በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በጌዴኦ ዞን የወናጎ ከተማ አስ/ር ፋ/ጽ/ቤት በወናጎ ከተማ አስተዳደር ከሚገኙ ከተለያዩ ሴ/መ/ቤት በቀረበው ጥያቄ መሰረት በ2019 በጀት ዓመት የጽህፈት መሣሪያና አላቂ የቢሮ ዕቃ ግዥ ለመፈፀም ይፈልጋል – test3.diretenders.com

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በጌዴኦ ዞን የወናጎ ከተማ አስ/ር ፋ/ጽ/ቤት በወናጎ ከተማ አስተዳደር ከሚገኙ ከተለያዩ ሴ/መ/ቤት በቀረበው ጥያቄ መሰረት በ2019 በጀት ዓመት የጽህፈት መሣሪያና አላቂ የቢሮ ዕቃ ግዥ ለመፈፀም ይፈልጋል


Addis Zemen (Sep 25, 2026)

የጨረታ ማስታወቂያ

ብሔራዊ ጨረታ ቁጥር 001/2019

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በጌዴኦ ዞን የወናጎ ከተማ አስ/ር ፋ/ጽ/ቤት በወናጎ ከተማ አስተዳደር ከሚገኙ ከተለያዩ ሴ/መ/ቤት በቀረበው ጥያቄ መሰረት በ2019 በጀት ዓመት የጽህፈት መሣሪያና አላቂ የቢሮ ዕቃ ግዥ ለመፈፀም ይፈልጋል።

በመሆኑም መ/ቤቱ የሚገባቸውን ዕቃዎች ዝርዝር የያዘ ሰነድ በሽያጭ የሚቀርብ ስሆን ተወዳዳሪዎች የሚከተሉትን መስፈርቶችን የሚያሟሉ ተጫራቾችን ይጋብዛል።

በጨረታው የሚሳተፉ ተጫራቾች ማሟላት ያለባቸው መስፈርቶች ፡–

  • በዘርፉ ሕጋዊ የንግድ ሥራ ፍቃድ ያላቸው፣
  • የዘመኑን ግብር የከፈለ /ከመንግስት ዕዳ ነጻ የሆነ/፣
  • የታደሰ የንግድ ስራ ፍቃድ ያላቸው ፣
  • የ/VAT/ ተመዝጋቢ የሆኑ፣
  • የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር ያለው/ TIN NO/
  • በአቅራቢነት የተመዘገቡ፣
  • አሸናፊ ድርጅት መክፍል ያለበትን የሽያጭ ታክስ 3% ይከፍላል።
  • አሸናፊ ድርጅት የውል ማስከበርያ ያሸነፈበትን ገንዘብ ልክ 10% ያስይዛል።
  • በጨረታ ላይ ለመሳተፍ የድርጅቱ ገንዘብ መቀበያ QR ኮድ ደረሰኝ አሳትሞ በእጁ የያዘ መሆን አለበት፣
  • ተጫራቾች ይህ ማስታውቂያ በአዲስ ዘመን ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የጨረታ ሠነዱን ከወናጎ ከተማ አስ/ር ፋ/ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 02 በመቅረብ በማይመለስ ብር 500ብር /አምስት መቶ ብር/ ብቻ በመግዛት መወዳደር ይችላሉ።
  • ዋጋ አቅራቢ ተወዳዳሪዎች የዕቃ ዓይቱንና ደረጃውን በሰነዱ ዝርዝር በተቀመጠው ቅደም ተከተል ሞልተው አንድ ፋይናንሻል ኦርጅናል እና አንድ ቴክኒካል ኦርጂናል ዶክመንት ለብቻውን እንዲሁም ፋይናንሻልና ቴክኒካል ኮፒ ለየብቻ በማድረግ ሁሉንም በሰም በታሸገ በእንድ እናት ፖስታ ማቅረብ አለባቸው።
  • ተጫራቾች የጨረታ ማስከበርያ /CPO/ በባንክ በተረጋገጠ 30,000 ብር በፊደልም (ሰላሳ ሺህ ብር) ማስያዝ ያለበት ሲሆን፤ /CPO/ ለብቻው ታሽጎ ከኦርጂናል ቴክኒካል ዶክመንት ጋር መቅረብ አለበት።
  • ጨረታው የሚከፈተው ይህ ጨረታ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ የሥራ ቀናት አየር ላይ ቆይተው በ16ኛው ቀን የሚከፈት ስሆን ዕለቱ በዓል ወይም ቅዳሜና ዕሁድ ከሆነ በቀጣይ ሥራ ቀን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ወ/ከ/ፋ/ጽ/ቤት በመሰብሰብያ አደራሽ ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ታሽጎ በ4፡30 ይከፈታል።
  • ማንኛውም ተጫራች እንዱ ባቀረበው ዋጋ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም።

ማሳሰቢያ፣ መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለበለጠ መረጃ፡– 09 49 15 97 55 / 09 32 19 48 07 

ደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በጌዴኦ ዞን የወናጎ ከተማ አስ/ር ፋ/ጽ/ቤት


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *