Addis Zemen (Sep 25, 2026)
የጨረታ ማስታወቂያ
የደቡብ ቤንች ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት በወረዳው ከተማ ልማት ኮንስትራክሽን ጽ/ቤት በ2019 በጀት ድጋፍ በዘልሚ መንደር ለሚገነባው አደባባይ፣ ካልቨርት እና የመንገድ አካፋይ ስራ በዘርፉ በተሰማሩ ድርጅቶች በጨረታ አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል።
በዚህም መሰረት በጨረታው ላይ ለመወዳደር ለምትፈልጉ ተጫራቾች ከዚህ በታች የተዘረዘረው ዝቅተኛ መስፈርቶች ማሟላት ይጠበቅባቸዋል።
1. በዘርፉ ህጋዊና የታደሰ የንግድ ፍቃድ ያለው/ላት
2. በደረጃ 5Gc እና ከዚያ በላይ የሆነ ድርጅት
3. በዘርፉ የንግድ የምዝገባ የምስክር ወረቀት ያለው እና ኮፒውን አያይዞ ማቅረብ የሚችል።
4 የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆነ እና ኮፒውን አያይዞ ማቅረብ የሚችል።
5. የቲን ነምበር/ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር/ ያለው/ላት
6. የንግድ ምዝገባ ሰርተፊኬት ማቅረብ የሚችሉ።
7. ተጫራቾች በጨረታ ላይ ሲወዳደሩ የጨረታ ማስከበሪያ ብር 100,000 (አንድ መቶ ሺህ) በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
8. የታደሰ የብቃት ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችል
9. የሳይት ምልከታ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል
10. ጨረታው ለ21 ተከታታይ ቀናት ክፍት ሆኖ በ21ኛው ቀን ከሰዓቱ 4፡00 ላይ ታሽጎ በ21ኛው ቀን ከሰዓቱ 4፡30 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በይፋ ይከፈታል።
11. ተጫራቾች የጨረታውን ዶክመንት ከደ/ቤ/ወ/ፋይናንስ/ጽ/ቤት ከግዥና ንብረት አስ/ር ቢሮ ቁጥር 2 በአካል በመቅረብ የማይመለስ ብር 500 (አምስት መቶ ብር) በመክፈል የጨረታውን ዶክመንት መግዛት ይኖርባቸዋል።
12. ተጫራቾች የጨረታውን ዶክመንት ቴክኒካሉን 1 ኦርጅናል እና 2 ኮፒ እንዲሁም ፋይናንሻሉን 1 ኦርጅናል እና 2 ኮፒ ለየብቻ በማሸግ ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
13. ተጫራቾች ያስገቡት የጨረታ ዶክመንት ሙሉ ከሆነ ተጫራቾቹ ቢገኙም ባይገኙም የጨረታ ፖስታዎች ይከፈታል። ነገር ግን ዕለቱ ዝግ ወይንም በዓል ከሆነ በቀጣይ ስራ ቀን የሚከፈት ይሆናል።
14. ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ ቫትን ያካተተና ያላካተተ መሆኑን በግልጽ ማስቀመጥ ይኖርባቸዋል። ያለበለዚያ ያስገቡት ዋጋ ቫትን ያካተተ ተደርጎ ይወሰዳል።
15. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ ፡– የደቡብ ቤንች ወረዳ ፋ/ኢ/ል/ጽ/ቤት
ደ/ወርቅ ስልክ፡ /09 29 24 17 31 / 09 10 99 77 47
የደቡብ ቤንች ወረዳ ፋ/ኢ/ል/ጽ/ቤት ጽ/ቤቱ