃ/ቃ/ክ/ከ/አነ/ግ/ከ/ቅ/ጽ/ቤት 001/2019
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ የአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ አነስተኛ ግብር ከፋዮች ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ የሚከተሉትን እቃዎች ግዥ መፈፀም ይፈልጋል።
- የደንብ ልብስ፣ የጽህፈት መሳሪያ እቃዎች፣ የህትመት ስራዎች፣ ልዩ ልዩ እቃዎች፣
- የጽዳት እቃዎች፣ የመኪና ማስዋቢያ እቃዎች፣ የተለያዩ ኮምፒውተር፣ ፕሪንተር እና
- ፎቶ ኮፒ ማሽን የጥገና መለዋወጫ እቃዎች፣ የአገልግሎት ጥገና እቃዎች፣ የውሃ ግዥ፣ ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች እና ቋሚ እቃዎች ሲሆኑ
በጨረታው መሳተፍ የሚፈልጉ ድርጅቶች የሚከተሉትን መስፈርቶች ማሟላት ይጠበቅባቸዋል።
1. ከሚወዳደሩበት እቃ ወይንም አገልግሎት ግዥ ጋር ለመወዳደር ተያያዥነት ያለው የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆኑ የሚያረጋግጥ ማስረጃዎችን (ክሊራንስ) ከግብር አስገቢው መ/ቤት ማቅረብ የሚችሉ።
2. በመንግስት ግዥና ንብረት አስተዳደር አገልግሎት ባዘጋጀው የእቃና አገልግሎት ግዥ በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ መሆኑን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።
3. ለተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆኑን እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (Tin Number) ሰርተፊኬት ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።
4 የሀገር ውስጥ የድጋፍ አቅራቢዎች ምዝገባ ምስክር ወረቀት (በጥቃቅን አነስተኛ የተደራጁ ማህበራት የተደራጁ መሆኑን እና ከአደራጃቸው አካል ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣ ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ መጠን ለአጠቃላይ ከሎት አንድ እስከ ሎት አስራ አንድ 1% ለእያንዳንዳቸው ሎቶች በባንክ በተመሰከረለት (CPO) ከጨረታ ሰነዱ ጋር ለብቻ በፖስታ አሽገው አያይዘው ማቅረብ አለባቸው። C.PO መሰራት ያለበት በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ ለአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ አነስተኛ ግብር ከፋዮች ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በሚል አድራሻ መሆን አለበት።
5. ተጫራቾች በአማርኛ ቋንቋ የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ ቀናት ቅዳሜን ጨምሮ እስከ 11፡30 በስራ ሰዓት የማይመለስ ብር 200.00 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ጨረታ መክፈቻው ቀን ድረስ ቃሊቲ ቶታል ፊት ለፊት ካፍደም ጎን ሰለሞን ህንጻ ከሚገኘው አቃቂ ቃሊቲ ክ/ ከተማ አነስተኛ ግብር ከፋዮች ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ግዥና ፋይናንስ የሥራ ሂደት 3ተኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 308 በመቅረብ መግዛት ይችላሉ። የሚያቀርቡት ዋጋ ቫትን ያጠቃለለ እና ስርዝ ድልዝ ሳይኖረው መሆን አለበት።
6. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋ በጥንቃቄ በማሸግ ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 11ኛው ቀን ድረስ ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት በፊት ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይገባቸዋል። ጨረታው በዚሁ እለት ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ታሽጎ ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት በመ/ ቤቱ 3ተኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 308 ግዥና ፋይናንስ የስራ ሂደት ቢሮ ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል። እለቱ የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት ይከፈታል። እያንዳንዱ ተጫራች ለጨረታ ለመወዳደር በሚቀርብበት ወቅት ፋይናንሺያል እና ቴክኒካል ኦሪጅናል እና ኮፒ እንዲሁም (CPO) ለብቻ በማሸግ እና አምስቱንም ፖስታዎች በአንድ ትልቅ ፖስታ በማሸግ መቅረብ ይኖርበታል።
7. ሰነዱን በሚመልስበት ወቅት ስልጣን ባለው አካል መፈረምና የድርጅቱ ማህተም መደረግ አለበት ነገር ግን የሚፈርመው አካል ተወካይ ከሆነ የውክልና ማስረጃ መያያዝ አለበት።
8. የጨረታው አሸናፊ የአሸናፊነት ደብዳቤ እንደደረሰው የመልካም ስራ አፈፃፀም ዋስትና 10% (አስር ፐርሰንት) CPO በማስያዝ ከመ/ቤቱ ጋር ውል ይፈራረማል።
9. ተጫራቾች በሚወዳደሩባቸው ሁሉም እቃዎች ላይ የጨረታ ሰነዱን ሲያስገቡ ናሙናዎችንም ለግዥና ፋይናንስ የሥራ ሂደት ማስረከብ አለባቸው።
10. የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ጸንቶ የሚቆይበት ጊዜ ጨረታው ከተከፈተበት ጀምሮ ለ90 ቀናት መቆየት አለበት።
11. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለተጨማሪ ማብራሪያ
ስልክ ቁጥር፡-011 471-5712/አዲስ አበባ
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ የአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ አነስተኛ ግብር ከፋዮች ቅርንጫፍ ጽ/ቤት