ደቡብ ኢትዮጵያ ዲዛይንና ግንባታ ቁጥጥር ድርጅት በ2019 ዓ.ም ድርጅቱ ካለው የስራ እንቅስቃሴ አንፃር የኪራይ መኪና ውለታ በመግባት በክልሉ ውስጥ ባሉ የተለያዩ ፕሮጀክቶች ለማሰማራት ለመስክ አገልግሎት የሚውል በሀገር አቀፍ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መከራየት ይፈልጋል – test3.diretenders.com

ደቡብ ኢትዮጵያ ዲዛይንና ግንባታ ቁጥጥር ድርጅት በ2019 ዓ.ም ድርጅቱ ካለው የስራ እንቅስቃሴ አንፃር የኪራይ መኪና ውለታ በመግባት በክልሉ ውስጥ ባሉ የተለያዩ ፕሮጀክቶች ለማሰማራት ለመስክ አገልግሎት የሚውል በሀገር አቀፍ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መከራየት ይፈልጋል


Addis Zemen (Sep 25, 2026)

የጨረታ ማስታወቂያ

ለሰርቪስ መኪና አከራዮች ምዝገባ የወጣ ማስታወቂያ

የጨረታ መለያ ቁጥር NCB 003/2019

ድርጅታችን ደቡብ ኢትዮጵያ ዲዛይንና ግንባታ ቁጥጥር ድርጅት ለመስክ አገልግሎት የሚውሉኪንግ ካፕ፣ደብል ካፕና ስቴሽንዋገን መኪኖችን ሲከራይ መቆየቱ ይታወቃል። በ2019 ዓ.ም ድርጅቱ ካለው የስራ እንቅስቃሴ አንፃር የኪራይ መኪና ውለታ በመግባት በክልሉ ውስጥ ባሉ የተለያዩ ፕሮጀክቶች ለማሰማራት ለመስክ አገልግሎት የሚውል በሀገር አቀፍ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መከራየት ይፈልጋል።

በዚሁ መሰረት፡–

1. በዘርፉ ተገቢ የሆነ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣

2. በጨረታ ለመሳተፍ ከገቢዎች የተሰጠ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣

3. ከአንድ መኪና በላይ የሚያቀርቡ ከሆነ የቫት ተመዝጋቢ የሆነ፣

4. ቢያንስ የአንድ መኪና የባለቤትነት ማረጋገጫ ሊብሬ ኮፒ የራሳቸው ካልሆነ ከ3ተኛ ወገን በውልና ማስረጃ የተወከሉበትን ውክልና አያይዘው ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው፡፡

5. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋ በታሸገ ፖስታ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ ቀናት ውስጥ እስከ 10ኛው ቀን 8፡30 ሰዓት ድረስ በድርጅቱ ግዥና ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 1ኛ ፎቅ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል። ጨረታው ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ10ኛው ቀን በቀኑ 8፡30 ሰዓት ላይ ተዘግቶ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ 9፡00 ላይ ይከፈታል። 10ኛው ቀን የስራ ቀን ካልሆነ ጨረታው በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓትና ቦታ ተዘግቶ ይከፈታል፡፡

6. ተጫራቾች የተዘጋጀውን ዝርዝር የጨረታ ብር ከድርጅቱ ግዥና ንብረት አስተዳደር በነጻ ቀርበው መውሰድ ይችላሉ፡፡

7. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን የጨረታ ሰነድ በታሸገ ኤንቨሎፕ አንድ ኦርጅናል ኮፒ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

8. ድርጅቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 0913 164 287 / 0964 064 989 / 0900 175 526 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።

የድርጅቱ አድራሻ ወላይታ ሶዶ ሊጋባ ት/ቤት አለፍ ብሎ ከሚገኘው ጦና አደባባይ ፊት ለፊት ነው፡፡

ደቡብ ኢትዮጵያ ዲዛይንና ግንባታ ቁጥጥር ድርጅት


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *